ሸኔና አልሸባብ መደምሰሳቸው የጊዜ ጉዳይ ሆነ
በፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ ግብዣ የኢፌዴሪ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ በዩጋንዳ በተከበረው 41ኛው የሰራዊት ቀን ላይ ተገኝተው በዚያው ከዩጋንዳ የጸጥታ ሃይላት ጋር በሁለቱ አገሮች ድንበሮች ዙሪያ በዝግ መክረው መምጣታቸውን ተከትሎ ኢትዮጵያና ኬንያ በድንበር አካባቢ የሚንቀሳቀሱ የሸኔንና የአልሸባብ ሃይሎችን በጋራ ለመመከት መስማማታቸውን ይፋ አደረጉ። ዜናው በርካታ ጉዳዮችን የሚያነካካ በመሆኑ የገዘፈ ሆኗል።
ምስራቅ አፍሪካን በንግድና በኢንቨስትመንት ለማቆራኘት እንዲቻል ቻይና በቀጥታ ከምታደርገው ከምታከናውነው ተግባሯ በተጨማሪ ቀጠናው የሰላም ኮሪዶር እንዲሆን አገራቱ ጸረ ሰላም ሃይሎችን በጋራ መመከት እንዲችሉ፣ አንዱ በሌላው ላይ ተቃዋሚ እንዳያደራጅ አቅዳ ልዩ ኮምቦይ መሰየሟን ማስታወቋ ይታወሳል። ከዚያም ቀደም ባለ ቀን ከኤርትራ ጋር ምጽዋን ለማልማት ሙሉ ስምምነት ማድረጓ አይዘነጋም።
ኢትዮጵያ ከኤርትራ፣ ከደቡብ ሱዳንና ጅቡቲ ጋር ያላት ግንኙነት አስተማማኝ እንደሆነ የሚናገሩ ክፍሎች በኬንያ እየተንቀሳቀሱ ያሉ፣ ከመካከል ሲጠቁ ወደዛ በመሸሽ የሚያገግሙ ሃይሎችን ለማክሰም ኢትዮጵያ ጥብቅ ስምምነት ማድረግ እንደሚገባት ሲያስታውቁ ቆይተዋል።
በቅርቡ የደቡብ ሱዳን ፈጥኖ ደረሽ የሚባለውን ሃይል የሚመሩትና የላዕላይ ምክር ቤቱ ምክትል ከሆኑት ጀነራል ጋር በመነጋገር ከሱዳን ጋር ያላውን ችግር በሰላም ለመፍታት ከስምምነት የደረሰችው ኢትዮጵያ ዛሬ ከኬንያ ጋር በይፋ በድነበር አካባቢ የሚነቅሳቀሱ ሃያላትን በጋራ ለመምታት ከስምምነት መድረሳቸውን ማወጃቸው ጉዳዩ ከሶማሌና ኦሮሚያ እንቅስቃሴ ጋር የሚገናኝ እንደሆነ ተመልክቷል።
ኢትዮጵያና ኬንያ በድንበር አካባቢ የሚንቀሳቀሱ የጥፋት ኃይሎችን በጋራ ለመመከት እንደሚሰሩ የሁለቱ አገራት የጸጥታ ዘርፍ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች መማማምታቸውን የመንግስት ሚዲያዎች አስታውቀዋል። ቀደም ሲል የኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ይህንኑ ብለው እንደነበር ይታወሳል። ዛሬ ይፋ የሆነው ዜና በድንበር በኩል ስላለው እንቅስቃሴ ያውራ እንጂ ናይሮቢ ቢሮ ያላቸውን ወገኖች አስመልክቶ ዝርዝር አላስታወቀም።
የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል፤ የኬንያ ብሔራዊ ፖሊስ አገልግሎት ኢንስፔክተር ጀነራል ሄላሪ ሙትያምባይ ከዚህ ስምምነት የደረሱትና ይህንኑ ይፋ ያደረጉት አዲስ አበባ ፌዴራል ፖሊስ ጽህፈት ቤት በጋር በሰጡት መግለጫ ነው።
