ሸኔና አልሸባብ መደምሰሳቸው የጊዜ ጉዳይ ሆነ በፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ ግብዣ የኢፌዴሪ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ በዩጋንዳ በተከበረው 41ኛው የሰራዊት ቀን ላይ ተገኝተው በዚያው ከዩጋንዳ የጸጥታ ሃይላት ጋር በሁለቱ አገሮች ድንበሮች ዙሪያ በዝግ መክረው መምጣታቸውን ተከትሎ ኢትዮጵያና ኬንያ በድንበር አካባቢ የሚንቀሳቀሱ የሸኔንና የአልሸባብ ሃይሎችን በጋራ ለመመከት መስማማታቸውን ይፋ አደረጉ። ዜናው በርካታ ጉዳዮችን የሚያነካካ በመሆኑ የገዘፈ ሆኗል። ምስራቅ አፍሪካን በንግድና በኢንቨስትመንት ለማቆራኘት እንዲቻል ቻይና በቀጥታ ከምታደርገው ከምታከናውነው ተግባሯ በተጨማሪ ቀጠናው የሰላም ኮሪዶር እንዲሆን አገራቱ ጸረ ሰላም ሃይሎችን በጋራ መመከት እንዲችሉ፣ አንዱ በሌላው ላይ ተቃዋሚ እንዳያደራጅ አቅዳ ልዩ ኮምቦይ መሰየሟን ማስታወቋ … [Read more...] about የኢትዮጵያና የኬኒያ ፖሊስ ያደረጉት ስምምነት እንደምታ
federal police
የሽብር ጥቃት ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ በቁጥጥር ስር ዋሉ
በአዲስ አበባና በአንዳንድ የኦሮሚያ ከተሞች የተቀናጀ የሽብር ጥቃት ለመፈፀም አቅደው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የሽብር ቡድን አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የደህንነትና ፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይል አስታወቀ፡፡ የደህንነትና ፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይል ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፥ በአዲስ አበባና በአንዳንድ የኦሮሚያ ከተሞች ሁከት፣ ሽብርና ትርምስ በመፍጠር ድብቅ የፖለቲካ አጀንዳቸውን ለማሳካት በሚንቀሳቀሱ የውጭ እና የውስጥ ፀረ-ሰላም ኃይሎች የሚደገፉ የሸብርተኞቹ የህወሓትና የሸኔ ቡድን አባላት በሰው ሕይወትና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ለማድረስ ሴራ ወጥነው ወደ እንቅስቃሴ ለመግባት በዝግጅት ላይ እንዳሉ በጋራ ግብረ ኃይሉ በተደረገባቸው ጥብቅና የተቀናጀ ክትትል በቁጥጥር ስር ውለዋል። ይህን እኩይ የጥፋት ሴራ ለመፈጸም ከውጭ በተለያዩ አካላት በሚደረግላቸው … [Read more...] about የሽብር ጥቃት ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ በቁጥጥር ስር ዋሉ
መፍትሔ ለትግራይ: ጊዜያዊ አስተዳደር ማቋቋም፣ ፌዴራል ፖሊስና መከላከያ መላክ
አርብ ዕለት የፌዴሬሽን ምክርቤት አፈጉባዔ የሆኑት አቶ አደም ፋራህ የትግራይን ሁኔታ አስመልክቶ ወሳኝ ንግግር አድርገው ነበር። በወቅቱም አፈጉባዔው ህወሓት ስለተባለው አሸባሪ የወንበዴዎች ቡድን አማራጭ ያሉት በዚህ መልኩ አስቀምጠዋል። “ከትግራይ ሁኔታ አንጻር በአገርአቀፍ ደረጃና በሁሉም ክልሎች ምርጫ የማስፈጸም ሥልጣን የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሆኖ፤ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማቋቋም ደግሞ የፌዴራል መንግሥት ሥልጣን ሆኖ፤ ሕገመንግሥቱ ባልሰጣቸው ሥልጣን የምርጫ ኮሚሽን አቋቁመው፤ አግላይ በሆነ አካሄድ ምርጫ አድርገው፤ ምርጫውን አሸንፈን መንግሥት መሥርተናል የሚሉበት ሁኔታ ስላለ፤ ይሔ በግልጽ የሕገመንግሥቱን ድንጋጌ የሚጥስ ስለሆነ፤ የትግራይ ክልል መንግሥት ሕገመንግሥቱን አደጋ ላይ እንደጣለ ይቆጠራል ማለት ነው”። ስለ እርምጃ አወሳሰድ በተመለከተ አቶ አደም ፋራህ የሚከተለውን … [Read more...] about መፍትሔ ለትግራይ: ጊዜያዊ አስተዳደር ማቋቋም፣ ፌዴራል ፖሊስና መከላከያ መላክ
ፌዴራል ፖሊስ የራሱ ሄሊኮፕተር እንዲኖረው ጠየቀ
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በሲሲቲቪ እና በድሮን የታገዘ የጸጥታ ጥበቃ ስራዎችን ሊያከናውን መሆኑን አስታወቀ። ኮሚሽኑ ለህዝብ ጥያቄ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት የሚስያችሉ ቴክኖሎጂዎችን ሊጠቀም መሆኑን አስታውቋል። ኮሚሽኑ ለህዝብ ጥያቄ ፈጣን ምላሽና አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን ማሟላት ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫው መሆኑን አስታውቋል። የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ጀይላን አብዲ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት የወንጀል መከላከል ስራን በሲሲ ቲቪ ካሜራ የተደገፈ እንዲሆን ማድረግ፣ ዘመናዊ የመገናኛ ራዲዮችን መጠቀም እንዲሁም ለወንጀል ምርመራ የሚስያፈልጉ በተለይ ለፎረንሲክ ምርመራ የሚውሉ ቴክኖሎጂዎችን፣ መሳሪያዎች፣ ሶፍትዌሮችን በማሟላት አገልግሎት ላይ እንዲውሉ ለማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል። ከዚህ ቀደም ፖሊስ በሀገሪቱ የሚከናወኑ ሀገራዊ፣ … [Read more...] about ፌዴራል ፖሊስ የራሱ ሄሊኮፕተር እንዲኖረው ጠየቀ
ከመስከረም 25 በኋላ “መንግሥት የለም” በሚል ትርምስ ለመፍጠር በሚሰሩ አካላት ላይ እርምጃ እወስዳለሁ – የፌዴራል ፖሊስ
የፌዴራል ፖሊስ ጥብቅ ፍተሻ እያደረገ ያለው ከአማራ ክልል በሚመጡ መንገደኞች ብቻ ሳይሆን ወደ መዲናዋ በሚያስገቡ በሁሉም በሮች ላይ ተመሳሳይ የቁጥጥር ስራ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ። የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል እንደሻው ጣሰው ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በአልን ምክኒያት በማድረግ በአዲስ አበባ የሽብር ድርጊት ለመፈጸም እና ይህንኑ ተከትሎ ሁከት እና ግጭት እንዲፈጠር በዝግጅት ላይ የሚገኙ አካላት እንዳሉ ደርሰንበታል ያሉት ኮሚሽነር ጄኔራሉ መረጃውን መሰረት በማድረግ ወደ አዲስ አበባ በሚያስገቡ በሁሉም በሮች ላይ ጥብቅ ፍተሻ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል ። የበዓሉን እንቅስቃሴ ለማደፍረስ ዕቅድ ያላቸው ሀይሎች እንዳሉ ፖሊስ በምርመራ እንደደረሰበት ጠቁመው፤ እነዚህ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቀቆጠቡ አሳስበዋል። ከመስከረም … [Read more...] about ከመስከረም 25 በኋላ “መንግሥት የለም” በሚል ትርምስ ለመፍጠር በሚሰሩ አካላት ላይ እርምጃ እወስዳለሁ – የፌዴራል ፖሊስ