አርብ ዕለት የፌዴሬሽን ምክርቤት አፈጉባዔ የሆኑት አቶ አደም ፋራህ የትግራይን ሁኔታ አስመልክቶ ወሳኝ ንግግር አድርገው ነበር። በወቅቱም አፈጉባዔው ህወሓት ስለተባለው አሸባሪ የወንበዴዎች ቡድን አማራጭ ያሉት በዚህ መልኩ አስቀምጠዋል። “ከትግራይ ሁኔታ አንጻር በአገርአቀፍ ደረጃና በሁሉም ክልሎች ምርጫ የማስፈጸም ሥልጣን የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሆኖ፤ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማቋቋም ደግሞ የፌዴራል መንግሥት ሥልጣን ሆኖ፤ ሕገመንግሥቱ ባልሰጣቸው ሥልጣን የምርጫ ኮሚሽን አቋቁመው፤ አግላይ በሆነ አካሄድ ምርጫ አድርገው፤ ምርጫውን አሸንፈን መንግሥት መሥርተናል የሚሉበት ሁኔታ ስላለ፤ ይሔ በግልጽ የሕገመንግሥቱን ድንጋጌ የሚጥስ ስለሆነ፤ የትግራይ ክልል መንግሥት ሕገመንግሥቱን አደጋ ላይ እንደጣለ ይቆጠራል ማለት ነው”። ስለ እርምጃ አወሳሰድ በተመለከተ አቶ አደም ፋራህ የሚከተለውን … [Read more...] about መፍትሔ ለትግራይ: ጊዜያዊ አስተዳደር ማቋቋም፣ ፌዴራል ፖሊስና መከላከያ መላክ