
ከትግራይ ክልል ጋር በተያያዘ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በክልሉ የሚገኙ የካቢኔ አባላት ህጋዊ ባልሆነ ምርጫ ተመርጠናል በሚል የሀገሪቱን ህገ መንግሥት በመጣሳቸው አሁን ባለው ሁኔታ የገንዘብ ሚኒስቴር ለትግራይ ክልል መንግሥት በጀት እንደማይለቅ የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ተናገሩ።
በትግራይ ክልል ለሚገኙ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት በወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮች በኩል በተጠና ሁኔታ እንዲደርሳቸው ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝም ጠቅሰዋል።
ይህ ለሁለተኛው ሩብ ዓመት (ጥቅምት-ህዳር-ታህሣሥ) ከፌዴራል ለክልሎች የሚለቀቅ በጀት እንደሆነ ይታወቃል።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
ገና TPLF ከኣሽዓነት ወደ ህወሓትነት የሽግግር ስዓታት ላይ በምትገኝበት ጊዝያቶች ላይ የዓድዋን ገጠሮችንና እንዲሁም እንደነ እንትጮ አይነት ትናንሽ ወደ ከተማነትን የሚከጅላቸው ቦታዎች ዘንዳ እጅን አሸልኮ ንብረትን ስቦ ወደኪስ የማግባት መንገዶች በነበሯት ስዓታት ላይ፣ ደርግ ለነይሓ ከተማ ልሁን ባዮች አይነቶች ቦታዎችን እንትጮ ውስጥ እህል ማከፋፈያ ካምፕ አቁሞ ለህዝበ ገጠር ዓድዋ፣ እንትጮ ሄዳችሁ እህል ውሰዱ ይላል:: ከኣሽዓነት ወደ ህወሓትነት ሽግግር ስዓታት ላይ የምትገኘዋ ወያነም፣ የደርግ የእህል ማከፋፈያ ካምፕ ውስጥ፣ ውስጥ ውስጡን በመለመለቻቸው ተባባሪ ካድሬዎችዋ በኩል አድርጋ ከካምፑ ከፍተኛውን የእህል ክፋል ወደ ራስዋው መሳብን ታበዛና ለተራበው ህዝብ የሚደርሰው እህል እየቀነሰ መምጣቱን የታዘቡ ይሓዎች፣ የእህል ማደያው ካምፕ ወደ ዓድዋ ከተማ እንዲዟዟርና (ዓድዋን ገና ደርግ ነበር የሚቆጣጠረው) የእንትጮ ማከፋፈያ እንደማሻቸው ይናገራሉ:: እንዲህ ብለው ሃሳብ ያቀረቡትን ሰዎች ገና አሽዓዋ TPLF በሌሊት ጭለማን ተከናንባ ወደየቤታቸው ዘልቃ ትገባና ግማሽ ሃብታቸውን፣ ድመትና ውሻም ሳይቀር ትከፍልና የቤት አባወራዎቹን እስከነ ግማሽ ንብረታቸ under hostage አስገብታ (ጠለፋ አካሂዳ) ወደ ሽረ ጉድጓድ እስር ቤቷ ኮብኩባ ትነዳና፣ ንብረታቸውን ለራስዋ ገቢ አድርጋ አባወራዎቹን ደግሞ በጭለማ ጉድጓድ እስር ቤቷ ውስጥ ፀሃይንም ሳያዩ ለሰባት ዓመታት ታስራለች:: ጤነኞችና እስከነ ጥቁር ፀጉራቸው ወደ ሽረ ጉድጓድ የተወሰዱት አባወራዎቹ ከሰባት አመታት በኋላ ከጭለማ እስር ሲለቀቁ ከግራ በኩል ሆነው ሲያነግሯቸው በቀኝ በኩል የሆነ ድምፅ ይሰማቸውና ወደ ቀኝ በኩል ዞር ብለው ምን አልከኝ የሚሉና፣ ፀጉራቸው በመላው እስከነ ቅንድባቸውም ሳይቀር ሸበቶ ብቻ ሆነው ይወጣሉ:: አባወራዎቹ እስከነ ግማሽ ሃብታቸው ከገዛ ግቢያቸው ተነድተው በሚኮበኮቡበት ጊዜ፣ ሚስቶቻቸው ንብረቴን አትውሰዱብኝ የልጆቼ ማሳደግያ ነው፣ ባለቤቴንም አትውሰዱብኝ ልጆቼን ብቻዬን ለማሳደግ ይከብደኝልና ብለው በጨለማ ስዓታት ላይ ድምፃቸውን ለማሰማት ሞክረው ነበር:: የወያነ መልስ ግን ጨከን ያለና፣ ባለቤትዎ እህል ዓድዋ ይከፋፈለን የሚል ሃጥያት ስለተናገሩ ይታሰራሉ፣ ከንብረታችሁም የእርሳቸውን ከፊል ግማሹ ንብረታችሁ ይወረሳል፣ ስለሆነም አሁን አፍዎን ይያዙ የሚለውን ቃል ወርውረውባቸ ባሎችንና ግማሽ ንብረትን ይዘው ሄዱ:: ታድያ አሁን “በትግራይ ክልል ለሚገኙ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት በወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮች በኩል በተጠና ሁኔታ እንዲደርሳቸው ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝም ጠቅሰዋል።” የሚለውን አረፍተ ነገር ሳይ፣ የጥንቱ ጭካኔ ትዝ አለኝና ጭካኔው አሁንም እንዳይደገም ጥናቱ እንድያውጠነጥነው ለማሳሰብ ያህል አባባላችንን ሰነዘርን እንጂ፣ ገና ጅቦች አሉ ተብሎ ጠቅላላ ህዝቡን ከሁሉም ጥቅም ላለመቁረጥ የሚደረገውን ጥረት ሳናደንቅ አናልፍም:: የተሻለ ቀን ያምጣ፣ unity in diversity!!