በውይይታቸውም በኢትዮጵያና ኬንያ ድንበር አካባቢዎች ሰላማዊ እንቅስቀሴ ለማረጋገጥ በጋራ የሚሰሯቸውን ሥራዎች ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች መምከራቸውን፣ በተለይም ደግሞ ኢትዮጵያና ኬንያ በጸጥታው ዘርፍ ተባብሮ በመሥራት በአካባቢው የሚንቀሳቀሰውን የአሸባሪው ሸኔ እኩይ ተግባር ለማክሸፍ በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን አስታውቀዋል።
ኢንስፔክተር ጀነራል ሄላሪ ሙትያምባይ “ኢትዮጵያና ኬንያ የድንበር አካባቢዎችን ጸጥታና ሰላም ለመጠበቅ በጋራ መሥራት የሚያስችላቸው ሥምምነት ላይ ደርሰዋል” ሲሉ በጋራ መግለጫቸው ላይ በገሃድ አስታውቀዋል። አያይዘውም “የመረጃ ልውውጦችን በማሳደግና በማሻሻል በአካባቢው ያለውን ሰላም በጋራ እንጠብቃለን” ብለዋል።
ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል በበኩላቸው ኢትዮጵያና ኬንያ በድንበር አካባቢ የሚንቀሳቀሱ የጥፋት ኃይሎችን በጋራ ለመመከት መስማማታቸውን አመልክተዋል። በሁለቱ አገሮች አዋሳኝ አካባቢዎች የሸኔን እንዲሁም የአልሸባብን እንቅስቃሴ ለማስቆም የጋራ ዘመቻ እንደሚያካሂዱ ይፋ አድርገዋል። “የጋራ ዘመቻው ወይም ኦፕሬሽን ውጤታማ እንዲሆን ከአንድ ወር ባጠረ ጊዜ ኬንያ ላይ የመግባቢያ ሥምምነት እንፈራረማለን” ሲሉም ተናግረዋል።
በአካባቢው የሚንቀሳቀሰው የመከላከያ ሃይል ከትናንት በስቲያ ጀምሮ ስርነቀል ዘመቻ መጀመሩን፣ ቀደም ሲል ትኩረቱ ሁሉ ወደ ሰሜን ስለነበር ሸኔ የመስፋፋት ምልክት እንዳሳየ፣ አሁን ግን በአጭር ጊዜ ነገሮች መልካቸውን እንደሚይዙ ማስታወቃቸው ይታወሳል።
የሶማሌ ክልል ረብሻና ሁከት ለማካሄድ የሞከሩት ክፍሎች አመራሮቻቸው ዋና መኖሪያቸው ከቱርክ በተጨማሪ ኬንያ እንደሆነ በተደጋጋሚ መገለጹ ይታወሳል። ምን አልባትም ከአልሸባብ ጋር በተያያዘ በሚካሄደው ኦፕሬሽን ሊካተቱ እንደሚችሉ ይገመታል። (ETHIO12)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
gi haile says
ዘግይተዋል ዶ/ር ኣቢይ ስልጣን በያዛ በወራት ውስጥ ይህ ድርድር ቢደረግ ኖሮ እጅግ መልካም ነበር። ኣሁንም ኣልዘገየም። የሕወኣት ዓለምአቀፍ የሕገወጥ ንግድ ስር የሰደደ የምስራቅ ኣፍሪካን ድንበር የሕገወጥ መሳሪያ ንግድ፣ሕገወጥ አደንዛዥ ዕዝ ዝወውር፣ ሕገወጥ የሰው ዝውውር፣ሕገወጥ ንግድ ለ27 ኣመታት የገነባው መረብ እጅግ ከባድ ነው ለሰው ዝውውር ከኢትዮጵያ እስካ ሰሜን ኣሜሪካ፣መካከለኛ ምስራቅ፣ኣውሮፓ፣ሰውዝ ኣፍሪካ ድረስ የዘለቀ የተደራጀ የምስጥር ድርጅት ከጀርባው ግን የውስጥም የውጭም ሃይላት ሕብረት ጋር የተቀናጀ ነው። በቀላሉ የከበሩበት መንገድ ነበር።
ሕወኣት በሙስናና በማጭበርበር ታዋቂና ልምድ ያለው ስለሆነ የጠረፍ ፓሊሶች ጥንካሬ ገና አጠያያቂ ቢሆንም በደንብ የድንበር ፓሊሶች መንግስት ከከፈላቸው ችግሩ ቶሎ ይቀረፋል።
Great Job Ethiopian Leader fof doung such amazing work .
hussen says
yeh aynt hasab liberetata yigebal betam temechegn