• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ

September 25, 2026 11:07 pm by Editor Leave a Comment

* ወደ ኋላ መመለሻ ድልድያቸው ተሰብሯል

በትህነግ፣ በሻዕቢያ፣ በአገው ሸንጎ እና በፋኖ መካከል የተመሠረተው የጥፋት ኃይሎች ጥምረት በሰቆጣ እና በአብዓላ ግንባሮች በከፈተው መጠነ-ሰፊ ማጥቃት በሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ የገጠመውን ሽንፈት ተከትሎ፣ ሙሉ በሙሉ የመበታተንና የመደምሰስ አደጋ እንደተጋረጠበት ለጎልጉል የደረሱ የውስጥ ምንጮችና ወታደራዊ ተንታኞች ገለጹ።

ከግንባር ለጎልጉል የደረሱ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፣ በጥምረቱ ስም በሚንቀሳቀሱት የትህነግ አርሚ 22 እና አርሚ 92 የጦር ክፍሎች እጅግ ከባድ የሰው ኃይልና የቁሳቁስ ኪሳራ ደርሷል።

ትህነግ በድሮን ፍርሃቻ ጥንት በበረኻ እያለ ሲደርግ እንደለመደው በአህያ እና በግመል በብዙ መከራ ያጠራቀመው መሣሪያና ቁሳቁስ ነው በሰሞኑ ጥቃት እንዳለ የወደመበት።

በዋግኸምራ ዞን የምትገኘውን ሰቆጣ ከተማን ለመቆጣጠር በከፍተኛ ጉራና የቅድመ-ዝግጅት ስብስብ አሰፍስፎ የመጣው ይኸው የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በማይበገረው የሀገር መከላከያ ሠራዊት እና በጀግናው 13ኛው እዝ አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቷል።

በቅርቡ ተመሠረተ በተባለው የሰባት ታጣቂ ቡድኖች ስብስብ የአገው ሸንጎ በይፋ ስሙ ባይጠራም በትህነግ ትዕዛዝ ታጣቂውን አሰማርቶ ይገኛል።  

ላለፉት ሦስት ቀናት በዛታ ወረዳ አድርጎ ወደ ሰቆጣ ለመግባት ውጊያ ሲያደርግ የነበረው የጥምረቱ አርሚ 22 ታጣቂ ቡድን፣ በመከላከያ ሠራዊቱ ብርቱ ክንድ ተመትቶ በመበታተን ላይ ይገኛል። ከተመታው የጥምረቱ ኃይል የተረፉት ታጣቂዎች ወደ ኮረም አቅጣጫ ለመፈርጠጥ የሞከሩ ቢሆንም፣ አሁንም በሰቆጣ ዙሪያ ፍጹም ተስፋ በቆረጠ ሁኔታ ከፍተኛ ውጊያ እያደረጉ መሆኑ ተጠቁሟል።

የጎልጉል የውስጥ ምንጮች እንዳረጋገጡት፣ የመጣው ወራሪ የጥምረት ኃይል እንደ ቅጠል ረግፎ ወደ ኋላ እየፈረጠጠ ሲሆን፣ የተረፈውም የጥራሪ ወንዝ እራት ሆኗል። የቀረውም የጥምረቱ ታጣቂ በየጢሻው እየገባ በመሸሸግ ላይ ይገኛል።

ለዚህ ጥምረት ትልቁ መርዶ የሆነው ግን ታጣቂዎቹ ወደ ኋላ የሚያፈገፍጉበት እና የሚመለሱበት ድልድይ አሁን ሙሉ በሙሉ የተሰበረ መሆኑ ነው። በመሆኑም በአሁኑ ወቅት በሰቆጣ ምድር ለተከበበው የጠላት ኃይል የቀረው ምርጫ ሁለት ብቻ ነው፤ እርሱም እጅ መስጠት ካልሆነም ሙሉ በሙሉ መደምሰስ!

በተመሳሳይ በአብዓላ አቅጣጫ በጥምረቱ አርሚ 92 ላይ የተከፈተው ውጊያ እስከ አመሻሽ ድረስ የቀጠለ ሲሆን፣ በመከላከያ የእግረኛ ጦር በተሰነዘረ ጥቃት የጠላት ኃይል ክፉኛ ተመትቷል። ውጊያውን ተከትሎ በሚግ (Mig) ተዋጊ ጄቶችና በድሮን የተደገፈው ድንገተኛ የአየር ጥቃት በጥምረቱ ይዞታ ላይ ከባድ ውድመት አስከትሏል።

በዚህ የአየር ድብደባ የጥምረቱ ሁለት የዙ-23 ፀረ-አውሮፕላን መሣሪያዎችና አንዲት ብረት ለበስ ታንክ ሙሉ በሙሉ ተቃጥለው ከጥቅም ውጭ መሆናቸውን ምንጮቻችን አረጋግጠዋል። ዛሬም በአብዓላ አካባቢ የተጀመረውን ማጥቃት በመቀጠል ሙሉ ቁጥጥር ለማድረግ ሠራዊቱ እየገሰገሰ መሆኑ ታውቋል።

ይህንን ወቅታዊ ወታደራዊ ሽንፈት አስመልክቶ አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ወታደራዊ ተንታኝ ለጎልጉል እንደተናገሩት፣ “እስካሁን ባለው ሁኔታ የሀገር መከላከያ ሠራዊት በማጥቃት ሳይሆን በመከላከል ስልት ላይ ሆኖ ነው ይህንን ያህል ግዙፍ ጉዳት በጥምረቱ ላይ ያደረሰው” ብለዋል።

ተንታኙ አክለውም፣ ትህነግና ተባባሪዎቹ በመከላከል መስመር ላይ በነበረው ሠራዊት ይህንን ያህል ከፍተኛ የሰውና የቁሳቁስ ውድመት ከደረሰባቸው፣ መከላከያ ሠራዊቱ በሙሉ ኃይሉ ወደ ማጥቃት ሲሸጋገር የቡድኑ ዕጣ ፈንታ ምን ሊሆን እንደሚችል ለመገመት እንደማያዳግትና ከሚጠበቀው በላይ እጅግ ከፍተኛ ጉዳት እንደሚደርስባቸው አብራርተዋል።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: News, Slider Tagged With: Agew Shengo, ethiopian terrorists, operation dismantle tplf, tplf, tplf terrorist

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule