የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በሲሲቲቪ እና በድሮን የታገዘ የጸጥታ ጥበቃ ስራዎችን ሊያከናውን መሆኑን አስታወቀ። ኮሚሽኑ ለህዝብ ጥያቄ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት የሚስያችሉ ቴክኖሎጂዎችን ሊጠቀም መሆኑን አስታውቋል። ኮሚሽኑ ለህዝብ ጥያቄ ፈጣን ምላሽና አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን ማሟላት ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫው መሆኑን አስታውቋል። የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ጀይላን አብዲ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት የወንጀል መከላከል ስራን በሲሲ ቲቪ ካሜራ የተደገፈ እንዲሆን ማድረግ፣ ዘመናዊ የመገናኛ ራዲዮችን መጠቀም እንዲሁም ለወንጀል ምርመራ የሚስያፈልጉ በተለይ ለፎረንሲክ ምርመራ የሚውሉ ቴክኖሎጂዎችን፣ መሳሪያዎች፣ ሶፍትዌሮችን በማሟላት አገልግሎት ላይ እንዲውሉ ለማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል። ከዚህ ቀደም ፖሊስ በሀገሪቱ የሚከናወኑ ሀገራዊ፣ … [Read more...] about ፌዴራል ፖሊስ የራሱ ሄሊኮፕተር እንዲኖረው ጠየቀ