• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ህወሓት “ጭንቅላቱ ደርቋል” – ጠ/ሚ/ር ዐቢይ

September 9, 2020 05:39 am by Editor 1 Comment

ህወሓት የተሰኘው የበረሃ ወንበዴዎች ስብስብ ላለፉት ሁለት ዐሥርተ ዓመታት የኢትዮጵያ ሕዝብ እስኪደነቁር ድረስ ሕገመንግሥት መናድ እያለ ተቃዋሚዎቹን ሁሉ ሲያሸማቅቅ እንዳልኖረ ዛሬ ያንኑ ሕገመንግሥት በመጻረር በትግራይ ሕገወጥ ምርጫ እያካሄደ ይገኛል።

ትላንት ማታ በETV በተላለፈው ቃለ ምልልስ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ በትግራይ የሚካሄደውን ሕገወጥ ምርጫ ከጨረቃ ቤት ሥራ ጋር እንደሚያመሳስሉት ገለጹ። ጠያቂው “በትግራይ ክልል የሚካሄደውን ክልላዊ ምርጫ እንዴት ይመለከቱታል?” ብሎ ለጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ላቀረበላቸው ጥያቄ “የትግራይን (የዛሬ) ምርጫ እንደ ጨረቃ ቤት ነው የምመለከተው፤ እዚያ ያለው ኃይል ጭንቅላቱ ደርቋል፤ ኪሱ ሲደርቅ ይጠፋል። እኛ የትግራይ ሕዝብን በልማት እንደግፋለን እንጂ ጦር አናዘምተበትም” ብለዋል።

“የትግራይ ምርጫ የጨረቃ ምርጫ ነው! ኮሽ ባለ ቁጥር ይደነግጣሉ! ሲኖትራክ ሲያልፍ ዶዘር መጣ ሊያፈርሰን ነው ብለው ይፈራሉ ሕጋዊ ምርጫ አይደለም።

“የሚሊሻ ብዛት አሳሳቢ አይደለም አሁን ትግራይ የሚያስፈልጋት ጦርነት ሳይሆን ውሃ ነው፣ የህወሓት የቁራ ጩኸት አሳሳቢ አይደለም፣ እኔ ለትግራይ የፊት ማስክ እንጂ ጥይት አልክም” ብለዋል።

ሲቀጥሉም “የጨረቃ ቤት ካርታ አንደሌለው ሁሉ ይሄም ምርጫ ሕጋዊ ያልሆነ ምርጫ ቦርድ የማያውቀው ነው”። … አገራዊው ምርጫ ሲካሂድ እዚያ ያለው ቡድን ካልተሳተፈ ፓርላማ መቀመጫ አይኖረውም። ለዚህ ብለን ጦርነት አንከፍተም። ለትግራይ ሕዝብ ኮሮናን አንዲከላከል አፍ መሸፈኛን እንሰጣለን አንጂ፣ ውሃን እናስገባለን፣ እድገትን እናመጣለን እንጂ የሆኑ ቡድኖችን ለመዋጋት ጦርነት አንከፍትም ። እዛ ያለው ሀይል ጭንቅላቱ ደርቋል። ኪሱ ሲደርቅ ይጠፋል። በድሮ በሞተ ሀሳብ የሚንቀሳቀስ ነው” ብለዋል።

ሙሉው ቃለ ምልልስ እዚህ ላይ ይገኛል።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: Interviews, News, Right Column Tagged With: tigray tplf election, tplf, tplf fake election

Reader Interactions

Comments

  1. Tesfa says

    September 10, 2020 02:15 pm at 2:15 pm

    አይ ምርጫ። አሁን ማን ይሙት በትግራይ ከወያኔ ውጭ ሰው መርጦ ቆሞ ይሄዳል? እንኳን አሁን አሰራራቸው ስር ሰዶ ይቅርና ድሮም በረሃ እያሉ ደንበር ገተር ሲሉ ፍትሃዊ ምርጫ ጭራሽ አድርገው አያውቁም። ሰው እንዴት ልብ ማለት አይችልም። ለትግራይ ህዝብ የሚያስቡ፤ ለኢትዮጵያ አንድነት የቆሙ የትግራይ ልጆች እኮ በደርግ ጥይት ሳይሆን በወያኔ ሴራ ነው አፈር የተመለሰባቸው። ግን ሆድ አምላካቸው ለሆነ፤ እኔ ከኖርኩ ሌላው ገደል ይግባ ለሚሉ ጭፍን የፓለቲካና የዘር አምላኪዎች ወያኔ ሰማያዊ እይታ አለው። በእነርሱ መስፈረት ወያኔ ለትግራይ ህዝብ ሲል ራሱን ጦም አሳድሮ በረሃ ለበረሃ የተንከራተተ ነው። ይህ ሁሉ ውሸት ነው። የሞተው የድሃው ልጅ። ዛሬም ና ታጠቅ የሚባለው የደሃው ገበሬ ልጅ ነው። የእነርሱ ልጆችና ቤተሰቦች በቻይና በአውሮፓ በአሜሪካ በተዘረፈ ሃብት ተንደላቀው ይኖራሉ። በሃገር የቀሩትም በተዘረፈ ሃብትና ንብረት ዘምነው ይንደላቀቃሉ። የትግራይ ልጆች ደም ለወያኔ የመነገጃ ብልሃት ነው።
    እኔ የሚገርመኝ ግን ሰው በኮሮና ቫይረስ እየተፈተነ፤ የአዲስ አመት መለወጫ ቀን በራፍ ላይ ቆሞ ሰውን የግድ ውጡና ምረጡ እያሉ ማጎሳቆል ለትግራይ ህዝብ ማሰብ ነው? በጭራሽ። የአቶ ስብሃት ነጋ ፓለቲካ መግደልና ማሰር፤ ማስፈራራትና የቆመን ማፍረስ በመሆኑ ህዝባችን በአዲስ ዓመት ዋዜማ እንኳን እፎይ ብሎ ከቤተሰቡ ጋር ያለውን እንዳይቀምስ ወያኔ በምርጫ ሰበብ ያዋክበዋል። ራሱ ወያኔ ያረቀቀውን የህገ መንግሥት ደንብ የሚጥስ እንዲህ ያለ ዘንዶ በኢትዮጵያ የፓለቲካ ታሪክ ውስጥ በቅሎ አያውቅም። ችግሩ እነርሱ የፈጠሩት የዘር ፓለቲካ ሃገሪቱን ከከፋ ደረጃ ላይ እያደረሳት መሆኑ ያሳዝናል። የአምልኮ ቤቶችን ዘግቶ፤ ቄሳውስትን ማሰር የጣሊያኑ ሞሶሎኒ ከሰራው ልዪነቱ ምንድን ነው? እንዴት ብለው ነው የትግራይ ልጆች ወያኔን የሚደግፉት? ተገደው/ፍርፋሪ ለቃሚ ሆነው/ወይስ እኔ ምን ቸገረኝ በሚሊ ግዴለሽነት? ግራ ያጋባል። አዲስ አበባ ላይ በትረ መንግስቱን ይዘው አራጊ ፈጣሪ በነበሩ ጊዜ ዞር ብለው ያላዪት የትግራይ ህዝብ አሁን ከስልጣን ሲሽቀነጠሩ አለንልህ ማለታቸው መደበቂያ ፍለጋ እንጂ ለትግራይ ህዝብ ደህንነት እና ሰላም ደንታ አይሰጣቸውም። የወያኔ ቋንቋ ትግርኛ አይደለም። ጦርነት እንጂ! ለመኖር እሳት ማንደድ፤ ክራር እየከረከሩና ቀረርቶ እያሰሙ መጡባቹሁ እያሉ የትግራይን ሰፊ ህዝብ ማዋከብ ነው። የትላንትም የፓለቲካ ታሪካቸው ይህ ነበር፤ አሁንም የሚጠቀሙበት የስልጣን መቆያ ብልሃታቸው ማምታት ነው። ጌታቸው ረዳ ከፓለቲከኞች ሁሉ ሙት ነው። የሚናገረውን እንኳን አያውቅም። ለመሆኑ ሰውና ሰውን በማናከስ እንዴት ሰላም ማምጣት ይቻላል? አሁን ማን ይሙት አቶ ኢሳያስ የትግራይን ህዝብ ሊያጠቁ ተነስተዋል? የውሸት ቱልቱላ ማለት ይሄ ነው። እኔ ሳየው የኤርትራው መሪ በዘመናቸው ማለቂያ ልብ ለመግዛት የከጀሉ፤ ጦርነትን የተጸየፉ ሆነው ነው የማያቸው። ግን ወያኔ ዛሬም የጦርነት ታምቡር እየመታ ለመሆኑ ወያኔ አፍቃሪ ድህረ ገጾችንና የወያኔን የቴሌቪዥንና የሬዲዪ ጣቢያዎችን ማዳመጥ በቂ ነው።
    ጠ/ሚ አብይ የወያኔን ተንኮል ጠንቅቆ ያውቀዋል። ያው ከወያኔ የፓለቲካ ጥምር ኮሮጆ አፈትልኮ የወጣ በመሆኑ። ግን ወያኔ ሰው ለመግደል፤ ሃገር ለማተራመስና ለመሸጥ ተኝቶ አያውቅም። ራሱ ባንዳ ሆኖ እያለ ተው ልብ ግዙ የትግራይ ህዝብ በእናንተ ተጨቆነ የሚሉ የትግራይና ሌሎች ኢትዮጵያዊያንና/ዊትን ድምጾችን ባንዳ እያለ የሚጠራ የማያፍር ወራዳ ድርጅት ነው። በእኔ እይታ ምንም አይነት ትንኮሳ ወያኔ ቢሞክርም ትግራይ ውስጥ ጦርነት አያስፈልግም። ራሱ ህዝቡ በጊዜው ሆ ብሎ በመነሳት አይቀጡ ቅጣት እንደሚሰጣቸው እርግጠኛ ነኝ። ያኔ ወያኔን አያርገኝ። ችሎ ችሎ የተነሳ ህዝብ የሚያቆመው ምንም ሃይል አይኖርም። መኖርና መሞቱ ልዪነት የለውምና! የወያኔ ምርጫ ፌዝ እንጂ ለትግራይ ህዝብና ለሃገራችን የሚያክለው ብጣቂ ነገር አይኖርም። ግን እኮ እንዴት ሰው ህይወቱን ሙሉ የፓለቲካ የፈጠራ ገድል እንደተጫወተ አለምን ይሰናበታል? የምችለው ሰጠኝ አለ ሸክም የጨነቅው። አታድርስ ነው። በቃኝ!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
Copyright © 2026 · Goolgule