* ወደ ኋላ መመለሻ ድልድያቸው ተሰብሯል በትህነግ፣ በሻዕቢያ፣ በአገው ሸንጎ እና በፋኖ መካከል የተመሠረተው የጥፋት ኃይሎች ጥምረት በሰቆጣ እና በአብዓላ ግንባሮች በከፈተው መጠነ-ሰፊ ማጥቃት በሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ የገጠመውን ሽንፈት ተከትሎ፣ ሙሉ በሙሉ የመበታተንና የመደምሰስ አደጋ እንደተጋረጠበት ለጎልጉል የደረሱ የውስጥ ምንጮችና ወታደራዊ ተንታኞች ገለጹ። ከግንባር ለጎልጉል የደረሱ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፣ በጥምረቱ ስም በሚንቀሳቀሱት የትህነግ አርሚ 22 እና አርሚ 92 የጦር ክፍሎች እጅግ ከባድ የሰው ኃይልና የቁሳቁስ ኪሳራ ደርሷል። ትህነግ በድሮን ፍርሃቻ ጥንት በበረኻ እያለ ሲደርግ እንደለመደው በአህያ እና በግመል በብዙ መከራ ያጠራቀመው መሣሪያና ቁሳቁስ ነው በሰሞኑ ጥቃት እንዳለ የወደመበት። በዋግኸምራ ዞን የምትገኘውን ሰቆጣ ከተማን … [Read more...] about የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ

