ባለፈው ሳምንት በተጠናቀቀው የአማራ ምክርቤት ስብሰባ ላይ የሰላ ሒስ የሰነዘሩት የምክር ቤት አባል ዮሐንስ ቧያለው ያለመከሰስ መብት ተነስቶ በአገር ክህደትና በመሳሰሉ ወንጀሎች እንዲቀጡ ጥያቄ መቅረብ ጀምሯል። አቶ ዮሐንስ ከስብሰባው በኋላ ሲናገሩ ተሰምተዋል በተባለው የድምጽ ቅጂ በአገር ክህደት ሊያስጠይቃቸው ይገባል የሚል ሃሳብ እየተሰጠ ነው። አቶ ዮሐንስ ቧያለው ከጥቂት ቀናት በፊት በተጠናቀቀው የአማራ ክልል ምክርቤት ስብሰባ ላይ ግማሽ ሰዓት ያህል በመውሰድ በክልሉ አሉ ያሏቸውን ችግሮች በዝርዝር ሲያስረዱ ተሰምተዋል። እንደ እርሳቸው አገላለጽና ግምገማ ክልሉ ምንም የሚጠቀስ ውጤታማ ሥራ አልሠራም። ወደፊትም አይሠራም፣ ባጭሩ ክልሉና አመራሩ ከሸፏል ነው ያሉት። በተለይ ንግግራቸው ሲጀምሩ ስብሰባው ቀጥታ ሊተላለፍ እንደሚገባና አፈጉባዔዋ ይህንን በመፍቀድ ታሪክ መሥራት … [Read more...] about የዮሐንስ ቧያለው ያለ መከሰስ መብት እንዲነሳና በአገር ክህደት እንዲከሰሱ ተጠየቀ
yohannes buwayalew
የማዳበሪያ ዕጥረት አለ በሚባልበት የአማራ ክልል 400 ኩንታል ማዳበሪያ ተያዘ
አቶ ዮሐንስ ቧያለው በክልላቸው ምክር ቤት ፊት ስለ ማዳበሪያ አቅርቦት ዕጥረት አምርረው በተናገሩና የክልሉ ገብርና ቢሮ ሥራ መሥራት ያልቻለ ደመወዝ በነጻ የሚበላ ነው ብለው ባፌዙበት ማግስት በአማራ ክልል 400 ሺህ ኩንታል ማዳበሪያ በሕገወጥ መልኩ ሲሰራጭ መያዙን ኢቢሲ ዘግቧል። በአማራ ክልል ማዳበሪያን የፖለቲካ መጠቀሚያ ለማድረግ ሲወራ የሰነበተው ሤራ ምን እንደሆነ ማሳያ ነው። የዜናው ሙሉ መረጃ ከዚህ በታች ቀርቧል። 400 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ በሕገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር በቁጥጥር ሥር ዋለ መነሻውን ከጅቡቲ ወደብ አድርጎ መዳረሻውን ወረታ ከተማ ለማድረግ የተንቀሳቀሰው 400 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ የጫነ ተሳቢ ተሽከርካሪ፤ ከታሰበው ቦታ ሳይደርስ በቁጥጥር ሥር መዋሉን የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ አስታወቀ፡፡ ሕገ ወጥ ድርጊቱ የተፈጸመው በባህርዳር ከተማ … [Read more...] about የማዳበሪያ ዕጥረት አለ በሚባልበት የአማራ ክልል 400 ኩንታል ማዳበሪያ ተያዘ