ከትግራይ ክልል ጋር በተያያዘ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በክልሉ የሚገኙ የካቢኔ አባላት ህጋዊ ባልሆነ ምርጫ ተመርጠናል በሚል የሀገሪቱን ህገ መንግሥት በመጣሳቸው አሁን ባለው ሁኔታ የገንዘብ ሚኒስቴር ለትግራይ ክልል መንግሥት በጀት እንደማይለቅ የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ተናገሩ። በትግራይ ክልል ለሚገኙ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት በወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮች በኩል በተጠና ሁኔታ እንዲደርሳቸው ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝም ጠቅሰዋል። ይህ ለሁለተኛው ሩብ ዓመት (ጥቅምት-ህዳር-ታህሣሥ) ከፌዴራል ለክልሎች የሚለቀቅ በጀት እንደሆነ ይታወቃል። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about ከጥቅምት ወር ጀምሮ ለትግራይ የበጀት ገንዘብ አይለቀቅም
tplf fake election
የፌዴሬሽን ም/ቤት ለዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡ ስለ ህወሃት ማብራሪያ ሰጠ
የፌዴሬሽን ምክር ቤት ህወኃትን በተመለከተ ባሳለፈው ውሳኔዎች ዙሪያ ለዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡ ማብራሪያ ሰጥቷል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባዘጋጀው በዚህ መድረክ በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች እና የቆንስላ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል። የፌዴሬሽን ምክር ቤት የትግራይ ክልል ምርጫን በሚመለከት ባሳለፈው ውሳኔ ዙሪያ የፌዴሬሽን ምክር ቤት የሕገ መንግሥት ትርጉምና የማንነት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ጸሐፊ ወርቁ አዳሙ ማብራሪያ አቅርበዋል። በማብራሪያው በ2012ዓ.ም በኢትዮጵያ ሊደረግ የነበረው ሀገራዊ ምርጫ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም ምክር ቤቱ በሕገ መንግሥት ትርጉም ተመሥርቶ ውሳኔ ማሳለፉ ተነስቷል፤ የትግራይ ክልልን የሚመራው ፓርቲ ህወሀት ውሳኔውን ወደ ጎን በመተው ኢ-ሕገ መንግሥታዊ በሆነ መንገድ ምርጫ በማድረግ ወደ መንግሥት … [Read more...] about የፌዴሬሽን ም/ቤት ለዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡ ስለ ህወሃት ማብራሪያ ሰጠ
መፍትሔ ለትግራይ: ጊዜያዊ አስተዳደር ማቋቋም፣ ፌዴራል ፖሊስና መከላከያ መላክ
አርብ ዕለት የፌዴሬሽን ምክርቤት አፈጉባዔ የሆኑት አቶ አደም ፋራህ የትግራይን ሁኔታ አስመልክቶ ወሳኝ ንግግር አድርገው ነበር። በወቅቱም አፈጉባዔው ህወሓት ስለተባለው አሸባሪ የወንበዴዎች ቡድን አማራጭ ያሉት በዚህ መልኩ አስቀምጠዋል። “ከትግራይ ሁኔታ አንጻር በአገርአቀፍ ደረጃና በሁሉም ክልሎች ምርጫ የማስፈጸም ሥልጣን የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሆኖ፤ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማቋቋም ደግሞ የፌዴራል መንግሥት ሥልጣን ሆኖ፤ ሕገመንግሥቱ ባልሰጣቸው ሥልጣን የምርጫ ኮሚሽን አቋቁመው፤ አግላይ በሆነ አካሄድ ምርጫ አድርገው፤ ምርጫውን አሸንፈን መንግሥት መሥርተናል የሚሉበት ሁኔታ ስላለ፤ ይሔ በግልጽ የሕገመንግሥቱን ድንጋጌ የሚጥስ ስለሆነ፤ የትግራይ ክልል መንግሥት ሕገመንግሥቱን አደጋ ላይ እንደጣለ ይቆጠራል ማለት ነው”። ስለ እርምጃ አወሳሰድ በተመለከተ አቶ አደም ፋራህ የሚከተለውን … [Read more...] about መፍትሔ ለትግራይ: ጊዜያዊ አስተዳደር ማቋቋም፣ ፌዴራል ፖሊስና መከላከያ መላክ
ህወሓት “ጭንቅላቱ ደርቋል” – ጠ/ሚ/ር ዐቢይ
ህወሓት የተሰኘው የበረሃ ወንበዴዎች ስብስብ ላለፉት ሁለት ዐሥርተ ዓመታት የኢትዮጵያ ሕዝብ እስኪደነቁር ድረስ ሕገመንግሥት መናድ እያለ ተቃዋሚዎቹን ሁሉ ሲያሸማቅቅ እንዳልኖረ ዛሬ ያንኑ ሕገመንግሥት በመጻረር በትግራይ ሕገወጥ ምርጫ እያካሄደ ይገኛል። ትላንት ማታ በETV በተላለፈው ቃለ ምልልስ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ በትግራይ የሚካሄደውን ሕገወጥ ምርጫ ከጨረቃ ቤት ሥራ ጋር እንደሚያመሳስሉት ገለጹ። ጠያቂው “በትግራይ ክልል የሚካሄደውን ክልላዊ ምርጫ እንዴት ይመለከቱታል?” ብሎ ለጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ላቀረበላቸው ጥያቄ "የትግራይን (የዛሬ) ምርጫ እንደ ጨረቃ ቤት ነው የምመለከተው፤ እዚያ ያለው ኃይል ጭንቅላቱ ደርቋል፤ ኪሱ ሲደርቅ ይጠፋል። እኛ የትግራይ ሕዝብን በልማት እንደግፋለን እንጂ ጦር አናዘምተበትም" ብለዋል። "የትግራይ ምርጫ የጨረቃ ምርጫ ነው! … [Read more...] about ህወሓት “ጭንቅላቱ ደርቋል” – ጠ/ሚ/ር ዐቢይ