ይህን ከባድ የተፈጥሮ አደጋ በቸልታ የሚታለፍ አይደለም። አፋር የሃገራችን ዳር ድንበር ለዘመናት እየጠብቁ የቆዩ፣ የሰው ልጆችን ሁሉ በእኩልነት እና በክብር ተቀብለው የሚያስተናግዱ እንግዳ ተቀባይ እና ከሌሎች ጋር ተካፍለው መብላት ህይወታቸው የሆነ የኢትዮጵያ ውድ ህዝቦች ናቸው።
እነዚህ ወገኖቻችን ባጋጠማቸው ከፍተኛ የሆነ የጎርፍ አደጋ ከ200 ሺህ ህዝብ በላይ ተፈናቅሎ የመንግስትን እና የህዝብን ድጋፍ እየጠበቁ ነው።
ሰብዓዊነት ሁሉም ሊሰማው ይገባል። አንድ አካላችን ሲታመም ሁሉም አካላችን እንደሚታመም ሁሉ የአፋር ወገኖቻችን ጉዳት እና ህመም እኛንም ሊያመን ይገባል።
በሌላ በኩል ፦
ጣና ሐይቅ በከፍተኛ ደረጃ ከመጨመሩ የተነሳ ውሃው ተመልሶ በሐይቁ ዙሪያ ያሉ ቀበሌዎችን እያጥለቀለቀ ይገኛል።
በዚሁ ምክንያት እስካሁን ድረስ በደንቢያ ወረዳ ከ600 በላይ ሰው እንደተፈናቀለ መረጃ የደረሰኝ ሲሆን ፎገራ ወረዳ ሁለት ቀበሌዎች፤ ሊቦ ከምከም ወረዳ ደግሞ አራት ቀበሌዎች በውሃ ተጥለቅልቀዋል።
የውሃው መጠን አሁን ካለው በላይ ጨምሮ ጉዳት እንዳይደርስ ሕዝቡ ከአካባቢው እንዲነሳና ወደ ደረቅ ቦታ እንዲሰፍር ማድረግ አስፈላጊ ነው።
ጉዳዩ የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ተገቢውን ትኩረት ሰጥተው ክትትል ሊያደርጉ ይገባል።
(ኡስታዝ አቡበክር አህመድ፣ መልካሙ ሹምዬ ኮከብ)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply