
ፈተና መስረቅ መላ ሊበጅለት ይሆን?
የትምህርት ሚኒስቴር እና ኢመደኤ የሳይበር ደህንነትን ለማስጠበቅ በሚያስችሉ የምርምር፣ ልማት እና ስልጠናዎች ላይ በጋራ መስራት መከሩ።
የትምህርትሚኒስቴር እና የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲን (ኢመደኤ) የሳይበር ደህንነትን ለማስጠበቅ በሚያስችሉ የምርምር፣ ልማት እና ስልጠናዎች ላይ በጋራ መስራት በሚያስችላቸዉ ጉዳይ ላይ መምከራቸው ተገለፀ።
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲን (ኢመደኤ) ጎብኝተዋል።
በጉብኝታቸው ወቅት የኤጀንሲውን የሳይበር ተሰጥዎ ልማት ማዕከልን፣ በኤጀንሲዉ ለምተዉ በዲጂታል ኤግዚብሽን ማዕከል የቀረቡ ምርት እና አገልግሎትን እንዲሁም የኢመደኤ ሠራተኞችና የኃላፊዎችን ቢሮዎች ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
ከጉብኝቱ ጎን ለጎን ሚኒስትሩ ከኢመደኤ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል።
በዉይይታቸዉም የሳይበር ደህንነትን ለማስጠበቅ በሚያስችሉ የምርምር፣ ልማት እና ስልጠናዎች ላይ በጋራ መስራት በሚያስችላቸዉ ጉዳይ ላይ መምከራቸውን ከኢመደኤ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ (አዲስ ማለዳ)
አስተያየት ሰጪዎች ምክክሩ በትምህርት ሚኒስቴር በኩል በተደጋጋሚ የሚከሰተውን የፈተና መሰረቅ አንድ መቋጫ ላይ ያደርሰዋል የሚል ግምት እንዳላቸው ተናግረዋል።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply