ፈተና መስረቅ መላ ሊበጅለት ይሆን? የትምህርት ሚኒስቴር እና ኢመደኤ የሳይበር ደህንነትን ለማስጠበቅ በሚያስችሉ የምርምር፣ ልማት እና ስልጠናዎች ላይ በጋራ መስራት መከሩ። የትምህርትሚኒስቴር እና የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲን (ኢመደኤ) የሳይበር ደህንነትን ለማስጠበቅ በሚያስችሉ የምርምር፣ ልማት እና ስልጠናዎች ላይ በጋራ መስራት በሚያስችላቸዉ ጉዳይ ላይ መምከራቸው ተገለፀ። የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲን (ኢመደኤ) ጎብኝተዋል። በጉብኝታቸው ወቅት የኤጀንሲውን የሳይበር ተሰጥዎ ልማት ማዕከልን፣ በኤጀንሲዉ ለምተዉ በዲጂታል ኤግዚብሽን ማዕከል የቀረቡ ምርት እና አገልግሎትን እንዲሁም የኢመደኤ ሠራተኞችና የኃላፊዎችን ቢሮዎች ተዘዋውረው ጎብኝተዋል። ከጉብኝቱ ጎን ለጎን ሚኒስትሩ ከኢመደኤ ከፍተኛ … [Read more...] about የትምህርት ሚኒስቴር እና ኢንሳ በጋራ ለመስራት መከሩ
INSA
የሽብር ጥቃት ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ በቁጥጥር ስር ዋሉ
በአዲስ አበባና በአንዳንድ የኦሮሚያ ከተሞች የተቀናጀ የሽብር ጥቃት ለመፈፀም አቅደው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የሽብር ቡድን አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የደህንነትና ፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይል አስታወቀ፡፡ የደህንነትና ፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይል ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፥ በአዲስ አበባና በአንዳንድ የኦሮሚያ ከተሞች ሁከት፣ ሽብርና ትርምስ በመፍጠር ድብቅ የፖለቲካ አጀንዳቸውን ለማሳካት በሚንቀሳቀሱ የውጭ እና የውስጥ ፀረ-ሰላም ኃይሎች የሚደገፉ የሸብርተኞቹ የህወሓትና የሸኔ ቡድን አባላት በሰው ሕይወትና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ለማድረስ ሴራ ወጥነው ወደ እንቅስቃሴ ለመግባት በዝግጅት ላይ እንዳሉ በጋራ ግብረ ኃይሉ በተደረገባቸው ጥብቅና የተቀናጀ ክትትል በቁጥጥር ስር ውለዋል። ይህን እኩይ የጥፋት ሴራ ለመፈጸም ከውጭ በተለያዩ አካላት በሚደረግላቸው … [Read more...] about የሽብር ጥቃት ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ በቁጥጥር ስር ዋሉ
አዲሱ የኢንሳ አርማ
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ የቀድሞዉን አርማ የቀየረ ሲሆን የቀድሞውን የኤጀንሲዉን አርማ (logo) እና ብራንዲንግ ለመቀየር ዲዛይኑን ለመስራት እንደ መነሻ የተወሰዱ ሃሳብ በአዲስ መልክ ከተሻሻለዉ የተቋሙ ተልዕኮ እና ራዕይ ጋር በማዛመድ የተሰራ ነዉ። ከእነዚህም ውስጥ በዋነኝነት ጋሻ (Shield)፡ ሳይበር(Cyber Security)፡ ቁልፍ (Key)፡የንስር አይን (An Eagle Eye)፡ የትክክል ምልክት (Right sign) የሚባሉትን ሃሳቦች አካቷል። ለተመረጠው የአርማ (logo) ዲዛይን ማብራራያ እንደ ሚከተለው ቀርቧል። የቀድሞዉ አርማ 1 ጋሻ (Shield) በኢትዮጵያ ታሪክ ብሎም በዓለም አቀፍ ታሪኮች ጥቃትን የመከላከያ መሳሪያ ቀዳሚ ተደርጎ የሚወሰደው አንዱ ጋሻ ነው፤ ስለዚህም በአርማው ላይ የሚታየው ጋሻ ማንኛውም አይነት ጥቃትን በብቃት መከላከል … [Read more...] about አዲሱ የኢንሳ አርማ
የህወሃት/ኢህአዴግ የስለላ መረብ እየተበረበረ ነው
“አዲሱ ቴሌ እና የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ/ኢንሳ” በሚል ርዕስ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ያዘጋጀው ጥናታዊ ሪፖርት የታላላቅ አገር የስለላ ተቋማት፣ ለጉዳዩ አግባብ ያላቸው መምሪያዎችና የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ትኩረት መሳቡ ታወቀ። ሪፖርቱን አገራቱ በራሳቸው ቋንቋ በመተርጎም የህወሃት/ኢህአዴግን የስለላ መረብ ከተለያየ አቅጣጫ እየመረመሩት ነው። የጎልጉል ምንጭ የሆኑ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው እንዳስታወቁት አኢጋን የህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም አዲሱ ቴሌን (ኢትዮ ቴሌኮምን) ከዋንኛው የስለላ መ/ቤት ብሔራዊ የመረጃና ደኅንነት አገልግሎት በእንግሊዝኛው ምህጻረ ቃል NISS (National Intelligence and Security Service) እና የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ ወይም በእንግሊዝኛው … [Read more...] about የህወሃት/ኢህአዴግ የስለላ መረብ እየተበረበረ ነው