በህገወጥ መንገድ የተቋቋመ ነው ላለው የትግራይ ክልል ምክር ቤት እና ካቢኔ የፌዴራል መንግሥት የበጀት ድጎማ እንደማያደርግ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አስታወቀ፡፡
የክልሉ ምክር ቤት እና ከፍተኛው የህግ አስፈፃሚ አካል (ካቢኔ) ህገመንግሥታዊ ቅቡልነት የላቸውም ያለው ምክር ቤቱ ሁሉም የፌዴራል ተቋማት ምንም ዓይነት ህጋዊ ግንኙነት ማድረግ እንደማይችሉ ገልጿል፡፡
ተቋማቱ የክልሉን ከፍተኛ ስራ አስፈፃሚ አካላት እንደ ህጋዊ አካል በመቁጠር ደብዳቤ መፃፃፍ፣ መረጃ መላላክ፣ ድጋፎች ማድረግ፣ በፌዴራል ደረጃ በሚካሄዱ መድረኮች ላይ ማሳተፍ እንደማይችሉም ነው የምክር ቤቱ አፈ-ጉባዔ አቶ አደም ፋራህ የተናገሩት፡፡
በአንጻሩ የክልሉ ህዝብ መሰረታዊ የልማትና የአገልግሎት ተጠቃሚነቱ እንዳይስተጓጎል እንደ ቀበሌ፣ ወረዳ፣ ከተማ ካሉ ህጋዊ የክልሉ መዋቅሮች ጋር ብቻ ግንኙነት እንደሚደረግ እና ይህም በሚዋቀር ኮሚቴ ክትትል እንደሚደረግ አፈ-ጉባዔው በተለይ ለኢቲቪ አስታውቀዋል፡፡
ከዚህ ውሳኔ ሊደረስ የቻለው የትግራይ ክልል መንግሥትና ገዥው ፓርቲ ህውሃት የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔን ባከበረ መልኩ የሥራ ዘመኑ በምክር ቤቱ ውሳኔ የተራዘመውን የክልሉን ምክር ቤት የህግ አስፈፃሚ አካል ወደ ቦታው መመለስ ስላልቻሉ ነው ብለዋል አፈ ጉባኤው፡፡
ውሳኔው የትግራይ ህዝብ ኢ-ህገመንግሥታዊ አካሄድ እየተከተለ ባለ ቡድን ምክንያት ከሰላም፣ ልማትና መሰረታዊ አገልግሎት አንፃር እንዳይጎዳና የትግራይ ህዝብ እንደሌሎች የአገራችን ህዝቦች መሰረታዊ የልማትና የደህንነት አገልግሎቶች እንዲያገኙ ታስቦ መተላለፉንም አመልክተዋል፡፡
“ይሄ ሊሆን የቻለው ለትግራይ ህዝብ ካለን ክብር ነው” ያሉት አቶ አደም “ህዝብም እንደ ሌሎች የአገራችን ህዝቦች ሊያገኘው የሚገባውን ጥቅም ሊከበርለት ይገባል ከሚል ጽኑ እምነት የመነጨ ነው” ሲሉም ተናግረዋል፡፡
የውሳኔ አፈፃፀምም የሚኒስትሮች ምክር ቤት ጥናት ላይ ተመስርቶ የሚከናወን ይሆናል ተብሏል፡፡
በቀጣይ በክልሉ ካሉ የከተማ አስተዳደሮች፣ ወረዳዎችና ቀበሌዎች ጋር ስለሚኖረው ግንኙነት በተለይ ህዝቡ ማግኘት የሚገባውን መሰረታዊ አገልግሎቶች እንዲያገኝ በጥናት ተመስርቶ ተፈፃሚ ይደረጋልም ተብሏል፡፡
በወረርሽኙ ምክንያት የ6ኛውን ሃገራዊ ምርጫ መራዘም በመቃወም የራሱን ክልላዊ ምርጫ ያደረገው የትግራይ ክልል ህገ መንግሥቱን በብቸኝነት እንዳከበረ በመግለጽ ከመስከረም 25 በኋላ የፌዴራሉ መንግስት ህጋዊ የስልጣን ዘመን እንደሚያበቃ እና እውቅና የሚሰጠው የፌዴራል መንግሥት እንደማይኖር ማስታወቁ የሚታወስ ነው፡፡
ይህ የድጎማ በጀቱን የተመለከተው ውሳኔ በፌዴራሉ እና በክልሉ መንግሥት መካከል ያለውን ውጥረት ይበልጥ እንደሚያከረው ይጠበቃል፡፡ (EBC)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
GI Haile says
ሕወኣት የተካነው አዳዲስ ችግሮችን መፍጠር እንጂ ችግር መፍተት ችሎታቸው መለስ ዜናዊ ከሞተ በኋላ ራዕያቸውም አብሮ ተቀብሮሃል። ምሁራኖቻቸውም ፈፈሪዎች የውሳኔ ኣቋም የሌላቸው የጥቅም እንጅ ሕጋዊነትን የሚያከብሩ ለሠሆኑ ይህ ውጥረት የግትርነት በሕሪይ ውጤት ነው።
shiferaw berkineh says
መንግስት ትክክለኛ ውሳኔ ወስኗል።የትግራይ ህዝብ በቀበሌ በሚገኙ ሹማምንቶቹ አማካኝነት ማንኛውንም አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ።
ዘረ-ያዕቖብ says
Under Mereja:
” የ5,000 ሜትር ሪከርድን ስፔን፣ ቫሌንሽያ ላይ ከሰበረችው አትሌት ለተሰንበት ግደይ ጋር ያደረግኩት አጭር ቃለ-መጠይቅ! Elias Meseret
– በመጀመርያ እንኳን ደስ አለሽ፣ ወደ ጥያቄዬ ስገባ፣ በአንቺ ስም እና ፎቶ የተከፈተ የፌስቡክ ገፅ ብዙ መረጃዎችን እያወጣ ነው። በአንድ ግዜ የተከታዮቹ ቁጥር ከ18,000 በልጧል፣ ይህ በእርግጥ የአንቺ ነው?–
አትሌት ለተሰንበት>> እኔ ምንም አይነት የፌስቡክም ሆነ የሌላ ሶሻል ሚድያ ተጠቃሚ አይደለሁም፣ ሌላው ቀርቶ ስልክ እንኳን በአሰልጣኜ ነው የምጠቀመው፣ እንደምታውቀው አሁን እራሱ የማወራህ በሱ (ሀይሌ) ስልክ ነው። እኔ ሙሉ ትኩረቴ አትሌቲክስ ላይ ብቻ ነው። አንድ የፌስቡክ ገፅ ሰሞኑን እኔ ያላልኩትን ነገር እያወጣ እንደሆነ ሰምቻለሁ፣ አዝኛለሁም። ይህ ደስ አይልም፣ የሚፃፈው ነገር ሞራል ሊነካ ይችላል። ለህዝብ የእኔ እንዳልሆነ አሳውቅልኝ፣ ምንም የሶሻል ሚድያ አካውንት የለኝም።–
– ቦሌ ኤርፖርት ያጋጠመሽ ነገር ምን ነበር?
–አትሌት ለተሰንበት>> ያጋጠመኝ ነገር ያን ያህል ከባድ የሚባል ችግር አልነበረም፣ አሰልጣኜ (ሀይሌ) ነበር ሲያናግራቸው የነበረው። በሗላ አትሌት ደራርቱ መጥታ ችግሩ ተፈቷል፣ በቃ ይሄው ነው።
–– አሁን የ5,000 ሜትር ሪከርድ ሰብረሻል፣ ቀጣይ ውጤት ምን እንጠብቅ?–
አትሌት ለተሰንበት>> የአሁኑ ውጤት ትልቅ ብርታት ሆኖኛል ስለዚህ በቀጣይ ነገሮች ከተመቻቹ የ10,000 ሜትር ሪከርድን መስበር እፈልጋለሁ፣ እሱን ማሳካት ቀጣይ እቅዴ ነው።”
እንዴት ነው ነገሩ ሁሉ? በሰላማውያን ተጋሩ ላይም ቦሌ ላይ ልዩነት ተጀመረ እንዴ? “ዘመንያ ግርምቢጥስ ማይ ንዓቐብ” እንዳይሆን አደራ…!
Worqu Belayeneh says
This should be only the first step. Others should follow, such as: (a) cut-off of fuel supply, (b) cut-off of foreign exchange to banks serving TPLF conglomerates, (c) selectively cutting electricity and telephone/Internet services, (d) going after EFORT to pay loans that were forgiven/written off when TPLF was in control, (e) confiscating properties in Addis Abeba that do not have registered/legal owners but most probably owned by TPLF and associates.