በ2014 የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን ከ50 በመቶ በላይ ያመጡት ተፈታኞች 3.3 በመቶ ብቻ መሆናቸውን የትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ፡፡ የ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ሪፖርት እና ዋና ዋና ግኝቶች ዙሪያ መግለጫ የሰጡት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ የዘንድሮው የ12 ከፍል ፈተና ውጤት አስደንጋጭ እንደሆነ እንረዳለን ብለዋል። በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ለፈተና የተመዘገቡ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በጠቅላላ 985ሺ 354 ተማሪዎች እንደነበሩ በመግለጫው ተጠቅሷል፡፡ ከዚህ ውስጥም ለፈተና የቀረቡት ተማሪዎች 908ሺ ሺህ 256 (92.2%) ሲሆኑ 77ሺህ 98 ተማሪዎች ፈተና አልወሰዱም ተብሏል። በትምህርት ዘርፍ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ከማህበራዊ ሳይንስ በተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ ሲሆን የተፈጥሮ ሳይንስ 31.63 ከመቶ … [Read more...] about “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው
ministry of education
የትምህርት ሚኒስቴር እና ኢንሳ በጋራ ለመስራት መከሩ
ፈተና መስረቅ መላ ሊበጅለት ይሆን? የትምህርት ሚኒስቴር እና ኢመደኤ የሳይበር ደህንነትን ለማስጠበቅ በሚያስችሉ የምርምር፣ ልማት እና ስልጠናዎች ላይ በጋራ መስራት መከሩ። የትምህርትሚኒስቴር እና የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲን (ኢመደኤ) የሳይበር ደህንነትን ለማስጠበቅ በሚያስችሉ የምርምር፣ ልማት እና ስልጠናዎች ላይ በጋራ መስራት በሚያስችላቸዉ ጉዳይ ላይ መምከራቸው ተገለፀ። የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲን (ኢመደኤ) ጎብኝተዋል። በጉብኝታቸው ወቅት የኤጀንሲውን የሳይበር ተሰጥዎ ልማት ማዕከልን፣ በኤጀንሲዉ ለምተዉ በዲጂታል ኤግዚብሽን ማዕከል የቀረቡ ምርት እና አገልግሎትን እንዲሁም የኢመደኤ ሠራተኞችና የኃላፊዎችን ቢሮዎች ተዘዋውረው ጎብኝተዋል። ከጉብኝቱ ጎን ለጎን ሚኒስትሩ ከኢመደኤ ከፍተኛ … [Read more...] about የትምህርት ሚኒስቴር እና ኢንሳ በጋራ ለመስራት መከሩ
በሁሉም ክልል 50 የልህቀት ት/ቤቶች ይገነባሉ፤ ለወደሙትም 1.6 ቢሊዮን ብር ተበጅቷል
በሁሉም ክልሎች በችሎታቸው የተመረጡ ተማሪዎች የሚማሩባቸው 50 ትምህርት ቤቶች ሊገነቡ መሆናቸውን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በሁሉም ክልሎች በዓይነታቸው ልዩ የሆኑና የልህቀት ማዕከል የሚሆኑ 50 ትምህርት ቤቶች ይገነባሉ ብለዋል። ትምህርት ቤቶቹ ቀጣይ የአገር መሪ የሚሆኑ ብቁና ተወዳዳሪ ተማሪዎች የሚፈልቁበት በችሎታቸው ብቻ የሚመረጡ ተማሪዎች የሚማሩባቸው መሆናቸውንም ተናግረዋል። በትምህርት ቤቶቹ የ8ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት መሠረት ባደረገና የትምህርት ሚኒስቴር በሚያወጣውን መመዘኛ የሚያሟሉ ተማሪዎች የሚማሩባቸው እንደሆኑም ተገልጿል። በሁሉም ክልሎች በሚገነቡት እነዚህ የልህቀት ማዕከላት ከሁሉም የአገሪቱ ክልሎች የሚመለመሉ ተማሪዎችን ተቀብለው የሚያስተምሩ ናቸው። በተያያዘ ዜና የትምህርት ሚኒስቴር … [Read more...] about በሁሉም ክልል 50 የልህቀት ት/ቤቶች ይገነባሉ፤ ለወደሙትም 1.6 ቢሊዮን ብር ተበጅቷል