ወሳኔው የተላለፈው በዚያን ጊዜው ህወሓት እንደፈለገ በሚዘውረው ፓርላማ ነበር። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ “የኢህአዴግ ከፍተኛ ሹሞችን ልዩ ልዩ ጥቅማጥቅም የሚያስከብር አዋጅ ጸደቀ” በሚል ርዕስ (February 13, 2017) ባተመው ዜና መረጃውን ሲዘግብ ይህንን ብለን ነበር፤ ከሁለት ዓመት በፊት በጭምጭምታ ደረጃ ወሬዉ ወደ አደባባይ የወጣዉ ባለሥልጣናት “ጡረታ” ሲወጡ የሚከበርላቸዉ ጥቅማጥቅም አሁን “ህጋዊ ዕዉቅና” አግኝቷል። ሐሙስ ዕለት በዋለዉ የኢህአዴግ “ፓርላማ” የህወሃት/ኢህአዴግ ከፍተኛ ባለሥልጣናት በልዩ ልዩ ምክንያቶች ከኃለፊነታቸዉ ሲነሱ ጥቅማጥቅማቸዉን የሚያስከብር አዋጅ ተሸሽሎ እንዲጸድቅ ተደርጓል። የተሻሻለዉ አዋጅ ከኃላፊነታቸዉ የሚነሱ የመንግስት ባለሥልጣናት እንደ የኃላፊነት ደረጃቸዉ የመቋቋሚያ አበል፣ የሥራ ስንብት ክፍያ፣መኖሪያ … [Read more...] about ለ6 የህወሓት ተጧሪዎች በ150 ሚሊዮን ብር የተገነቡት ቤቶች በ1.2 ቢሊዮን ብር ሊሸጡ ነው
tigray tplf election
ከጥቅምት ወር ጀምሮ ለትግራይ የበጀት ገንዘብ አይለቀቅም
ከትግራይ ክልል ጋር በተያያዘ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በክልሉ የሚገኙ የካቢኔ አባላት ህጋዊ ባልሆነ ምርጫ ተመርጠናል በሚል የሀገሪቱን ህገ መንግሥት በመጣሳቸው አሁን ባለው ሁኔታ የገንዘብ ሚኒስቴር ለትግራይ ክልል መንግሥት በጀት እንደማይለቅ የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ተናገሩ። በትግራይ ክልል ለሚገኙ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት በወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮች በኩል በተጠና ሁኔታ እንዲደርሳቸው ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝም ጠቅሰዋል። ይህ ለሁለተኛው ሩብ ዓመት (ጥቅምት-ህዳር-ታህሣሥ) ከፌዴራል ለክልሎች የሚለቀቅ በጀት እንደሆነ ይታወቃል። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about ከጥቅምት ወር ጀምሮ ለትግራይ የበጀት ገንዘብ አይለቀቅም
የፌዴሬሽን ም/ቤት ለዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡ ስለ ህወሃት ማብራሪያ ሰጠ
የፌዴሬሽን ምክር ቤት ህወኃትን በተመለከተ ባሳለፈው ውሳኔዎች ዙሪያ ለዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡ ማብራሪያ ሰጥቷል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባዘጋጀው በዚህ መድረክ በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች እና የቆንስላ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል። የፌዴሬሽን ምክር ቤት የትግራይ ክልል ምርጫን በሚመለከት ባሳለፈው ውሳኔ ዙሪያ የፌዴሬሽን ምክር ቤት የሕገ መንግሥት ትርጉምና የማንነት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ጸሐፊ ወርቁ አዳሙ ማብራሪያ አቅርበዋል። በማብራሪያው በ2012ዓ.ም በኢትዮጵያ ሊደረግ የነበረው ሀገራዊ ምርጫ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም ምክር ቤቱ በሕገ መንግሥት ትርጉም ተመሥርቶ ውሳኔ ማሳለፉ ተነስቷል፤ የትግራይ ክልልን የሚመራው ፓርቲ ህወሀት ውሳኔውን ወደ ጎን በመተው ኢ-ሕገ መንግሥታዊ በሆነ መንገድ ምርጫ በማድረግ ወደ መንግሥት … [Read more...] about የፌዴሬሽን ም/ቤት ለዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡ ስለ ህወሃት ማብራሪያ ሰጠ
ለሕገወጡ የትግራይ ምክር ቤትና ካቢኔ የፌዴራል በጀት ድጎማ ተከለከለ
በህገወጥ መንገድ የተቋቋመ ነው ላለው የትግራይ ክልል ምክር ቤት እና ካቢኔ የፌዴራል መንግሥት የበጀት ድጎማ እንደማያደርግ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አስታወቀ፡፡ የክልሉ ምክር ቤት እና ከፍተኛው የህግ አስፈፃሚ አካል (ካቢኔ) ህገመንግሥታዊ ቅቡልነት የላቸውም ያለው ምክር ቤቱ ሁሉም የፌዴራል ተቋማት ምንም ዓይነት ህጋዊ ግንኙነት ማድረግ እንደማይችሉ ገልጿል፡፡ ተቋማቱ የክልሉን ከፍተኛ ስራ አስፈፃሚ አካላት እንደ ህጋዊ አካል በመቁጠር ደብዳቤ መፃፃፍ፣ መረጃ መላላክ፣ ድጋፎች ማድረግ፣ በፌዴራል ደረጃ በሚካሄዱ መድረኮች ላይ ማሳተፍ እንደማይችሉም ነው የምክር ቤቱ አፈ-ጉባዔ አቶ አደም ፋራህ የተናገሩት፡፡ በአንጻሩ የክልሉ ህዝብ መሰረታዊ የልማትና የአገልግሎት ተጠቃሚነቱ እንዳይስተጓጎል እንደ ቀበሌ፣ ወረዳ፣ ከተማ ካሉ ህጋዊ የክልሉ መዋቅሮች ጋር ብቻ ግንኙነት እንደሚደረግ … [Read more...] about ለሕገወጡ የትግራይ ምክር ቤትና ካቢኔ የፌዴራል በጀት ድጎማ ተከለከለ
መፍትሔ ለትግራይ: ጊዜያዊ አስተዳደር ማቋቋም፣ ፌዴራል ፖሊስና መከላከያ መላክ
አርብ ዕለት የፌዴሬሽን ምክርቤት አፈጉባዔ የሆኑት አቶ አደም ፋራህ የትግራይን ሁኔታ አስመልክቶ ወሳኝ ንግግር አድርገው ነበር። በወቅቱም አፈጉባዔው ህወሓት ስለተባለው አሸባሪ የወንበዴዎች ቡድን አማራጭ ያሉት በዚህ መልኩ አስቀምጠዋል። “ከትግራይ ሁኔታ አንጻር በአገርአቀፍ ደረጃና በሁሉም ክልሎች ምርጫ የማስፈጸም ሥልጣን የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሆኖ፤ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማቋቋም ደግሞ የፌዴራል መንግሥት ሥልጣን ሆኖ፤ ሕገመንግሥቱ ባልሰጣቸው ሥልጣን የምርጫ ኮሚሽን አቋቁመው፤ አግላይ በሆነ አካሄድ ምርጫ አድርገው፤ ምርጫውን አሸንፈን መንግሥት መሥርተናል የሚሉበት ሁኔታ ስላለ፤ ይሔ በግልጽ የሕገመንግሥቱን ድንጋጌ የሚጥስ ስለሆነ፤ የትግራይ ክልል መንግሥት ሕገመንግሥቱን አደጋ ላይ እንደጣለ ይቆጠራል ማለት ነው”። ስለ እርምጃ አወሳሰድ በተመለከተ አቶ አደም ፋራህ የሚከተለውን … [Read more...] about መፍትሔ ለትግራይ: ጊዜያዊ አስተዳደር ማቋቋም፣ ፌዴራል ፖሊስና መከላከያ መላክ
ህወሓት “ጭንቅላቱ ደርቋል” – ጠ/ሚ/ር ዐቢይ
ህወሓት የተሰኘው የበረሃ ወንበዴዎች ስብስብ ላለፉት ሁለት ዐሥርተ ዓመታት የኢትዮጵያ ሕዝብ እስኪደነቁር ድረስ ሕገመንግሥት መናድ እያለ ተቃዋሚዎቹን ሁሉ ሲያሸማቅቅ እንዳልኖረ ዛሬ ያንኑ ሕገመንግሥት በመጻረር በትግራይ ሕገወጥ ምርጫ እያካሄደ ይገኛል። ትላንት ማታ በETV በተላለፈው ቃለ ምልልስ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ በትግራይ የሚካሄደውን ሕገወጥ ምርጫ ከጨረቃ ቤት ሥራ ጋር እንደሚያመሳስሉት ገለጹ። ጠያቂው “በትግራይ ክልል የሚካሄደውን ክልላዊ ምርጫ እንዴት ይመለከቱታል?” ብሎ ለጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ላቀረበላቸው ጥያቄ "የትግራይን (የዛሬ) ምርጫ እንደ ጨረቃ ቤት ነው የምመለከተው፤ እዚያ ያለው ኃይል ጭንቅላቱ ደርቋል፤ ኪሱ ሲደርቅ ይጠፋል። እኛ የትግራይ ሕዝብን በልማት እንደግፋለን እንጂ ጦር አናዘምተበትም" ብለዋል። "የትግራይ ምርጫ የጨረቃ ምርጫ ነው! … [Read more...] about ህወሓት “ጭንቅላቱ ደርቋል” – ጠ/ሚ/ር ዐቢይ
አጀንዳ ካልተላከልኝ አልሰበሰብም ሲል የነበረው ሕወሓት ምርጫውን ማስቆም “ጦርነት ማወጅ ነው” አለ
በዓለምአቀፍ የአሸባሪዎች ቋት በሽብርተኝነት እስካሁን ተመዝግቦ የሚገኘውና በትግራይ መሽጎ የተቀመጠው ህወሓት የተሰኘው የበረሃ ወንበዴዎች ቡድን ነገ ለሚደረገው የፌዴሬሽን ምክርቤት ስብሰባ አጀንዳ ካልተላከልኝ አልሰበሰብም በማለት ነሐሴ 27 ቀን 2012 ዓ.ም ለፌዴሬሽን ምክር ቤት በጻፈው ደብዳቤ አስታውቆ ነበር። ከዚህ በመቀጠል ደግሞ አገር አስገንጣይ በረኸኞቹ የተከማቹበት ምክርቤቱ በትግራይ ክልል ሊካሄድ የታሰበውን ምርጫ ለማስቆም በፌዴሬሽን ምክር ቤት የሚተላለፍ ማንኛውም ውሳኔ ጦርነት አዋጅ እንደሚቆጥረው ባወጣው መግለጫ አስታውቋ። ከአሃዱ ሬዲዮና ከቢቢሲ አማርኛ ያወጡትን ዘገባ ከዚህ እንደሚከተለው አቅርበናል። መግለጫው የወጣው የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ከቀናት በፊት ነገ ቅዳሜ የሚካሄድ አስቸኳይ ስብሰባን መጥራቱን አስመልክቶ … [Read more...] about አጀንዳ ካልተላከልኝ አልሰበሰብም ሲል የነበረው ሕወሓት ምርጫውን ማስቆም “ጦርነት ማወጅ ነው” አለ