የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በሲሲቲቪ እና በድሮን የታገዘ የጸጥታ ጥበቃ ስራዎችን ሊያከናውን መሆኑን አስታወቀ። ኮሚሽኑ ለህዝብ ጥያቄ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት የሚስያችሉ ቴክኖሎጂዎችን ሊጠቀም መሆኑን አስታውቋል። ኮሚሽኑ ለህዝብ ጥያቄ ፈጣን ምላሽና አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን ማሟላት ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫው መሆኑን አስታውቋል። የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ጀይላን አብዲ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት የወንጀል መከላከል ስራን በሲሲ ቲቪ ካሜራ የተደገፈ እንዲሆን ማድረግ፣ ዘመናዊ የመገናኛ ራዲዮችን መጠቀም እንዲሁም ለወንጀል ምርመራ የሚስያፈልጉ በተለይ ለፎረንሲክ ምርመራ የሚውሉ ቴክኖሎጂዎችን፣ መሳሪያዎች፣ ሶፍትዌሮችን በማሟላት አገልግሎት ላይ እንዲውሉ ለማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል። ከዚህ ቀደም ፖሊስ በሀገሪቱ የሚከናወኑ ሀገራዊ፣ … [Read more...] about ፌዴራል ፖሊስ የራሱ ሄሊኮፕተር እንዲኖረው ጠየቀ
drone
በሀገራችን የመጀመሪያዎቹ ፈቃድ ያገኙት ድሮኖች!
በኢትዮጵያዊው ወጣት ናኦል ዳባ የተሰሩ ሁለት ድሮንና (ፀረ-አረም መድሃኒት መርጫና ከርቀት ሆኖ ለማኅበረሰቡ መልክዕት ማድረስ የሚያስችሉ) አንድ የኮሮና ቫይረስ ሙቀት መለኪያ የፈጠራ ውጤቶች ይፋ ሆነዋል። ለጸረ-አረም መርጫ የሚያገለግለው ድሮን 10 ሊትር የመያዝ አቅም ያለው ሲሆን በአንድ ጊዜ 65 ሄክታር መሬት መርጨት ያስችላል። በቀጣይ በሞዴሉ እስከ 500 ሊትር የመያዝ አቅም የሚኖረው ይሆናል። የሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኮሎኔል ወሰንየለህ ሁነኛው እስካሁን በድሮውን ዘርፍ ፈቃድ የሚሰጥበት አሰራር እንዳልነበረ አውስተዋል። አሁን አሰራሩን የሚፈቅድ ህግ በመርቀቁ የፈጠራ ባለቤቱ ወጣት ናኦልና ሌሎች መስፈርቱን አሟልተው ሲገኙ ፈቃድ እንደሚሰጥ አረጋግጠዋል። (ምንጭ፤ ኢፕድ) ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about በሀገራችን የመጀመሪያዎቹ ፈቃድ ያገኙት ድሮኖች!