የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ለፓርላማ በሰጡት ማብራሪያ፤ የተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ በአግባቡ እንደሚሰራበት አመልክተዋል።
“በምንም አይነትና መስፈርት አግባብ የሌለውና አድሎ ላይ የተመሰረተ ምደባ አይኖርም” ሲሉ ተናግረዋል።
“እያንዳንዱ ተማሪ በጠየቀው በችሎታው፣ በሚገባው ቦታ እንዲመደብ እናደርጋል” ያሉት ሚኒስትሩ “አንድና ብቸኛው ከዛ የምንወጣበት አስቸኳይ የሆነና ቅርብ የሆነ ክትትል የሚያስፈልጋቸው የህክምና ጉዳይ ሲኖር ነው” ብለዋል።
“የህክምና ኬዞችንም ስንመለከት ከዶክተር ወረቀት ማምጣት ብቻ ሳይሆን በቦርድ ደረጃ ተነጋግረውበት ያ የህክምና ጉዳይ ሌላ ቦታ ሄዶ ለመማር የማያስችል ነው፤ ለህይወቱ/ቷ አስቸጋሪ ነገር ያመጣል ከተባለ ብቻና ብቻ ነው” ሲሉ አስገንዝበዋል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ፤ “ለአንድ የመንግሥት ባለስልጣን ፣ አንድ የምክር ቤት አባል፣ አንድ ዝም ብሎ ሃብታም ነኝ ብሎ ለሚያስብ ሰው ከሚገባው ውጭ ለልጁ የሚሰጥ ምንም ነገር የለም” ብለዋል።
ከምደባ ጋር በተያያዘ አንዳንድ ጥያቄዎች እየተጠየቁ መሆኑን ያልደበቁት ፕ/ር ብርሃኑ “ስልኮች ይደወላሉ ነገር ግን የምንሰጠው መልስ አንድ ነው ፤ ‘ሁሉም ኢትዮጵያዊ ትምህርት ቤት እኩል ነው። በችሎታው ነው እንጂ የሚመዘነው ከዛ ውጭ ባለ ሌላ መስፈርት ማንንም እድል አንሰጥም’ የሚል ነው” ብለዋል።
“ከዚህ ውጭ የተሰራና የሚሰራ ስራ ካለ አሳዩን፤ ንገሩን እናስተካክላለን” ሲሉ ተናግረዋል።
ፕ/ር ብርሃኑ ለምደባ በሚል ጉዳይ እሳቸውም ጋር የሚመጡ እንዳሉ ገልጸው “ለሁሉም የምለው አትሞክሩ፣ ባትደውሉ ነው የሚሻለው embarrassing ይሆናል ፤ ትክክለኛ ጥያቄ አለን ካላችሁ በትክክለኛው ሂደት እለፉ ከዛ ውጭ ግን የሚመጣ የአቋራጭ መንገድ የለም” ሲሉ ተናግረዋል። (tikvahethiopia)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Benjamin says
Ethiopians educational cariculum is down to the bortom nivo and have to be inquestion mark as well as the minster too! I sujust he has to resign immidietly with out any hisitation in my opinion! Sorrey to say that but we can’t denay the reality on the ground that’s oviously we can se clearly either it’s supposed to be vanish the entir generation to come!