የስሙ መነሻ ግንድ የሚመዘዘው ከላቲን ነው። “vates” ይባላል። ትርጉሙም “prophet” ነቢይ፣ ወይም Fortune teller ትንቢት አብሳሪ፣ የወደፊቱን ገላጭ እንደ ማለት ነው። ስሙንም ስያሜውንም ጠቅሶ ማብራሪያ ያኖረው ራሱ ቡድኑ ሲሆን ከስሙ ለመረዳት እንደሚቻለው “ሰማያዊ ቅባትን” ራሱ ላይ ደፍቷል። የአደባባይ የድረገጹ ስምና መገኛው vatescorp.com ነው። ምርመራና የሥጋት ቅድመ ትንተና ማድረግ ዋናው የሥራው የጀርባ አጥንት እንደሆነ የሚጠቁመው ይኸው ቡድን ከስያሜውና ለራሱ ከሰጠው የነቢይነት አክሊል ውጪ ሌላ ዝርዝር የማንነት መገለጫ ስለሌለው ጥሞናን ለሚያስቀድሙ ዜጎች ሁሉ “ማነህ ነቢዩ? እነማን ናችሁ ትንቢት አብሳሪዎቹ?” ወዘተ የሚል ጥያቄ እንዲያነሱ አስገድዷቸዋል። ይህ ግራ አጋቢነቱ ቀድሞ መነጋገሪያ የሆነበት ማኅበር፣ ቡድን፣ የመናፍስት … [Read more...] about የኅቡዕ ቡድን ሪፖርት በኅቡዕ በሚሠሩ “ኢትዮጵያውያን” – ኢትዮጵያ ላይ የተመዘዘ ሰይፍ!
Reporter
ቀሲስ በላይን ፊት አድርጎ የተሞከረው የማጭበርበር ሤራ ከሸፈ
* ሚዲያው አስቀድሞ ዝግጅት አድርጎበታል ቀሲስ በላይን ግንባር አድርጎ አፍሪካ ኅብረትን ለመዝረፍ የተወጠነው ሤራ መክሸፉ አርብ ዕለት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አለሳልሶ ይፋ አድርጎታል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃላ አቀባይ አቶ ነቢዩ ተድላ “ጉዳዩ በሕግ ያለ ነው። ዝርዝር ልንናገር አንችልም። የተሞከረው ጥቃት ግን ከሽፏል። ጉዳዩ ወደ ሌላ ደረጃ ሳያልፍ ወይም ጉዳት ሳያስከትል ለመቆጣጠር ተችሏል” ማለታቸው ጉዳዩ ሤራ መሆኑን ያመላክታል። “ከኅብረቱ ጋር ባደረግነው ቀጥተኛ ውይይት ይህ አይነት እሳቤ በተቋሙ ውስጥ እንደሌለ የተቋሙ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አረጋግጠዋል” ሲሉ በመግለጫቸው ያመለከቱት አቶ ነቢዩ ጉዳዩ ሕግ የያዘው በመሆኑ ዝርዝር ለመስጠት እንደማይችሉ ገልጸዋል። የጎልጉል የአዲስ አበባ ተባባሪ ዜናው ከተሰማበትና ሪፖርተር ጋዜጣ በአማርኛና በእንግሊዘኛ ሁለት የተለያዩ … [Read more...] about ቀሲስ በላይን ፊት አድርጎ የተሞከረው የማጭበርበር ሤራ ከሸፈ
ሪፖርተር የፓርላማ ወንበር አስልቶ የአስቸኳይ አዋጁ በፓርላማ እንዳይደገፍ አቅጣጫ አመላከተ
የትህነግ ልዩ ዓላማ እየተተገበረ ያለበትን የአማራ ክልል ቀውስ ለማስታገስ የወጣው የአስቸኳይ አዋጅ ከመጽደቁ በፊት ሪፖርተር ጋዜጣ የድምጽ ስሌት አቅርቦ የአማራ ብልጽግና ከዋናው ብልጽግና የተለየ አቋም እንዲይዝ የቢሆን ስሌትና ምኞት ያለበት ዜና አሰራጨ። አብንና ኢዜማንም ደምሯል። ምንም እንኳን በሪፖርትር ስሌትና "የቢሆንልኝ" ምልከታ የድምጽ መመጣጠን ሊፈጠር የሚችልበት አጋጣሚ ሊታሰብ እንደማይችል የገለጹ እንደሚሉት፣ የዜናው ምኞትና አቅጣጫ ትህነግ የሚከተለውን "በብሄር አስብ" የሚለውን ርዕዮት የሚያንጸባርቅና አማራ ክልል በዚህ ቀጥሎ በሁከት ሲናጥ ትህነግ የከሰራቸውን ኪሳራዎች መልሶ እንዲያገኝ ለሚያደርገው ዝግጅት መንገድ ለመጥረግ እንደሆነ አመልክተዋል። "... በሚኒስትሮች ምክር ቤት የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ምክር ቤቱ በሁለት ሦስተኛ ድምፅ ማፅደቅ … [Read more...] about ሪፖርተር የፓርላማ ወንበር አስልቶ የአስቸኳይ አዋጁ በፓርላማ እንዳይደገፍ አቅጣጫ አመላከተ