• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

በአዲስ አበባ ገቢዎች የታክስ ኦዲት ባለሙያ ሌቦች ተያዙ

September 19, 2024 02:18 pm by Editor Leave a Comment

በአዲስ አበበ ከተማ የታክስ ኦዲት ቡድን አስተባባሪ፣ ባለሙያዎች እና ደላሎች በሙስና ወንጀል እጅ ከፍንጅ ተይዘው በቁጥጥር ሥር ዋሉ።

የአዲስ አበበ ከተማ አስተዳዳር ገቢዎች ቢሮ ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ኦዲት ቡድን አስተባባሪ የሆኑት፦ 

1ኛ. ሃብታሙ ግዲሳ ጆቴ 

2ኛ. ስምረት ገ/እግዚአብሔር አሰፋ የከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ኦዲት ከፍተኛ ኦፊሰር 

3ኛ. ዮሴፍ ባቡ ሆራ የከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ኦዲት ከፍተኛ ኦፊሰር 

4ኛ. አቤኔዘር ቶሎሳ ሙሉ የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ታክስ ኦዲት ከፍተኛ ኦፊሰር 

5ኛ. ለሚ ሲሌ ከፍተኛ ግብር ከፋይ የታክስ ኦዲት ከፍተኛ ኦፊሰር እና 

6ኛ. መቅደስ አረጋዊ ገንዘብ ተቀባይ የሆኑት በቀን 06/01/2017 ዓ.ም 

በሙስና ወንጀል ተጠርጥረዉ በቁጥጥር ስር ውለዉ ምርመራ እየተጣራ እንደሚገኝ የከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል።

ከ1ኛ እስከ 5ኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሱት ተጠርጣሪዎች በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር ገቢዎች ቢሮ ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ኦዲት ቡድን አስተባባሪ እና ባለሙያዎች ናቸው።

ጳጉሜ 05/2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ውስጥ ግብር ከፋይ ከሆኑ ግለሰብ የ2011 ዓ.ም እና 2012 ዓ.ም የአንድ አመት ግብር ኦዲት እንዲደረግላቸዉ የሚጠበቅበትን ሰነድ ያቀረበላቸዉ ሲሆን መክፈል ያለብህ አንድ መቶ ሚሊየን ብር (100,000000) ነዉ በማለት የገለፁለት በመሆኑ፤ ይህን ያህል አልከፍልም ካልክ ግማሹን አስይዘህ ነዉ ይግባኝ የምታቀርበዉ በማለት ማቅረባቸው ተገልጿል።

ጊዜዉ በቁጥጥር ስር ያልዋለ ግለሰብ ሂሳብ አስጨራሽ በሚል የቀረ ደላላ ጉዳዩን አስተካክላለሁ በሚል በማግባባት ለራሱ ሶስት ሚሊየን ብር (3,000,000) እና ለሰራተኞቹ ስምንት ሚሊየን ብር (8,000,000) ለመንግስት ከመቶ ሚሊየን በመቀነስ አስራ ሶስት ሚለየን ብር (13,000000) ትከፍላለህ በማለት ማስማማታቸው ነው የተገለፀው።

በዚህም (8,000,000) ስምንት ሚሊየን ብር በቤተሰቦቻቸዉ አማካኝነት በመቀበል 13,000,000 (አስራ ሶስት ሚሊየን) ብር የመንግስት የሚከፈለዉን እንዲከፍል መተማመኛ ሲሰጡት በተደረገ ክትትል እጅ ከፍንጅ የተያዙ እና ምርመራዉ ቀድሞ በነበረዉ ክትትል በስፋት እየተጣራ እንደሚገኝም ከከተማ አስተዳደሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። (ኢቢሲ)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: News, Right Column Tagged With: abenezer, habtamu, lemmi, mekdes, operation dismantle tplf, simret, theives at addis ababa revenue office, yosef

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ ሕዝብ ደም የሚደረገው የሥልጣን ቁማር ያብቃ! October 14, 2026 11:04 pm
  • የኒዳል ሀሰን በርሸና የሞት ፍርድ ሲፈጸምበት በቀጥታ ሥርጭት እንዲተላለፍ መወሰኑ ውዝግብ አስነሳ October 9, 2026 12:33 pm
  • ሴቶችን በመሾም ኢትዮጵያ በእርግጥ ተወዳዳሪ የሌላት ነች?  October 8, 2026 11:20 pm
  • Ethiopian Defense Forces Capture Advanced TPLF Military Drones and Documents Linked to Sudan October 7, 2026 12:40 pm
  • በሱዳን በኩል ለትህነግ የተላኩ የM6 ድሮኖችና ወታደራዊ መሣሪያዎች በመከላከያ እጅ መግባታቸው ተገለጸ October 7, 2026 11:20 am
  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
Copyright © 2026 · Goolgule