• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ዲጂታል “ወያኔ”፤ “እረኛውን ግደል፣ መንጋው ይበተናል”

July 26, 2019 08:17 am by Editor 2 Comments

አገራችን ከህወሓት አፋኝ የግፍ አገዛዝ ወጥታ በለውጥ ሒደት ውስጥ ትገኛለች። ሆኖም በአፋኙ ዘመነ ወያኔ እንኳን ሆኖ በማያውቅ መልኩ በአሁኑ ጊዜ አገራችንን እያፈረሰ የሚገኘው በማኅበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ ያለው የሃሰትና የፈጠራ ዜና ነው። ለዚህ ደግሞ በርካታ መዋዕለ ንዋይ እየፈሰሰ ቀንተሌት ተግተው የሚሠሩ “የሳይበር ወታደሮች” ተመድበዋል። እነዚህ በተለይ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በትጋት የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች ዓላማቸው መረጃ ማዛባት፤ የሃሰት መረጃ መበተን፤ የሚወጡ መረጃዎችን ማወዛገብ (ሕዝብ እውነቱንና ሐሰቱን እንዳይለይ ማድረግ)፤ ወዘተ ናቸው።

ይህ በዕዝና ቁጥጥር የሚመራ ኃይል ዋና ትኩረት የሚያደርገው በለውጡ ዙሪያ ያሉትን አመራሮች ማጠልሸት፤ የሕዝብ ድጋፋቸውን ማምከን፤ ከተቻለም ሕዝብ እንዲነሳባቸው ማድረግ ነው። ከዚህም በተጨማሪ በልዩ ልዩ ረቂቅ ስልት በሚበትኑት መረጃ ሕዝብ ከሕዝብ ጋር እንዲጋጭ፤ ደም እንዲቃባ፤ ሰላም እንዲደፈርስ፤ ሕዝብ እንዲፈናቀል፤ ሕዝብ በመሪዎቹ ላይ እምነት እንዲያጣ በማድረግ “በአመራር ላይ ያለው ኃይል አገር ማስተዳደር አቅቶታል” በሚል በአገር ውስጥና በውጪ ተዓማኒነቱን ማሳጣት ነው።

ከዚህ ዓይነቱ እኩይ ተግባር ጋር በተያያዘ ዛጎል ዜና “መንግሥትን ከህዝብ የመነጠሉ ዘመቻ የተሳካ መሆኑ ተገመገመ፤ መንግሥት በሚስጢር የያዘው ኩዴታ የዚሁ አካል ነው” በሚል አንድ ዜና አስነብቧል። ከዚህ በታች እንደሚከተለው የቀረበ ሲሆን ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ከዚህ የዲጂታል ፀረ-ኢትዮጵያ ዘመቻ ጋር በተያያዘ ምን እየሆነ እንዳለ ሰሞኑን የሚያቀርበው ዘገባ ይኖራል፤ በቀጣይም አገር ለማፍረስ የተካሄደውን የግድያ ሤራ አስመልክቶ ከዚሁ የዲጂታል የፈጠራ ወሬ ወረርሽኝ ጋር ያለውን ተዛምዶ በተመለከተ የሚያቀርበው ዘገባ ይኖረዋል።

መንግሥት ለመግልበጥ ውስጥ ውስጡን የተዘረጋው መረብ መበጠሱን የዛጎል የመረጃ ምንጮች አመለከቱ። ዕቅዱ የቆየ ቢሆንም ተግባራዊ ለማድረግ የተፈለገው የለውጡን መሪዎች ተቀባይነት ካመናመኑ በኋላ ሲሆን፣ ይህንኑ ተግባራዊ ለማድረግ የሕዝቡን ንቃተ ህሊናና ባህል ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት በከፍተኛ በጀት፣ በባለሙያዎችና በማዕከላዊ ዕዝ ደረጃ የተደራጀ የማኅበራዊ ሚዲያ ሠራዊት (ዲጂታል “ወያኔ”) ትልቁን ሚና እንደተጫወተ ታውቋል።

የመረጃው ምንጮች እንዳሉት ከፌዴራል መንግሥት ቀጥሎ ከፍተኛ ሠራዊትና የትጥቅ አቅም ያደራጀው ቡድን፣ መንግሥት አመኔታ እንዳይኖረው ባሰማራው የማኅበራዊ ሚዲያ ሠራዊት አማካይነት ውጤታማ ሥራ መሥራቱን ግምግሟል። በግምገማውም ጠቅላይ ሚ/ር ዐቢይን ለይቶ መምታት የሚለው ስትራቴጂ ግቡን መትቷል። ለዚሁም በዋናነት የዜጎች መፈናቀል፣ በተለይም በሚፈለገው መልኩ የተጠለፈው የአዲስ አበባ የባለቤትነት አጀንዳ፣ የለገጣፎ ህገወጥ ግንባታ አፈራረስና “ኦሮሞ መምራት አይችልም” የሚለው ስልት ከሚፈለገው በላይ ሰርጿል። የለውጡ መሪዎች የገነቡት የሕዝብ ድጋፍ እንዲተን ተደርጓል።

ዳግም ወደ ሥልጣን ለመምጣት እየሠራ ያለው ቡድን ሃሳቡን እውን ለማድረግ ቢነሳ የሚገዳደረው ኃይል የመከላከያ ሠራዊት ብቻ እንደሆነ ገምግሞ የመከላከያው ሠራዊት ውስጥ ሰርጎ የመግባት ሰፊ ሥራ ሰርቷል። ወዳጅ አገራትና ታማኝ የሠራዊቱ አመራሮች ሤራውን እንዳከሸፉት የገለጹት የመረጃው ሰዎች “ውጥኑ ውስን የብሔር ድርጅቶችን እንዲያካትት ተደርጎ የተሠራ ነበር” ሲሉ ገልጸዋል። የብሄር ድርጅት ያሏቸውን ግን አልዘረዘሩም።

ከመከላከያ ሠራዊት ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ሰአረ ግድያ ጋር ጉዳይ ግንኙነት ይኖረው እንደሆነ ለተጠየቁት ዝምታን የመረጡት የዛጎል ምንጮች፣ ሰሞኑንን የመከላከያ ሠራዊት ውስጥ ከፍተኛ መኮንኖች በውስጣቸው ምንም ዓይነት ችግር እንደሌለና ለሕገመንግስቱ ታማኝ ሆነው እንደሚሠሩ በተደጋጋሚ ያስታውቁት በምክንያት መሆኑንን ግን አልሸሸጉም።

የአሜሪካ የጦር መኮንኖች በሥልጠና ስም ወደ ኢትዮጵያ የገቡት ለዚሁ ዓላማ ይሁን አይሁን ምላሽ ያልሰጡት የዜናው ሰዎች፣ ሕዝብ “እረኛውን ግደል፣ መንጋው ይበተናል” የሚል መርህ ያዘለውን አገሪቱን የመበተን ሤራ በማስተዋል ቢመረምር እንደሚሻል ግን ጠቁመዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ባህር ዳር የተፈጠረውን ቀውስ ተከትሎ ድንገተኛ መግለጫ ሲሠጡ አዲስ አበባ ዙሪያ ሁሉንም ተቆጣጥረናል፤ ችግር የለም ማለታቸው ይታወሳል። እርሳቸው ዝርዝሩን ባይናገሩም የድሮው አውሮፕላን ማረፊያ በሚገኘው የደኅንነት ቢሮ አዲስ አበባ ላይ የታቀደውን ሤራ ሲያቀነባበር ተደርሶበት እጃቸውን እንዲሰጡ የተጠየቁ መታኮስ መርጠው መመታታቸውን ውስጥ አዋቂዎቹ እንደማሳያ ገልጸዋል።

ዛጎል በዚህ መልኩ ያቀረበውን ዘገባ በተለየም የጦር ኃይሎች አካባቢ ግድያና ተኩስ በተመለከተ በወቅቱ የአሶሼትድ ፕሬስ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ጦር ኃይሎች አካባቢ ሰኔ 15 ቀን ምን እንደተከሰተ በወቅቱ ያሰባሰበውን መረጃ እንደዚህ ዘግቦት ነበር።

ሰኔ 15 ቀን አመሻሽ ላይ በአማራ ክልል እንዲሁም በአዲስ አበባ ውስጥ ቦሌ አካባቢ የተከሰተው ግርግር እና ግድያ ብዙ ትኩረት ቢስብም ጦር ኃይሎች በተለምዶ ሲግናል (በድሮ አጠራሩ መኮ) የተከሰተው ሁነት ግን እስካሁን ይፋ አልሆነም።

ጋዜጠኛ ኤልያስ ቢያንስ ሶስት ምንጮች አረጋገጡልኝ እንዳለው ጦር ኃይሎች አካባቢ በነበረው ግጭት ሁለት ወይም ሶስት ሰዎች ህይወታቸው አልፏል። እስከ ሌሊቱ ስድስት ሰዓት ገደማም የጥይት ተኩስ ይሰማ ነበር። ይህ ክስተት በዕለቱ ከነበሩት ሌሎች ግድያዎች ጋር የሚያያዝ እንደሆነ ግልፅ አይደለም።

