• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው 

January 27, 2023 09:11 am by Editor 1 Comment

በ2014 የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን ከ50 በመቶ በላይ ያመጡት ተፈታኞች 3.3 በመቶ ብቻ መሆናቸውን የትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ፡፡

የ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ሪፖርት እና ዋና ዋና ግኝቶች ዙሪያ መግለጫ የሰጡት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ የዘንድሮው የ12 ከፍል ፈተና ውጤት አስደንጋጭ እንደሆነ እንረዳለን ብለዋል።

በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ለፈተና የተመዘገቡ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በጠቅላላ 985ሺ 354 ተማሪዎች እንደነበሩ በመግለጫው ተጠቅሷል፡፡

ከዚህ ውስጥም ለፈተና የቀረቡት ተማሪዎች 908ሺ ሺህ 256 (92.2%) ሲሆኑ 77ሺህ 98 ተማሪዎች ፈተና አልወሰዱም ተብሏል።

በትምህርት ዘርፍ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ከማህበራዊ ሳይንስ በተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ ሲሆን የተፈጥሮ ሳይንስ 31.63 ከመቶ እንዲሁም የማህበራዊ ሳይንስ 27.79 ከመቶ በአማካኝ አስመዝግበዋል ተብሏል።

የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት አስደንጋጭ ቢሆንም፤ ነገ የተሻለ ትውልድ ለመፍጠር በዚህ ውስጥ ማለፍ ግድ ይላል – ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

በ2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ሪፖርት እና ዋና ዋና ግኝቶች ዙሪያ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ መግለጫ ሰጥተዋል።

ከዚህ በፊት የነበረው የትምህርት እና ምዘና ስርዓት በርካታ ብልሹ አሰራሮች እንደነበሩበት ያነሱት ሚንስትሩ፤ የአሁኑ የፈተና ስርዓት ይህን ብልሹ አሰራር ለማረም የተወሰደ የመጀመሪያ እርምጃ ነው ብለዋል።

የፈተናው አሰጣጥ በብዙ ፈተናዎች ውስጥ ያለፈ እንደሆነ አንስተው፤ በስኬት ለመጠናቀቁ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

ፈተናው ሙሉ ለሙሉ ከስሮቆት የፀዳ እንደነበረም ተነስቷል።

በጠቅላላ የተመዘገቡት ተፈታኞች ቁጥር 985,354 ሲሆኑ፤ ከነዚህ ውስጥ 92 ከመቶ የሚሆኑት ፈተናውን ወስደዋል።

20,170 ተማሪዎች በፈተናው ከተገኙ በኋላ በተለያዩ የደንብ ጥሰቶች ምክንያት ተባረዋል።

የዚህ ዓመት ውጤት አንድምታ ሲታይ፥ ለዓመታት ከትውልድ ትውልድ ሲንከባለል የተሻገረውን እና ተሸፋፍኖ የቆየውን የትምህርት ስርዓት ብልሽት የሚያሳይ ነው ብለዋል ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በመግለጫቸው።

ለዚህም መንግሥት የትምህርት ስርዓቱን ባለማሻሻል፣ ወላጆች ልጆቻቸውን ባለመከታተልና በሥነምግባር ባለመቅረፅ፣ ትምህርት ቤቶች እና ባለሀብቶች በጋራ የወድቀቱ ተጠያቂ ናቸው ብለዋል።

ከላይ የተጠቀሱ አካላት ቀጣይ መፍትሄዎች ላይ የአንበሳውን ድርሻ በመውሰድ ሊሰሩ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ዩኒቨርስቲ ከሚቀላቀሉት እና መደበኛ ኮርስ ከሚጀምሩ 29,909 ተማሪዎች ውጭ ያሉ ሌሎች ከ100 ሺህ የሚልቁ ተማሪዎች በውጤታቸው ተለይተው እንደ ዩኒቨርሲቲዎች የመቀበል አቅም እየታየ ለአንድ ዓመት የማሻሻያ ትምህርት ወስደው በድጋሚ እንዲፈተኑ ይደረጋል ብለዋል።

ውጤቱ አስደንጋጭ እንደሆነ እንረዳለን ያሉት ሚኒስትሩ፣ ነገ የተሻለ ትውልድ ለመፍጠር በዚህ ውስጥ ልናልፍ ግድ ይለናል፤ ይህ የማንቂያ ደወል ሊሆን ይገባል ብለዋል።

በዘንድሮው የ12 ከፍል ፈተና ውጤት ከተፈጥሮ ሳይንስ 666 ከፍተኛ ውጤት ሆኖ ተመዘገበ

በዘንድሮው የ12 ከፍል ፈተና ውጤት በሀገር አቀፍ ደረጃ ከተፈጥሮ ሳይንስ የተመዘገበው 666 ከፍተኛ ውጤት ሆኖ መመዝገቡን የትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ።

የትምህርት ሚኒስቴር እና የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በጋራ በ12ኛ ክፍል ውጤት ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫውም፥ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተመዘገበው ከፍተኛ ውጤት ከሰባት መቶ 666 በተፈጥሮ ሳይንስ ሲሆን፤ ከማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ ከስድስት መቶ 524 መመዝገቡ ተጠቅሷል።

በተፈጥሮ ሳይንስ 600 እና ከዛ በላይ ያስመዘገቡ 263 ተማሪዎች መኖራቸውም በመግለጫው ላይ ተመልክቷል።

በማህበራዊ ሳይንስ በአጠቃላይ 500 እና ከዛ በላይ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ 10 ተማሪዎች መሆናቸውም ተጠቅሷል። (ሰለሞን ከበደ እና ዋለልኝ ታምር፤ ኢዜአ)

ፕሮፌሰር ብርሃኑ እንዳሉት ውጤቱ አስደንጋጭ ነው። ግን በትክክል መደረግ ያለበት ደፋር ውሳኔ ነው። በዘመነ ት ህነግ በገነት ዘውዴ መበላሸት የጀመረው የትምህርት ሚኒስቴር አሠራር ትውልድ በማክሸፍ አሁን ላለንበት ዝቅጠት ዳርጎናል። ይህ ደግሞ በዕቅድ የተደረገ ኢትዮጵያን የማፍረስ ትልቁ ፕሮጀክት ነው። ይህ እኩይ ዓላማ ቀጥሎ ትምህርት ሚኒስቴርን ሲያበላሹ እና ትውልዱን መቀመቅ ሲከቱ ከነበሩት መካከል ሌላው ተጠቃሽ ሸፈራው ሽጉጤ ነው።

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ከእነዚህ ትውልድ አፍራሾች የተረከቡትን ትምህርት ሚኒስቴር በድፍረት ወሳኝ እርምጃዎችን በመውሰድ ለዚህ ስላበቁትና አገርን የመታደግ ትልቁን እርምጃ ስለወሰዱ ትልቅ ምስጋና ሊሰጣቸው ይገባል። እንዲህ ዓይነት ደፋርና ማርሽ ቀያሪ እርምጃ በሌሎቹም የፖለቲካ አካሄዶቻችን ላይ መታየት ይገባዋል። ኢትዮጵያ መፈወስ የምትጀምረው ዛሬ ነው።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ 

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Left Column, News Tagged With: berhanu nega, ministry of education, operation dismantle tplf

