
የፌዴሬሽን ምክር ቤት ህወኃትን በተመለከተ ባሳለፈው ውሳኔዎች ዙሪያ ለዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡ ማብራሪያ ሰጥቷል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባዘጋጀው በዚህ መድረክ በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች እና የቆንስላ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል።
የፌዴሬሽን ምክር ቤት የትግራይ ክልል ምርጫን በሚመለከት ባሳለፈው ውሳኔ ዙሪያ የፌዴሬሽን ምክር ቤት የሕገ መንግሥት ትርጉምና የማንነት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ጸሐፊ ወርቁ አዳሙ ማብራሪያ አቅርበዋል።
በማብራሪያው በ2012ዓ.ም በኢትዮጵያ ሊደረግ የነበረው ሀገራዊ ምርጫ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም ምክር ቤቱ በሕገ መንግሥት ትርጉም ተመሥርቶ ውሳኔ ማሳለፉ ተነስቷል፤ የትግራይ ክልልን የሚመራው ፓርቲ ህወሀት ውሳኔውን ወደ ጎን በመተው ኢ-ሕገ መንግሥታዊ በሆነ መንገድ ምርጫ በማድረግ ወደ መንግሥት ምሥረታ መግባቱም ተጠቅሷል።
ህወሀት ከዚህ ድርጊቱ እንዲቆጠብ ጥረት ቢደረግም ፈቃደኛ ባለመሆኑ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ያሳለፋቸውን ውሳኔዎችን አቶ ወርቁ ለዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡ አብራርተዋል።
ህወሀት እየሄደበት ካለው ኢ- ሕገ መንግሥታዊ ጉዞው እንዲታረም በፌዴራል መንግሥት በኩል ሁሉንም ዓይነት ውይይቶችን እና ሕጋዊ መንገዶችን ተከትሎ መጠየቁን ለዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡ ማብራሪያ ተሰጥቷል። ህወሀት የሰላም እና ሕጋዊነት የተላበሱ ውይይቶችን ለመቀበል ፍቃደኛ አለመሆኑም ተጠቅሷል።
ሀገራዊ ምርጫውን በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ ለማካሄድ ሁሉም ዓይነት ዝግጅቶች እየተደረጉ እንደነበር በሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማዕከል የሕዝብና ዓለማቀፍ ግንኙነት ኃላፊ ቢቄላ ሁዴሳ (ዶክተር) አስረድተዋል።
በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የምርጫ ቦርድ ምርጫውን ማካሄድ እንደማይችል በማሳወቁ መንግሥት የወሰደውን የሕገ መንግሥት ትርጉም መፍትሔም አብራርተዋል። ምርጫው ከ9 ወር እስከ 1 ዓመት እንዲራዘም ውሳኔ ያሳለፈ መሆኑ እየታወቀ በትግራይ ክልል መንግሥት በኩል ግን ኢ-ሕገ መንግሥታዊ የሆነ ምርጫ መካሄዱን ዶ/ር ቢቂላ ገልጸዋል።
‘‘የሀገሪቱ ሕገ ሁሉ የበላይ ሕግ የሆነው ሕገ መንግሥት በሁሉም ክልሎች እኩል መከበር አለበት። ሁለቱ ምክር ቤቶች የሚያሳልፉት ውሳኔ ገዥ መሆኑ እየታወቀ ‘የትግራይ ክልል መንግሥት ያካሄደው ምርጫ ተቀባይነት የሌለው፣ የማይፀና እና ኢ-ሕገ-መንግሥታዊ ነው’ በሚል በትግራይ በኩል የተካሄደው ምርጫ ተቀባይነት የለውም’’ በሚል ውሳኔ መተላለፉን የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡ እንዲረዳም ዶ/ር ቢቂላ አብራርተዋል።
የልማት ሥራዎችን በመንግሥትም ሆነ በተለያዩ ለጋሽ አካላት ማከናወን ያልተቋረጠና የሚቀጥል መሆኑንም ለዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡ አስታውቀዋል። (ጋሻው ፋንታሁን፤ አብመድ)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
TPLF Leaders are not Law abiding group. They are not representing Tugray people and Tigray people are hostages by TPLF. Tigray people they don’t have democratic rights and they were under Dictatorships for 30 Years. Tigray people silenced by TPLF they have no choices.
TBLF is adamant to hear the very people it is claiming to serve. Worse still, it thinks the people can be human shields and save it when the final whistle is blown by the Federal Government. This will never happen as it never shared what it looted for 27 years from the country with them.