በቅርቡ ስለ ጉዳዩ ጋዜጠኛው የጠየቃቸው አንድ የመንግሥት የሥራ ኃላፊ “ስለ ጉዳዩ መረጃ የለኝም፤ አጣርቼ መልስ ልሰጥህ እሞክራለሁ” የሚል ምላሽ ሰጥተው ነበር።

በጉዳዩ ዙሪያ መረጃ አለኝ ያለ አንድ ግለሰብ ለጋዜጠኛው ተከታዩን መረጃ አቀብሎ ነበር፦ “ስለ ሰኔ 15ቱ (የጦር ኃይሎች አካባቢ ጉዳይ) የተወሰነ መረጃ አለኝ። መረጃውን ላገኝ የቻልኩት ደግሞ በዛ ምሽት ከሞቱት ሶስት የፌዴራል ኮማንዶዎች አንዱ የአክስቴ ልጅ ስለነበር ሬሳ ለመቀበል ከቤተሰብ ጋር በሄድንበት ጊዜ የአሟሟቱ ጉዳይ ስለተነገረን ነው። እናም ጉዳዩ ከጄኔራሎቹ ግድያ ጋር በተያያዘ የተጠረጠረ አንድ ኮሎኔል ለመያዝ በሄዱበት ጊዜ በተፈጠረው የተኩስ ልውውጥ ምክንያት ነው። ግን እስካሁን አንድ የመንግሥት አካል ስለ ጉዳዩ ምንም ነገር አለማለታቸው እጅግ በጣም አሳዝኖኛል” በማለት የዓይን እማኝነቱን መስጠቱን ኤልያስ ዘግቧል።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News, Politics Tagged With: digital woyane, Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. እውነቱ ይነገር says

    August 19, 2019 01:06 am at 1:06 am

    ራሳቸውን ለእለት እንጀራ ብለው በክፉ መንፈስ ተወርሰው ክፉ ሥራን በወገናቸው ላይ የሚፈጽሙ (ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ! ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም (ዮሐንስ 10፡10 እንደተባለው) ተጋላቢ ሰዎች እውነትን ለጊዜው ገለው ሊቀብሯት ይችሉ ይሆናል! አንድ ቀን ግን የሰው እጅ ሳይነካው የእውነት መቃብር ቃ! ቃ!! ቃ!!! ቁ! ቁ!! ቁ!!! ቃቁ! ቃቁ!! ቃቁ!!! በማለት የተቀበረው በድን ሳይሆን እውነት በራሷ ሕያው ሆና በመነሳት ራሷን በይፋ ትገልጣለች!!!

    ያኔ ውሸት በእውነት፣ ጥላቻ በፍቅር፣ ጦርነት በሰላም፣ ዘረኛነት በሰውነት፣ ጠባብነት በሰፊነት፣ መለያየት በአብሮነት፣ሞት በሕይወት ደህና አድርገው ይዋጣሉ!!! እስከ አሁን ድረስ የተባለውና የተሟረተው ክፉ ነገር ሁሉ በምድራችን/በሕዝባችን ላይ እንዳይሆን ሳናውቀው የከለከለልን የሰማይና የምድር ጌታ እግዚአብሔር ለዘላልም ይክበር!!! አሜን፡፡

    Reply
  2. እውነቱ ይነገር says

    August 19, 2019 05:48 am at 5:48 am

    ይድረስ ለነፍሰ ገዳዮች እና አስገዳዮች ወይም ሐገር በጥባጮች በሙሉ!!!
    (የነፈሰ ገዳዩ/የሰይጣን ምቹ ፈረሰኞችና ፈረሶች በሙሉ!)
    የማስጠንቀቂያ መልእክት አለኝ!!!

    ራሳቸሁን ለእለት እንጀራ ብላችሁ ለክፉ ሥራ/መንፈስ ተሰታችሁና ተወርሳችሁ ክፉ ሥራን በወገናችሁ ላይ የፈጸማችሁና (ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ! ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም የዮሐንስ ወንጌል 10፡10 እንደተባለው) እያስፈጸማችሁ ያላችሁ ተጋላቢና ጋላቢ ሰዎች እውነትን ለጊዜው ገላችሁ መቅበር ትችሉ ይሆናል! አንድ ቀን ግን የሰው እጅ ሳይነካው የእውነት መቃብር ቃ! ቃ!! ቃ!!! ቁ! ቁ!! ቁ!!! ቃቁ! ቃቁ!! ቃቁ!!! በማለት የተቀበረው በድን ሳይሆን እውነት በራሷ ሕያው ሆና በመነሳት ራሷን በይፋ ትገልጣለች!!! ከዚያም እናንተ ወይም ልጆቻችሁና የልጅ ልጆቻችሁ በሙሉ ትናንት በትቢትና በትምክህት ዛሬ ደግሞ በፍርሃት ከተደበቃችሁበት ዋሻ ብቅ እያላችሁ በጉልበት ከድሐው ጉሮሮ በማስለቀስ በሰበሰባችሁት የሐገር ሐብት/ገንዘብ ሆደ አምላካቸው የሆኑትን ምንደኞችን እየገዛችሁ እንደ ወረርሺኝ በምድሪቷ ላይ የዘራችሁትን ደህና አድርጋችሁ እንደምታጭዱ ቅንጣት ያህል አልጠራጠርም!!!

    ያኔ ውሸት በእውነት፣ ጥላቻ በፍቅር፣ ጦርነት በሰላም፣ ዘረኛነት በሰውነት፣ ጠባብነት በሰፊነት፣ መለያየት በአብሮነት፣ሞት በሕይወት ደህና አድርገው ይዋጣሉ!!! ብርቱ የሆነው ጨለማ ከእሱ በበራታ ብርሃን ይገለጣል! ሞትና ጮኸት፣ ዋይታና ለቅሶ አስለቃሽ በነበሩት ላይ ማንም ሳያዝዛቸው ለባለቤቱ ይመለሳሉ!!!

    እስከ አሁን ድረስ የተባለውና የተሟረተው ክፉ ነገር ሁሉ በምድራችን/በሕዝባችን ላይ እንዳይሆን ሳናውቀው የከለከለልን የሰማይና የምድር ጌታ እግዚአብሔር ለዘላልም ይክበር!!! አሜን፡፡
    እኔ እንደሆንሁ እመኑኝ ይሆናል ብለን ሳንገምት እግዚአብሔር በራሱ የጀመረውን ይህን የምድሪቷን አንድነት መንፈስ በራሱ ኃይልና ምህረት በመልካም እንደሚጨርሰው በቃሉ በኩል ተስፋ ይዤ በመታመን እጠብቀዋለሁ፡፡ ከእኔ ጋር የሚስማማ ሳይሆን በተስፋ ቃሉ የሚታመን ብቻ አሜን ይበል???

    ሰላም ሁኑልኝ
    እውነቱ ይነገር ነኝ
    እግዚአብሔር ፈቅዶ
    ከሚያኖረኝና ከምኖርበት
    ስፍራ/ሐገር በመሆን!!!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
  • “ከህወሓት፣ ከሻዕቢያ፣ ከግብፅ ሰዎች ጋር ሆኖ እንዴት የአማራን ጥያቄ ማስመለስ ይቻላል?” ኮሎኔል ፈንታው January 25, 2026 04:23 am
  • የኢትዮጵያ አየር ኃይል: ለአፍሪካ ሀገራት የመጀመሪያዎቹን የአየር ኃይል አብራሪዎች ያሰለጠነ ተቋም January 25, 2026 03:50 am
  • የአማረ ሪፖርተር እያደረሰ ያለው የብሔራዊ ደኅንነት አደጋ January 22, 2026 01:56 am
  • የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የማርያምን ማዕረግ ዝቅ አደረገች December 12, 2025 09:27 pm
  • ኢህአፓ: ከነጭ ሽብር ወደ “አዲስ አበባ ትናገር” የጎዳና ሽብር? December 12, 2025 09:11 pm
  • EOC Bans Haile Gebrselassie Over Are­qie Comments Linked to Doping November 21, 2025 07:47 pm
  • በሥራ ማቆም አድማ ጥሪ ዘርፍ ባለሙያው ጃዋር ሌላ ጥሪ አቀረበ November 17, 2025 09:25 am
  • የ-አብሮነት ማኅበር የመረጠው ሕቡዕ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይፋ ሆነ November 5, 2025 12:06 pm
  • “የኢሳያስ አፈወርቂ ውድቀት አይቀሬ ነው … “ፅምዶ” ራዕይ ዓልባ” ነው – ሼትል ትሮንቮል October 26, 2025 10:15 pm
  • አሜሪካ ስላልተቀበለችው ነው “የሽሽግር መንግሥት” ስብሰባው በአምስተርዳም ተካሄደው October 25, 2025 11:09 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule