• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የኢቲቪ ባለሥልጣናት ኦሊምፒክና አትሌቲክስ ላይ ያነጣጠረ ፕሮፓጋንዳ እንዲሠራ አዘዙ

August 25, 2024 01:48 am by Editor 1 Comment

የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ባለሥልጣናት በኦሊምፒክና በአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ላይ ትኩረት ያደረገ የፕሮፓጋንዳ ሥራ እንዲሠራ መመሪያ መስጠታቸው ተሰማ። መመሪያው ተግባራዊ መሆኑን ተከትሎ ኢቲቪ የሚያቀርበው ዘገባ የሕግ ጥያቄ ማስደገፊያ እንዲሆን ተደርጎ ለመረጃነት እየተዘጋጀ መሆኑ ከሌሎች ወገኖች ተደምጧል።

ከፓሪሱ ኦሊምፒክ መጀመር ቀደም ብሎ በማኅበራዊ ሚዲያው የተጀመረው ዘመቻ ሁለት ቡድኖች ጎራ ለይተው ውዝግብ መጀመራቸውን አመላካች እንደነበር ይታወሳል።

ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴና አትሌት ገዛኸኝ አበራ ጎራ ለይተውና ተመሳሳይ አቋም ይዘው የለኮሱት ተቃውሞ ውድድሩ ከመጀመሩ ቀናት በፊት ሲሆን፣ ማኅበራዊ ሚዲያው ተቃውሟቸውን ለመግዛትና ለማሰራጨት ጊዜ አልወሰደም። ከወራት በፊት በተጠናቀቀ ምርጫ ላይ ቅሬታ በማንሳት የተጀመረው ክስ ውድድሩ ከተጀመረ በኋላም ከፓሪስ በሚወጡ ዐውዳቸውን በሳቱ መረጃዎች ታጅቦ ማኅበራዊ ሚዲያውን ናጠው። በተለይ ስፖርት ነክ መረጃ በማውጣት የሚታወቁት የሰበር ዜና አብሳሪና በየዕለቱ በአጀንዳ መልክ የሚወጣ መረጃ ፋና ወጊ ሆነው ዘመቻውን ሲመሩ ተስተውሏል።

በእነ ኃይሌ በኩል ያለው ኃይል ቀድሞ የተደራጀና ያሰበበት በሚመስል መልኩ በተከታታይ የሚወጡ መረጃዎች ሕዝብን አስቆጡ። ውጤቱ በተባለው መሠረት መበላሸቱ ታክሎበት ማኅበራዊ ሚዲያው ጉዳዩን አጦዘው። “ማመዛዘን፣ ማመጣጠን፣ ማጣራት፣ ወዘተ” የሚባሉት የጋዜጠኛነት መሠረታዊ መርሆች ተናዱ። መረጃ ያካፈሉን ወገኖች እንደሚሉት ለወትሮውም በቅጡ የማይተገበርና ሙያን ያላከበረ አሠራር ከድጡ ወደማጡ ወርዶ አፈር በላ።

ዜናውን ያካፈሉት ወገኖች ከላይ በጠቀሷቸው ምክንያቶችና ለጊዜው ይፋ ባላደረጓቸው ጉዳዮች ማኅበራዊ ሚዲያው በትንሽ ቅንጫቢ እውነት ታጅቦ በተከታታይ ሲሰራጭለት የነበረውን አጀንዳ እያናፈሰ ማስተጋባቱ የፈጠረው ጫና የኋላ ኋላ የኢቲቪ ኃላፊዎችን እጅ ጠመዘዘ።

“ችግር የለም፣ ተዳፍኖ ይቆይ ለማለት ሳይሆን የኢቲቪ ባለሥልጣኖች የሰጡት መመሪያ መንግሥትን በማኅበራዊ ሚዲያ ጫና እየበረገገ መርኽ የሚጥስ እንዳያስመስለውና፣ ይህ ክፉ ልማድ እንዳይደጋገም ሥጋት ስላለን ነው” የሚሉት እነዚህ ወገኖች እንዲህ ያለው አሠራር ባስቸኳይ ጥብቅ እርማት ሊደረግ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

ራሳቸውን በማኅበራዊ ሚዲያ አውታሮች ያደራጁና “አክቲቪስት“ ብለው የመደቡ በመናበብ ያደረሱትን ጉዳት የሚያስታውሱት ክፍሎች፣ በአብዛኞቹ በሚባል ደረጃ ከሚዲያ አሠራር መርኽ ውጭ አፈንግጠው ለአገራችን ሰላም መደፍረስ፣ ለእርስ በእርስ ዕልቂት፣ መፈናቀልና ውድመት ዛሬም ድረስ እንደቀጠለ ገልጸው “መንግሥትም ሆነ ባለሥልጣናቱ የማኅበራዊ ሚዲያ ፊት አውራሪዎችን ስድብና የደቦ ዘመቻ በመፍራት የሚወስኑት ውሳኔ እያደር አገሪቱን በደቦ ፍርደኞች እጅ እንዳይጥላት እንሰጋለን” በሚል አስጠንቅቀዋል።

የጎልጉል መረጃ አቅራቢዎች እንዳሉት የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ኃላፊዎች ለስፖርት አዘጋጆች ግልጽ መመሪያ መስጠታቸውን ተንተርሶ ሚዛናዊና የተመጣጠነ መረጃ ማቅረብ አልተቻለም። ይህንኑ ተከትሎም በመንግሥት የኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያዎች ሳይቀር የሚግለበለበው የኦሊምፒክና አትሌቲክስ ጉዳይ “ሥልጣን ልቀቁ” ከሚለው ውጪ በሽታውን የሚያድን ሆኖ አልታየም።

ኢቲቪ የአገሪቱ ብሔራዊ ሚዲያ እንደመሆኑ ጥንቃቄ ወስዶ፣ አመጣጥኖና በሚቻል መጠን ሙያው የሚጠይቀውን ሁሉ በማድረግ ለሕዝብ፣ ለዕውነት የቀረበ መረጃ ማቅረብ እንደሚገባው ጠቅሰው ዜናውን ያቀበሉን እነዚሁ ለድርጅቱ ቦርድ ቅርብ የሆኑ እንዳሉት፣ ውሳኔው ሊጤን ይገባዋል፤ አደገኛም ነው።

“መንግሥት በማኅበራዊ ሚዲያ ማዕበል ውስጥ በሚገርም ሁኔታ እየተንሳፈፈ ነው። አክቲቪስት ነን የሚሉና ጫና ፈጣሪ አድርገው ለራሳቸው ማዕረግ በሰጡ አካላት የደቦ ጩኸት ሲነዳ እየታየ ነው“ የሚሉት ወገኖች፣ ዜናውን ሲሰሙ መደናገጣቸውንና ማስተካከያ እንዲደረግ በአቀራቢያቸው ላሉ ማሳሰባቸውን አመልክተዋል።

የነጻ የፕሬስ መብት በኢትዮጵያ አጠቃቀሙን ባልተረዱና፣ መረዳት ባልቻሉ ክፍሎች ለአደጋ ሲጋብዝ በተለያዩ ጊዜያት መታየቱን፣ ይህም አዝማሚያ ማደጉን፣ ለበርካታ ተዋንያኖቹ ደግሞ ወቅት እያፈራረቁ ቡድን በመፍጠርና በመለየት ኪሳቸውን የሚያደልቡበት የንግድ መስክ መሆኑን ማስረጃ ጠቅሰው መረጃውን ያደረሱት ተናግረዋል።

የጎልጉል የአዲስ አበባ ተባባሪ የፓሪሱን ኦሊምፒክ ተከትሎ ሕዝብ የጠራ መረጃ እንዳላገኘ አስታውቋል። በሥፍራው የነበሩ ታዛቢዎችን አነጋግሮ እንደተረዳው ታዛቢዎቹ አደባባይ ወጥተው ለመናገር አይደፍሩም። ምክንያታቸው ደግሞ “በፍረጃና በደቦ ፍርድ ውግዘት ይደርስብናል፣ እኛ የማንም ደጋፊ ባንሆንም ነገሩ በዓላማ ዕቅድ ተይዞለት እየተሠራ ያለ በመሆኑ እየተስተጋባ ያለውን በጭፍን ከመደገፍ ውጪ ሌላ ምንም ዓይነት እውነተኛ መረጃ ማቅረብ አይቻልም፤ ማስፈራሪያም አለ” የሚል ነው።

የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የስፖርት አዘጋጆችም ሁሉንም እውነት እንደሚያውቁ፣ በቂ መረጃም እንዳላቸው የሚገልጹት እነዚሁ ወገኖች ክስ አላቸው። “ኢቲቪ ውስጥ ያሉት የስፖርት ክፍለ ጊዜ አዘጋጆች ሐቁን በደንብ ያውቁታል። በቂ መረጃ አላቸው። ያሻቸውን መረጃ ለማሰባሰብ የተመቻቸላቸው ናቸው። ግን አያደርጉትም። ለዚህም ዋናው ምክንያት ከሁለቱ በአንዱ ቡድን ተጠልፈዋል። ወይም የተነሳው የማኅበራዊ ሚዲያ ማዕበል አስምጧቸዋል። ወይም ጀርባቸው የጸዳ ባለመሆኑ ደመራው ወደ አጋደለበት ዘመዋል። ወይም የበላን ያብላላል እንዲሉ ሆነዋል” ሲሉ ይከሷቸዋል።

በዚሁ መነሻ ኢቲቪ ውስጥ የአለቆቻቸው ውሳኔ ዕድል የሆነላቸው፣ ውሳኔው ያሸማቀቃቸው፣ አወዳደቃቸውን ለማሳመር የሚፋለሙ፣ የተሸማቀቁና ቸልተኛነትን እንዲመርጡ ወይም እዚያና እዚህ እንዲጫወቱ የተገደዱ አሉ። ለአንድ ወገን ባደሉና በዚሁ አቋማቸው ለሚከፈላቸው ሰፊ ዕድል እንደፈጠረ የተነገረለት ይህ የአለቆች መመሪያ በአንድ አገር ብሔራዊ ቴሌቪዥን ሊቀርቡ የማይገባቸው የፍረጃ፣ ክብረ ነክ፣ የቡድን ስያሜና የማጠልሻ ንግግሮች እንዲሰሙ ዕድል ከፍቷል። ጎልጉል እንደሰማው ከሆነ በብሔራዊ ቴሌቪዥን የሚቀርቡት ለችግሩ መፍትሔ የማይሰጡ ዘለፋዎች ወደ ሕግ የሚያመሩበት አግባብም እየተመቻቸ ነው።

የማኅበራዊ ሚዲያው ማዕበል ባሰመጣቸው የኢቲቪ ባለሥልጣናት ቀጭን መመሪያ ሳቢያ ሕዝብ በተባራሪ መረጃ እንዲሰክር ስለተፈረደበት ማንም ከሚፈልገው ውጪ ሌላ ምንም ነገር መስማት አይፈልግም። ከምንም በላይ የአገሪቱ ትልቅ ሚዲያ ስፖርቱ ከገባበት ቅርቃር ሊያወጣው የማይችል የቡድን ውዝግብ ማራገቢያ እንዳደረገው የሚናገሩት ወገኖች፣ “ቢልልን ኖሮ” ሲሉ ምኞታቸውን ከኃፍረታቸው ጋር ቀላቅለው ይናገራሉ።

“ቢልልንማ” ይሉና የተለያዩ አገራትን የምርመራ ጋዜጠኞች ጀግንነት የተሞላው ሪፖርት አስታውሰው ከምኞት ዓለም ይመስለሱና “ቢልልንማ ኢቲቪ በየጓዳው የያዘውን፣ እጁ ላይ ያለውን፣ ከፈለገበት ቦታ መረጃ የማግኘት ዕድሉን ተጠቅሞ፣ በየሥርቻው የሚጮሁትንና የሚያስጮሁትን አንድ ላይ ሰብስቦ ወይም በግል አድምቶ ቢመረምር የጠራ መረጃ ይሰጠን ነበር” ይላሉ። አያይዘውም “አለቆቻቸው ሊወቅሷቸውና ሊገሯቸው ሲገባ በተቃራኒው መረን ውጡ ብለው መመሪያ በመስጠት የአገሪቱን ብሔራዊ ሚዲያ ባኮረፉ፣ ቂም በያዙ፣ ሥልጣን በሚፈልጉ፣ ወዘተ አካላትና በማኅበራዊ ሚዲያ አወራራጆች እጅ እንዲወድቅ አደረጉት። ይህ ብሔራዊ ኃፍረት ነው። ጆሮ ያላቸው ይስሙ” ሲሉ የማስጠንቀቂያ መልዕክት አሰምተዋል።

ፓሪስ ሚኒሊክ ሬስቶራንት ሲመገቡ የነበሩ ሳሙኤል ኃይሉ የሚባሉ ዕማኝ “ አፍሬያለሁ” ሲሉ በላኩት አጭር መልዕክት “ውድድሩ ከመጀመሩ በፊት የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ቡድን ልዑካኖች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደኤታና ሌሎች ባለሥልጣናት ባሉበት ወደ ሚኒሊክ ሬስቶራንት ሲገቡ እዚያው ነበርኩ። ባንድ ተዘጋጅቶ ስለነበር ጉሮ ወሸባዬ ሲባል ተነስቼ አጨብጭቤያለሁ። አለ ገና ተብሎ ተዘፍኗል። ምን ያህል እንደተከፈለ፣ ምን ውል እንዳለ አላውቅም እንጂ አቀባበሉ ደስ የሚልና ስሜት የሚስብ ነበር። ለሜቻ መሰናክል ከወደቀ በኋላ ይህ ቪዲዮ እየተቆራረጠ ፍጹም ውሸት ተቀብቶ በሚዲያ ሲተላለፍ አየሁ። ምንም ውድድር ሳይካሄድ የተቀዳ ቪዲዮ ኢትዮጵያ ላይ በደረሰ ሽንፈት ተደስተው ጨፈሩ የሚለውን በዚህ እኔ በነበርኩበትና በዓይኔ ባየሁት ቪዲዮ ታጅቦ ሲቀርብ አየሁ፤ ሰማሁ። ትልቅ ውሸት ነው፤ ይህን እውነት ለመመስከር ያህል ነው” ሲሉ እማኝነታቸውን ሰጥተዋል።

እሳቸው እንዳሉት መቼ፣ እንዴት፣ የት፣ ለምንና በምን መልኩ እንተቀረጸ በይፋ ያልተገለጸ በሬስቶራንት ውስጥ የተቀረጸ የቪዲዮ ፊልም የአትሌቲክስና የኦሊምፒክ አመራሮችና አትሌቶች በከፊል እንዲታዩ ተደርጎ፣ ፊልሙ ከውድድር በኋላ በደረሰው ሽንፈት ደስታ መነሻነት የተከናወነ ፌሽታ እንደሆነ ተደርጎ መሰራጨቱን ዝግጅት ክፍላችን አይቷል።

የሆቴሉ ሥራ መሪ አቶ ኤርሚያስን ዝርዝሩን ባይገልጹም በሰሙትና ባዩት ማዘናቸውን አመልክተዋል። የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጋዜጠኞች ፊልሙ እያላቸው እውነቱን ለሕዝብ ለምን እንዳላስረዱ ግልጽ እንዳልሆነላቸው ተናግረዋል።

ይህ ብቻ አይደለም በስፍራው የነበሩ “ጋዜጠኞች” በስማ በለው የሚቀርቡ መረጃዎችን አግባብ ካለው አካል ጠይቀው የማቅረብ ኃላፊነታቸውን ትተው በፓሪስ ጎዳና ሲንቀዋለሉ ቆይተዋል ወይም የተነሳው የደቦ ማዕበል ሰለባ እንደሆኑ ገምተዋል።

በአትሌቲክስም ሆነ በኦሊምፒክ ውስጥ ቀደም ሲል ጀምሮ በርካታ ችግሮች ነበሩ። እንደዚህ እንደዛሬ እንደ ማኅበራዊ ሚዲያ ዓይነት የደቦ ጩኸት ማሰራጪያው ዐውድ ክፍት ሳይሆን የአሠራር ክፍተት ብቻ ሳይሆን አሳፋሪ ወንጀሎችም ጭምር ይፈጸሙ ነበር። በማን አለብኝነት ካድሬዎችና ባለ ጊዜዎች ስፖርቱ ውስጥ ገብተው ሲፈተፍቱ መኖራቸው እያደር ስፖርቱን እንደበላው በተለይ ስፖርቱ አካባቢ ቅርብ የነበሩና በስፖርቱ ውስጥ ያለፉ በደንብ ያውቁታል።

ዛሬ ድረስ የዘለቀውና የለመድነውን የሩጫ ድል ቀብር እያፋጠነ ያለው ችግር እንዲቀረፍ፣ ስፖርቱን ጠቅጥቆ የያዘው የድንቁርና በሽታና ጥቅም ላይ የተመሠረተ አድሏዊ አሠራር እንዲሻሻል የሚፈልጉ አካላት ያለምንም የደቦ ጩኸት፣ ያለ አንዳች ውሸትና ግነት ሃቁን ብቻ ይዘው መታገል ቢችሉ ውጤታማ ሊሆኑ እንደሚችሉ ታዛቢዎች ይገልጻሉ። በተለይም ኮታና ብሄር ተኮር የሆነው የአገሪቱ የፖለቲካ ስሪት፣ የስፖርቱን አደረጃጀት ማንም ብሄሩ ውስጥ ተወሽቆ ያለ ዕውቀት እንዲያጨማልቀው አድርጎታል። አጥፊ እንዳይቀጣ፣ ዐቅም አልባ እንዳይሰናበት አንቆ የያዘው አደረጃጀትና ጎሳ ላይ የተተከለ የስፖርት ፖሊሲ እስካልተቀየረ ድረስ ምንም ለውጥ እንደማይመጣ፣ በኮታ የመጡትን አባርሮ በኮታ ሌሎችን ማግበስበስ ትርፉ አሁንም ውድቀት በመሆኑ ኢቲቪና አመራሮቹ በማኅበራዊ ሚዲያ አጀንዳ ውስጥ ከመንቦጫረቅ እዚህ ላይ እንዲያተኩሩ ዜናውን የላኩልን ገልጸዋል።

“ኢቲቪ የበቃ የሰነድና የምስል መረጃ እጁ ላይ ይዞ ሃቅ ላይ በመመርኮዝ በዶክመንታሪ መልኩ በተደጋጋሚ ሐቁን ማፍረጥረጥ እየቻለ የቡድንና የግለሰብ ፍላጎትን ለማርካት ተደራጅተው በማኅበራዊ ሚዲያ የደቦ ጩኸት በሚያሰሙ አካላት አጀንዳ ውስጥ እንዲንቦጫረቅ መመሪያ መሰጠቱ ችግሩን ያብስ እንደሆነ እንጂ አያቀለውም። ፍርደ ገምድልነት የተጣባቸውን ሪፖርተሮች ኪስ ማደለቢያ ምቹ ሁኔታ ከመፈጥር በዘለለ ውጤት አልባ ነው። እንኳን ውጤት ሊያመጣ እያደር እያሽቆለቆለ ለመጣው ስፖርቱ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ይሆንበታል” በማለት ዜናውን ከማሳሰቢያ ጋር ያካፈሉን ተናግረዋል።

ኦሊምፒክን በሚያክል ታላቅ ውድድር ኢትዮጵያን ወክለው ለመወዳደር ወደ ፓሪስ ያቀኑ አትሌቶች ገና ሩጫ ሳይጀምሩ ሽባ ያደረጋቸው የማኅበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ያሳደረውን ጫና ራሳቸው አትሌቶቹ ሲበርድ የሚገልጹት የታሪካችን አንዱ ጠባሳ እንደሚሆን የጎልጉል ዘጋቢ ከአዲስ አበባ ሰማሁ ሲል አስታውቋል።

በችግርና በተበላሸ አሠራር የነቀዘውን የአገሪቱን ስፖርት ለመቀየር ኦሊምፒክ እስኪጀመር አድፍጦ መቆየት በየትኛውም መሥፈርት ትክክል አይሆንም።

የአዲስ አበባ ዘጋቢያችን ከስሜት ራቅ ብለው አስተያየት የሚሰጡ ነባር አትሌቶችን መካከል “አገር ወክለው የሚወዳደሩ ስፖርተኞች ላይ በዚህ ደረጃ እንደ ባዕድ ቆጥሮ የቀጠቀጠ፣ ስሜት ያበላሸ አገርም ሆነ ሚዲያ የለም” ያሉ አጋጥመውታል።

ከአትሌቶች መካከል ሰለባ የነበረ መሆኑን አስታውሶ “እንኳንም የፓሪሱ አትሌቲክስ ቡድን አባል አላደረገኝ” በማለት ሃዘኑን ገልጿል። “ስንሰማ ውድ ድር ሥፍራ ደረስ ኬዲስ አበባ ይደወላል። ሚዲያ ላይ ወጥታችሁ ይህን በሉ የሚባሉ አትሌቶች ነበሩ። እንቅልፍ መተኛት ያቃታቸው አትሌቶች ነበሩ። ሕዝብ ይህን አይረዳም። ችግሩን የሚያውቀው አትሌቱ ብቻ ነው። እንዴት ነው በዚህ ደረጃ ጫና የሚደርስበት አትሌት የሚያሸንፈው?” ሲል ይኸው አትሌት ይጠይቃል። አያይዞም “ኦሊምፒክ እስኪያልቅ መጠበቅ አይቻልም ነበር” ሲል የተመረጠውን ጊዜና ጊዜውን መርጠው በውጤቱ ላይ አሉታዊ ጫና ካሳደሩ በኋላ የራሳቸውን ፍላጎት ወደፊት አምጥተው ሥልጣን የጠየቁትን ባልደረቦቻቸውን በማየታቸው መገረሙን ገልጿል።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News, Right Column, Social Tagged With: Ashebir Woldegiorgis, Derartu TUlu, ethiopian athletics federation, Gezahegn Abera, Haile Gebreselassie, Los Angeles 2028, paris 2024

Reader Interactions

Comments

  1. Segel says

    August 26, 2024 02:38 am at 2:38 am

    አድር ባይ ሆናችኋል። ጎልጉል በወያኔ ዘመን ከሚከታተሉት ውስ አውራው ነበርኩ unsubscribe ካደረግኋችሁ በኋላ ለምን እና እንዴት እንደመጣችሁ ሳላውቅ ተከሰታችሁ። I’m done with golgul.

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • Rusted screws, metal spikes and plastic rubbish: the horrific sexual violence used against Tigray’s women July 4, 2025 01:48 am
  • በሞርሞን ቤ/ክ ዕርዳታ የኪዳነምህረት ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ማምለኪያ ሥፍራ አገኘች July 2, 2025 01:28 pm
  • የበረከት ስምዖን “አየር ላይ ትዕይንት” አየር ላይ ተበተነ July 2, 2025 01:24 am
  • “ዐቢይ ይውረድ፣ እኛ እንውጣ፣ በተራችን እንግዛ” ስልቴዎች (ስብሃት፣ ልደቱ፤ ቴዎድሮስ) June 11, 2025 01:56 am
  • ኤሊያስ መሠረት የሚሠራው ለማነው? ለብጽልግና? ወይስ …? June 3, 2025 01:27 am
  • በግንቦት 20 – የሁለት መሪዎች ወግ May 28, 2025 02:01 am
  • በፈቃዳቸው የተመለመሉ ወጣቶች ሁርሶ ሥልጠና ጀመሩ May 22, 2025 09:11 am
  • ድብቁ ሤራ ሲጋለጥ – “ሦስትን ወደ አራት” May 21, 2025 01:01 am
  • ከትግራይ ሾልኮ የወጣው ምሥጢራዊው ሰነድ ምንድነው? May 20, 2025 09:18 am
  • በደቡብ ጎንደር በጸዳሉ ደሴ የተመሩት 72 ታጣቂዎች እጃቸውን ሰጡ May 19, 2025 02:24 pm
  • የተመሠረተው የፋኖ አደረጃጀት ዋነኛ ዓላማው ድርድር መሆኑ ተነገረ May 14, 2025 11:07 pm
  • ከፍተኛ የፋኖ አመራሮች መገደላቸው ተነገረ May 6, 2025 10:40 pm
  • ሃይማኖትን ለተራ የፖለቲካ ሸቀጥ ማዋል ውርደት ነው April 24, 2025 12:43 am
  •  የኬሪያ ኢብራሒም ኑዛዜ “ብትንትናችን ወጥቷል” April 22, 2025 12:08 am
  • ለወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አመራሮች ወታደራዊ ሥልጠና ተሰጠ April 16, 2025 11:44 pm
  • ዓቅም እንደሌለው የገመገመው ሻዕቢያ ፊቱን ከጦርነት ወደ ዲፕሎማሲ እያዞረ ነው   April 15, 2025 12:32 am
  • “አንድ የፋኖ ተቋም (የእስክንድር) ተመሥርቷል፤ ሌሎቹ ደግሞ እንዲሁ አንድ ተቋም መሥርተው ወደዚህ ይመጡ” አበበ ጢሞ April 11, 2025 12:07 am
  • መለስ (ለገሰ) ዜናዊ – ተዋርዶ ያዋረደን! April 9, 2025 10:28 pm
  • የተከዜ ዘብ: የሉዓላዊነት መጠበቂያ April 8, 2025 11:49 pm
  • አዲስ አበባ አስተዳደር የሪፖርተርን የተዛባ መረጃ ኮነነ፤ ሕጋዊ እርምጃ እወስዳለሁ አለ April 8, 2025 10:06 pm
  • ሀሰተኛውን የሪፖርተር ዘገባ ንግድ ባንክ በጽኑ ተቃወመ፤ እርማትም ጠየቀ April 8, 2025 09:48 pm
  • “ኦሮሚያ ላይ ወይም ሌላ ቦታ ላይ ስታደርገው ከነበረ ትግራይ ወስጥም የማታደርግበት ምንም ምክንያት አይኖርህም” ነው ጌታቸው ረዳ April 7, 2025 10:22 pm
  • “TPLF’s belief in a strong federal government was always tied to its own dominance in Addis Ababa” April 7, 2025 10:15 pm
  • Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation March 31, 2025 02:36 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2025 · Goolgule