አርብ ዕለት የፌዴሬሽን ምክርቤት አፈጉባዔ የሆኑት አቶ አደም ፋራህ የትግራይን ሁኔታ አስመልክቶ ወሳኝ ንግግር አድርገው ነበር። በወቅቱም አፈጉባዔው ህወሓት ስለተባለው አሸባሪ የወንበዴዎች ቡድን አማራጭ ያሉት በዚህ መልኩ አስቀምጠዋል።
“ከትግራይ ሁኔታ አንጻር በአገርአቀፍ ደረጃና በሁሉም ክልሎች ምርጫ የማስፈጸም ሥልጣን የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሆኖ፤ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማቋቋም ደግሞ የፌዴራል መንግሥት ሥልጣን ሆኖ፤ ሕገመንግሥቱ ባልሰጣቸው ሥልጣን የምርጫ ኮሚሽን አቋቁመው፤ አግላይ በሆነ አካሄድ ምርጫ አድርገው፤ ምርጫውን አሸንፈን መንግሥት መሥርተናል የሚሉበት ሁኔታ ስላለ፤ ይሔ በግልጽ የሕገመንግሥቱን ድንጋጌ የሚጥስ ስለሆነ፤ የትግራይ ክልል መንግሥት ሕገመንግሥቱን አደጋ ላይ እንደጣለ ይቆጠራል ማለት ነው”።
ስለ እርምጃ አወሳሰድ በተመለከተ አቶ አደም ፋራህ የሚከተለውን ግልጽ መልዕክት ለበረኸኞቹ አስተላልፈዋል፤
“የፌዴራል መንግሥት ሊወስዳቸው የሚችሉ እርምጃዎች በሕጉ ላይ በግልጽ ተቀምጠዋል፤
- “የመጀመሪያው ሕግ አውጪውንና ሕግ አስፈጻሚውን በማገድ ለፌዴራል መንግሥት ተጠሪ የሆነ ጊዜያዊ አስተዳደር በማቋቋም ችግሩ እንዲፈታ ማድረግ ነው
- “በተያያዘም የፌዴራል ፖሊስንና የመከላከያ ሠራዊትን በክልሉ ላይ በማሰማራት ሕገመንግሥታዊ ሥርዓቱን አደጋ ላይ የጣለው ድርጊት እንዲቆም ማድረግ ነው።
“እነዚህን እርምጃዎች ለመውሰድ የሚያስችል በቂ የሆነ ሕገመንግሥታዊ መሠረት አለ” በማለት አቶ አደም ግልጽ መልዕክት ለህወሓት ወንበዴዎች አስተላልፈዋል።
የአቶ አደም ንግግር ከዚህ በታች ይደመጣል።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
ነፃ ሕዝብ says
ጎልጉሎች እንዳው በፈጠራሽሁ የኮ/ል አብይ መንግሥት ይህንን ያደርጋል ብላችሁ ትጠብቃላችሁ እንዴ ? እርሱ ምስኪኑን የወላይታ ሕዝብ ይጨርስ እንጂ የትግራይን ፋሽስት ህወሃት ንክች አያደርገውም ፥ ኮ/ል አብይ የሚበረታው ሕግን የሚያከብሩትንና የሚፈሩትን አባሮ የሚገድለው የሚያስረው ፥ ኮ/ሉ ፍጹም ፈሪና ወሬኛ ነው ፥ በአሁኑ ሰዓት ከፋሽስቱ ህወሃት ጋር ጦርነት ያስፈልጋል የሚል እምነት የለኝም ፥ ህወሃትን የፌደራል በጀት መዝጋት ወይም ማቆም ፥ ከዚያም ዙሪያውን መግቢያ መውጪያ ማሳጣት ፥ ምንም ዓይነት የትራንስፖርት አገልግሎት ወደ ትግራይ እንዳይገባ ማድረግ ፥ ሁሉንም ማዕቀብ መጣልና የሰበሰበው ሚሊሺያ ያለምንም ውጊያ እጁን እንዲሰጥ ማድረግ ይቻላል ፥ ሰፊ የፕሮፖጋንዳ ሥራም ያስፈልጋል ፥ ፕ.መስፍን ወ/ማርያም ነፍሳቸውን ይማርና በአንድ ወቅት እንደተናገሩት ” የትግራይ ሕዝብ በአንድ ፋብሪካ እንደተሰራ ብርጭቆ ነው” ብለው ነበር ፥ በአሁኑ ሰዓት ሕዝቡ በአንድነት ከወያኔ ጋር ይቆማል ብየ አላስብም ፥ አንድ ኩንታል ጤፍ $6000.00 ብር እንደገባ እየተነገረ ባለበት ሕዝቡ ለፋሽስቱ ህወሃት ድጋፉን ያደርጋል የሚል እመነት የለኝም ፥ ለማንኛውም የኦሮሙማው መንግሥት የሚወስደውን እርምጃ እናያለን ።