የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ የቀድሞዉን አርማ የቀየረ ሲሆን የቀድሞውን የኤጀንሲዉን አርማ (logo) እና ብራንዲንግ ለመቀየር ዲዛይኑን ለመስራት እንደ መነሻ የተወሰዱ ሃሳብ በአዲስ መልክ ከተሻሻለዉ የተቋሙ ተልዕኮ እና ራዕይ ጋር በማዛመድ የተሰራ ነዉ። ከእነዚህም ውስጥ በዋነኝነት ጋሻ (Shield)፡ ሳይበር(Cyber Security)፡ ቁልፍ (Key)፡የንስር አይን (An Eagle Eye)፡ የትክክል ምልክት (Right sign) የሚባሉትን ሃሳቦች አካቷል። ለተመረጠው የአርማ (logo) ዲዛይን ማብራራያ እንደ ሚከተለው ቀርቧል።
1 ጋሻ (Shield)
በኢትዮጵያ ታሪክ ብሎም በዓለም አቀፍ ታሪኮች ጥቃትን የመከላከያ መሳሪያ ቀዳሚ ተደርጎ የሚወሰደው አንዱ ጋሻ ነው፤ ስለዚህም በአርማው ላይ የሚታየው ጋሻ ማንኛውም አይነት ጥቃትን በብቃት መከላከል መቻልን፤ ከውጭ ሃይላት የሚቃጡ የመረጃ ምዝበራ ጥቃትን መመከት መቻልን የሚያመለክት ይሆናል።
2 የሳይበር ደኅንነት (Cyber Security)
የበይነ መረብ (Internet) እና ተያያዥ ቴክኖሎጂዎችን የሚመለከት ሲሆን፤በአለማችን እየታየ ያለው ፈጣን የቴክኖሎጂ እድገት በበይነ መረብ አማካኝነት የሚሰነዘሩ ጥቃቶች እየተበራከቱ እንዲመጡ እያደረገ ይገኛል፤በዚህም አማካኝነት አንድ ሀገር ጠንካራ የሆነ የበይነ መረብ (የሳይበር) ደህንነት ሊኖረው ይገባል። ተቋማችንም በዋነኛነት በዚሁ በሳይበር ላይ ተንተርሰው የሚከሰቱ ጥቃቶችን በብቃት መከላከል ጋር የተያያዘ መሆኑን የሚያመለክት ነው።
3 ቁልፍ (Key)
ደህንነትን ያመለክታል፤ ደህንነት ስንል የመረጃ እና የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶች ደህንነትን ሲሆን፡ የመረጃተአማኒነት፣ ሚስጥራዊነትእናተደራሽነትተጠብቆ፤ መረጃዎችን በመለዋወጥ ሀገርን ከመረጃ መንታፊዎች በመታደግ አስፈላጊውን መረጃ መለዋወጥ ማስቻልን የሚያመለክት ነው።
4 የንስር አይን (An Eagle Eye)
ከርቀት በከፍተኛ ጥራት መመልከትን እና መለየትን ያመለክታል፤ በሀገር (የመንግስት እና የግል ተቋማት) ላይ ሊደርስ የሚችልን ማንኛውንም የበይነ መረብን መሰረት ያደረገ የሳይበር ጥቃትን ወይንም ማንኛውም አይነት ቴክኖሎጂ ላይ መሰረት ያረገ ጥቃትን አስቀድሞ በማየትና በመለየት በሀገር ላይ ሊደርስ ከሚችለው ጥፋት መከላከልን ያመለክታል።
5 የትክክል ምልክት (Right sign)
የአሰራር ጥራትን እና ማረጋገጥን (Confirmation) ያመለክታል። በተጨማሪም ከተቋሙ መጠሪያ ስም ስር ያለው ዲዛይን በዋና ቀለማት እና የሳይበር ምልክት ላይ ተመስርቶ የተሰራ ሲሆን ይኸም መቀናጀትን፣ መናበብን እና መደጋገፍን ያመለክታል።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
mohamed says
i want subscribe this newspaper