ባለፈው ሳምንት በተጠናቀቀው የአማራ ምክርቤት ስብሰባ ላይ የሰላ ሒስ የሰነዘሩት የምክር ቤት አባል ዮሐንስ ቧያለው ያለመከሰስ መብት ተነስቶ በአገር ክህደትና በመሳሰሉ ወንጀሎች እንዲቀጡ ጥያቄ መቅረብ ጀምሯል። አቶ ዮሐንስ ከስብሰባው በኋላ ሲናገሩ ተሰምተዋል በተባለው የድምጽ ቅጂ በአገር ክህደት ሊያስጠይቃቸው ይገባል የሚል ሃሳብ እየተሰጠ ነው። አቶ ዮሐንስ ቧያለው ከጥቂት ቀናት በፊት በተጠናቀቀው የአማራ ክልል ምክርቤት ስብሰባ ላይ ግማሽ ሰዓት ያህል በመውሰድ በክልሉ አሉ ያሏቸውን ችግሮች በዝርዝር ሲያስረዱ ተሰምተዋል። እንደ እርሳቸው አገላለጽና ግምገማ ክልሉ ምንም የሚጠቀስ ውጤታማ ሥራ አልሠራም። ወደፊትም አይሠራም፣ ባጭሩ ክልሉና አመራሩ ከሸፏል ነው ያሉት። በተለይ ንግግራቸው ሲጀምሩ ስብሰባው ቀጥታ ሊተላለፍ እንደሚገባና አፈጉባዔዋ ይህንን በመፍቀድ ታሪክ መሥራት … [Read more...] about የዮሐንስ ቧያለው ያለ መከሰስ መብት እንዲነሳና በአገር ክህደት እንዲከሰሱ ተጠየቀ
digital woyane
ባለፉት 3 ዓመታት የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ሲያሰራጩ ከነበሩ 49%ው በዲጂታል ወያኔ የተከፈቱ ናቸው
ባለፉት 3 ዓመታት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ሲያሰራጩ ከነበሩ አካውንቶች ውስጥ 49 በመቶ የሚሆኑት በዲጂታል ወያኔ ቡድን የተከፈቱ አካውንቶች ናቸው ተባለ። የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ በወጣው መግለጫ 122,000 ሀሰተኛ የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶች በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ንቁ ተሳትፎ ያደርጋሉ ብሏል። ከእነዚህ የሀሰት መረጃ ከሚያሰራጩ አካውንቶች ውስጥ 49 በመቶ የሚሆኑት በዲጂታል ወያኔ ቡድን የተከፈቱ መሆናቸውን አጀንሲው ተነግሯል። ከዚህ በተጨማሪም የህውሐት ቡድን በ2013 ዓ.ም ጦርነት በከፈተበት ህዳር ወር ብቻ 17,000 የሚሆኑ ሀሰተኛ የቲዊተር አካውንቶችም በዲጂታል ወያኔ ቡድን ተከፍተው ነበር ተብሏል።የኤጀንሲው የግልጽ ምንጭ መረጃ ኦፕሬሽን ማዕከል ኃላፊ የሆኑት አቶ አሸናፊ ኃይሉ በቡድኑ በተከፈቱ ሀሰተኛ አካውንቶች … [Read more...] about ባለፉት 3 ዓመታት የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ሲያሰራጩ ከነበሩ 49%ው በዲጂታል ወያኔ የተከፈቱ ናቸው
የመከላከያ ሚኒስትር ለማ መገርሳ መልቀቂያ አላቀረቡም!!
ዜናው የውሸት ነው ለሥራ ወደ አሜሪካ ያቀኑት የመከላከያ ሚኒስትር ለማ መገርሳ የሥልጣን መልቀቂያ ማስገባታቸውን ጠቅሶ ፋኑኤል ክንፉ ፈንታሌ በሚባለው የግል የዩቲዩብ ገጹ በድምጽ ያሰራጨው ዜና ከእውነት የራቀ መሆኑ ተጠቆመ። “የፈንታሌ ሚዲያ ምንጮች" እንደነገሩት ያስታወቀው ፋኑኤል ክንፉ ዜናው እውነት እንደሆነ አድርጎ ለማሳየት የተጠቀመው አቶ ለማ ለቪኦኤ የሰጡትን ቃለ ምልልስ ነው። ለአቶ ለማም ሆነ በኦሮሚያ ጉዳይ እጅግ ቅርብ የሆኑ የሚዲያ ውጤቶች ለጊዜው ምንም ያላሉበትን ጉዳይ ፋኑኤል ምንጮቹን ጠቅሶ ይህንን አነጋጋሪ ዜና ትናትን ሌሊት (በአዲስ አበባ አቆጣጠር) ላይ መለጠፉ አነጋጋሪ ሆኗል። ዛሬ ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የመከላከያ ሚኒስትርን ጠቅሶ እንዳለው ከሆነ የአቶ ለማ የስልጣን መልቀቅ ጥያቄ የሚታወቅ አይደለም። … [Read more...] about የመከላከያ ሚኒስትር ለማ መገርሳ መልቀቂያ አላቀረቡም!!
ጃዋር፤ ለኦሮሚያ የተጠመደ ፈንጂ!
“… ስሙን መጥቀስ ባያስፈልግም አንድ ጎረምሳ ልንለው እንችላለን። ጃዋር ዜግነቱ አሜሪካዊ በመሆኑ የጃዋር ሚዲያ የተመዘገበው በዚህ ጎረምሳ ስም ነው። ከየአቅጣጫው የሚሰበሰበው ገንዘብ የሚቀመጠው በዚሁ ልጅ ስም ነው። መኪኖችና አንዳንድ ንብረቶች የሚገዙትም በዚሁ ስም ነው። ይህ ጎረምሳ አዲስ አበባ እጅግ መንዛሪና በከፍተኛ ቅንጦት እንደሚኖር የሚያውቁት ነገረውኛል። የቄሮ አካልም አልነበረም። ቄሮ ከድል በኋላ ቤቱ ሲመለስ የጠበቀው ማሳውና መደቡ ሲሆን እነ ጃዋርና ስማቸውን የሚጠቀሙባቸው ጎረምሶች በሚሊዮኖች እየረጩ ዘመናዊ ተሽከርካሪ ይሸምታሉ፤ ንብረት ያከማቻሉ፤ ሰዎች ሰላም ሰፍኖ በተረጋጋ መልኩ እንዳያስቡ ቀውስ ይመረትላቸዋል። ልክ ከዚህ በፊት ተደርጎ እንደማይታወቅ በዓሉንም፣ ልደቱንም፣ በሚዲያ እያስጮሁ ያሳብዱታል። ይህ ወጣት የሰከነ ዕለት ለጃዋር የሚቀርብለት ጥያቄ ስለሚታወቅ … [Read more...] about ጃዋር፤ ለኦሮሚያ የተጠመደ ፈንጂ!
የወቅቱ የአገራችን ችግር፤ የሐሰት ዜና ወረርሽኝ!
በኢትዮጵያ ደረጃ የሚታየው መድረሻውን ያስቀመጠ የሀሰተኛ መረጃ ሻሞ ወይም እርባታ ሕዝብን እንደ ዋዛ እያሳከረ፣ አገርን ለአደጋ የሚዳርግ፣ ታስቦበት፣ በዕቅድ፣ በባለሙያ፣ በበጀት፣ በድርጅት፣ በመሪ፣ በሥልጠና የሚከናወን የዘመኑ የዲጂታል ጦርነት ነው። ሰሞኑን የፓሪስ ከተማ ክፉኛ ተንጣ ነበር። የናጣት በማኅበራዊ ሚዲያ የተሰራጨ አንድ ሐሰተኛ መረጃ ሲሆን፣ መረጃው “የፓሪስ ውሃ ተመርዟልና አትጠጡ” የሚል የጅምላ ጥሪ ነበር። መረጃው የነፍስ ጉዳይ በመሆኑ የከተማዋን ነዋሪዎች ክፉኛ ናጣቸው። ይህንን አሸባሪ መረጃ ለመከላከል የፓሪስ አካባቢ ኃላፊዎች መግለጫ እንዲሰጡ አስገደዳቸው። በመሆኑም አርብ ሐምሌ 12፤ 2011 (ጁላይ 19) ተመረዘ የተባለው ውሃው እንደተባለው እንዳልተመረዘና ለመጠጥም ቢሆን ምንም የማያሰጋ መሆኑን አስረግጠው ተናገሩ። ይህ የሐሰት መረጃ ፓሪስን … [Read more...] about የወቅቱ የአገራችን ችግር፤ የሐሰት ዜና ወረርሽኝ!
ዲጂታል “ወያኔ”፤ “እረኛውን ግደል፣ መንጋው ይበተናል”
አገራችን ከህወሓት አፋኝ የግፍ አገዛዝ ወጥታ በለውጥ ሒደት ውስጥ ትገኛለች። ሆኖም በአፋኙ ዘመነ ወያኔ እንኳን ሆኖ በማያውቅ መልኩ በአሁኑ ጊዜ አገራችንን እያፈረሰ የሚገኘው በማኅበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ ያለው የሃሰትና የፈጠራ ዜና ነው። ለዚህ ደግሞ በርካታ መዋዕለ ንዋይ እየፈሰሰ ቀንተሌት ተግተው የሚሠሩ “የሳይበር ወታደሮች” ተመድበዋል። እነዚህ በተለይ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በትጋት የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች ዓላማቸው መረጃ ማዛባት፤ የሃሰት መረጃ መበተን፤ የሚወጡ መረጃዎችን ማወዛገብ (ሕዝብ እውነቱንና ሐሰቱን እንዳይለይ ማድረግ)፤ ወዘተ ናቸው። ይህ በዕዝና ቁጥጥር የሚመራ ኃይል ዋና ትኩረት የሚያደርገው በለውጡ ዙሪያ ያሉትን አመራሮች ማጠልሸት፤ የሕዝብ ድጋፋቸውን ማምከን፤ ከተቻለም ሕዝብ እንዲነሳባቸው ማድረግ ነው። ከዚህም በተጨማሪ በልዩ ልዩ ረቂቅ ስልት በሚበትኑት መረጃ … [Read more...] about ዲጂታል “ወያኔ”፤ “እረኛውን ግደል፣ መንጋው ይበተናል”