Reader Interactions

Comments

  1. Tesfa says

    January 27, 2023 12:17 pm at 12:17 pm

    ወገኖቼ ይህ ውጤት የሚጠበቅ ነው። ከንጉሱ ፍንገላ በህዋላ ሃገሪቱ መሰረቷ እየተናጋ ከአንድ አፍራሽ ወደ ሌላው አፍራሽ ስትሸጋገር አሁን ያለንበት የዘርና የሃይማኖት ፍትጊያ ላይ ደርሰናል። ታዲያ ባለፉት ዘመናት በልዪ ልዪ የትምህርት ተቋሞች በመጀመሪያ ዲግሪም ሆነ በሁለተኛና ብሎም ዶ/ር ለመባል የተደረገው ውድድርና ቆብ መጫንም ሁሉም ባይባል ይበልጡ ባዶ ነው። የሃገሪቱን የትምህርት አሰጣጥና የተማሪዎችን የወደፊት እድል ፈንታ ለማዘመን የሚቻለው ዓለም አቀፋዊ የሆነ መለኪያና የመማሪያ ቋንቋ ሲኖር ብቻ ነው። በኦሮምኛ ተማረ ወይ በአማርኛ ፋይዳ ቢስ ነው። ዛሬ አለም በሶስት ቋንቋዎች ተወጥራ ተይዛለች። ከዚህ ቀዳሚው እንግሊዝኛ ቋንቋ ሲሆን ሌሎቹ ፈረንሳይኛና ስፓኒሽ ናቸው። ይህ ማለት ሌላው ቋንቋ አይጠቅምም ለማለት አይደለም። ግን ትምህርቱ ዓለም አቀፋዊ ተሰሚነትና ተቀባይነት እንዲኖረው የምርምር ውጤቶች በእነዚህ ቋንቋዎች ቢጻፉ ሥርጭታቸው ከፍ ይላል ለማለት እንጂ። ባጭሩ የሃገሪቱ ትምህርት በእንግሊዘኛ ቋንቋ ቢሰጥ ብዙ ነገሮችን ለመቅረፍ መሳሪያ ይሆናል። አንድ መስመር በእንግሊዝኛ ቋንቋ አረፍተ ነገር አሳክቶ መጻፍ የማይችል ሰው ዶ/ር ሲባል የሚያሳዝን ነው።
    ለውጤቱ እንዲህ መውረድ የነበረውና ያለው ጨቋኝና ዘረኛ ሥርዓት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጉ እንዳለ ሆኖ የመምህራንም ከተማሪው አለመሻል አንድ የችግሩ አካል ነው። በዘሩና በቋንቋው እየተደገፈ ያለፈው ሁሉ አሁን ግባና ዋኝ ሲባል መስጠሙ ነገራችን ሁሉ ውሻላዊ እንደነበርና እንደሆነ ይነግረናል። ዶ/ር ተብለው ዛሬ በየቦታው እየዞሩ የሚለፈልፉ የሰለጥኑበትን ሙያ ትተው የመድረክ ሰው በመሆን ሰዎችን በዲስኩር በሃይማኖትና በሳይኮሎጂ አልፎ ተርፎም ከአሜሪካ የማታለያ ዘዴ በተቀዳው ሞቲቬሽናል ንግግር የሚያምታቱት ፍሬ ቢሶች ሁሉ ወደ ልቦናቸው ተመልሰው በሰለጥኑበት ሙያ የሚችሉትን በማድረግ ህዝባችንና ሃገራችን ቢያግዙ መልካም ነው። ተጨባጩ ተግባር ይህ ነውና!
    ለእኔ ፈተና ከተቀመጡት መካከል 3% ማለፉ አስደንጋጭ ሳይሆን አይን ከፋች ነው። የት ላይ ነው የቆምነው? ወዴትስ እየተጓዝን ነው? የፓለቲካ ቶስቷሶች ለመጣ ለሄደው ስርዓት ሁሉ በማደግደግ ጊዜአዊ ፍርፋሪ ከመልቀም ይልቅ ለትውልድና ለሃገር ዘመን ተሻጋሪ የሆነ ተግባር ፈጽመው ቢያልፉ በግፍ ከተገኘ እልፍ የብር ክምር በእጅጉ ይልቃል። ምድሪቱ በክፋት ተይዛለችና ይህ ጨካኝና ግፈኛ ትውልድ እይታው እንዲለወጥ ለማድረግ መጀመሪያ የራስን አስተሳሰብ መለወጥ ቀዳሚ ተግባር ይሆናል። ለሃገርህ፤ ለወገንህ እየተባለ በሰሜንና በሌሎች አካባቢዎች ሂዶ የተሰዋው ቤተሰብ ዛሬ ላይ ማን ነው ዞር ብሎ የሚያያቸው? ልጆቻቸው ከወዳቂው 97% ውስጥ እንዳይሆኑ የሚረዳቸው ማን ነው? በፈተናው የወደቁት የኑሮ ጫና የሚያጣድፋቸው፤ የጠራ ትምህርት ያላገኙ፤ በጦርነትና በግፈኞች የተፈናቀሉ፤ መብራትና የመማሪያ መሳሪያዎች ያልተሟላላቸው ይበልጦቹ የአርሶ አደርና የድሃ ልጆች ናቸው። ይህ እንዳይደገም ግን አሁን ያለውም የፓለቲካ አቲካራና መፈናቀል ፋታ አይሰጥም።
    በመጨረሻም ፈተና መውደቅ የዓለም ሁሉ መጨረሻ አይደለም። ያኔም ይወደቃል፤ ዛሬም ዛሬ ነው። ዋናው በህይወት ተስፋ አለመቁረጥ ነው። የእጅ ሙያ ከወታደራዊ ተቋሞች (ከሰባት አመት አገልግሎት በህዋላ መውጣት ይቻላል)፤ ከግል ኩባኒያዎች፤ በግልና በህብረት በመፍጨርጨር የመኖሪያ ብልሃት በመፍጠር ኑሮን ማጣፈጥ ይቻላል። በዓለም ላይ የናጠጡት ሃብታሞች ዶ/ር፤ እንጂኒየር ገለ መሌ የሚል የስም ቅጥያ ያላቸው አይደሉም። ስለሆነም ውጤት ላልመጣላቸው ተፈታኞች የማስተላልፈው መልዕክት አትደናገጡ። ችግሩ እናንተ ያመጣችሁት ሳይሆን በየዘመናቱ በጠበንጃ አንጋቾች የምትናወጠው ሰላም አልባ ሃገር የፈጠረችው ትርምስና ምስቅልቅል ነው። ሰላም ቢኖር፤ ሰው በሰውነቱ ቢታይ፤ በቋንቋና በዘሩ በክልሉ ባይሰላ የእናትም ውጤት የተሻለ እንደሚሆን ጭራሽ አልጠራጠርም። ስለሆነም አይዞአችሁ!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ሤራ አክሻፊው ጎንደር ለሦስተኛ ጊዜ ታሪክ ሠራ May 10, 2023 09:25 am
  • ማር በከፍተኛ ደረጃ የኮንትሮባንድ ሰለባ ሆኗል May 9, 2023 09:24 am
  • ኦነግ በኦሮሚያ ሪፈረንደም እንዲካሄድ መጠየቁ ለሰላም ንግግሩ ዕንቅፋት ሆነ May 4, 2023 01:12 am
  • መረጃ ቲቪ ያጋራው አሳሳች መረጃ May 2, 2023 12:37 pm
  • “ከፈጣሪ በታች መከላከያ የሁላችን ዋስ ጠበቃ ነው፤ ትልቅ ይቅርታ እንጠይቃለን” April 13, 2023 10:19 am
  • በትግራይ የ”ልጆቻችን የት ናቸው?” ጥያቄ እየተሰማ ነው April 13, 2023 08:56 am
  • በትህነግ የፈረሰው የአክሱም ኤርፖርት ያስከተለው ዘርፈብዙ ኪሣራ April 13, 2023 03:21 am
  • “የከተማው ነዋሪ በመሰላቸቱ ተፈናቃዮች ከፍተኛ የምግብ ችግር” ገጥሟቸዋል April 12, 2023 09:23 am
  • ከዕድሜ ልክ እስከ 20 ዓመት ቅጣት ተበይኖባቸዋል April 11, 2023 02:58 pm
  • የኡጋንዳ የክልሎች ሚኒስትር በቆርቆሮ ሌብነት ተጠርጥረው ታሰሩ April 10, 2023 03:59 pm
  • ታከለ ከተነሳ በኋላ የመዐድን ሌቦች እየተያዙ ነው April 6, 2023 02:53 pm
  • አገር ለማተራመስ ያለመ የምሁራን፣ የሚዲያ ባለቤቶችና አክቲቪስቶች ህቡዕ ቡድን ተያዘ April 4, 2023 10:07 am
  • በ10 ዓመት ውስጥ ከ44 ቢሊየን ዶላር በላይ ሸሽቷል April 4, 2023 09:26 am
  • አየር ጨብጦ አሁን ያለውን መንግሥት ከሥልጣን ልቀቁ አይሆንም March 29, 2023 09:47 am
  • ሦስት ትውልድ የበላ የሐሰት ትርክት! March 23, 2023 11:59 am
  • “ሽብርተኝነቱን ማንሳቱ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለማቋቋም ይረዳል” – ዶ/ር ጌዲዮን March 22, 2023 05:05 pm
  • አስነዋሪ ተግባር ሲፈጸምባቸው የነበሩ የምሽት ክለቦች ተዘጉ March 22, 2023 12:57 pm
  • ህወሓትን ከሽብርተኝነት እንዲሰረዝ የወሰናችሁ ሁሉ ተጠያቂዎች ናችሁ – ኢዜማ March 22, 2023 12:06 pm
  • የኡጋንዳ ፓርላማ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በእስር የሚያስቀጣ ወንጀል የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ አጸደቀ March 22, 2023 12:44 am
  • በጌታቸው ምርጫ ማግስት በትግራይ ሕዝባዊ ዐመፅ ተጀመረ March 21, 2023 11:01 pm
  • በትግራይ ሥልጣንና ንጉሥ ፈጣሪነት ከአድዋ ወደ ራያ ተሻገረ March 19, 2023 03:45 am
  • ኤርሚያስ ከጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው March 19, 2023 02:44 am
  • እየተገባደደ ያለው የምስራቅ አፍሪቃ የትራንስፖርት ኮሪደርና ለውጥ የናፈቃት ኤርትራ March 15, 2023 04:44 pm
  • በባዶ እግር በሮም አበበን ለመድገም March 15, 2023 01:40 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule