በኢትዮጵያዊው ወጣት ናኦል ዳባ የተሰሩ ሁለት ድሮንና (ፀረ-አረም መድሃኒት መርጫና ከርቀት ሆኖ ለማኅበረሰቡ መልክዕት ማድረስ የሚያስችሉ) አንድ የኮሮና ቫይረስ ሙቀት መለኪያ የፈጠራ ውጤቶች ይፋ ሆነዋል።
ለጸረ-አረም መርጫ የሚያገለግለው ድሮን 10 ሊትር የመያዝ አቅም ያለው ሲሆን በአንድ ጊዜ 65 ሄክታር መሬት መርጨት ያስችላል። በቀጣይ በሞዴሉ እስከ 500 ሊትር የመያዝ አቅም የሚኖረው ይሆናል።
የሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኮሎኔል ወሰንየለህ ሁነኛው እስካሁን በድሮውን ዘርፍ ፈቃድ የሚሰጥበት አሰራር እንዳልነበረ አውስተዋል። አሁን አሰራሩን የሚፈቅድ ህግ በመርቀቁ የፈጠራ ባለቤቱ ወጣት ናኦልና ሌሎች መስፈርቱን አሟልተው ሲገኙ ፈቃድ እንደሚሰጥ አረጋግጠዋል። (ምንጭ፤ ኢፕድ)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply