አቡነ ሉቃስ በተከሰሱበት የቅስቀሳ ወንጀል ጥፋተኛ በተባሉበት ድንጋጌ በሥድስት ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ተወሰነ። ከፈጸሙት ወንጀል አኳያ ወደ ኢትዮጵያ ተላልፈው ሊሰጡ ይችላሉ። የቅጣት ውሳኔውን የወሰነው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ ሕገ-መንግሥታዊና በሕገ-መንግሥት ሥርዓት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀል ጉዳዮች የሚመለከተው ችሎት ነው። የፍትሕ ሚኒስቴር የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጀነራል ዐቃቤ ሕግ በአቡነ ሉቃስ ላይ ከሦስት ወራት በፊት÷ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀጽ 247 (ሐ) እና አንቀጽ 258 (ሀ) ሥር እና የወንጀል ሕግ አንቀጽ 251 (ሐ) የተመላከተውን ድንጋጌ ተላልፈዋል የሚሉ ሁለት ክሶች ማቅረቡ ይታወሳል፡፡ ተከሳሹ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተ-ክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ አባል እና የምሥራቅ … [Read more...] about አቡነ ሉቃስ 6 ዓመት ተፈረደባቸው፤ ወደ ኢትዮጵያ ተላልፈው ሊሰጡ ይችላል
Religion
ቀሲስ በላይን ፊት አድርጎ የተሞከረው የማጭበርበር ሤራ ከሸፈ
* ሚዲያው አስቀድሞ ዝግጅት አድርጎበታል ቀሲስ በላይን ግንባር አድርጎ አፍሪካ ኅብረትን ለመዝረፍ የተወጠነው ሤራ መክሸፉ አርብ ዕለት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አለሳልሶ ይፋ አድርጎታል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃላ አቀባይ አቶ ነቢዩ ተድላ “ጉዳዩ በሕግ ያለ ነው። ዝርዝር ልንናገር አንችልም። የተሞከረው ጥቃት ግን ከሽፏል። ጉዳዩ ወደ ሌላ ደረጃ ሳያልፍ ወይም ጉዳት ሳያስከትል ለመቆጣጠር ተችሏል” ማለታቸው ጉዳዩ ሤራ መሆኑን ያመላክታል። “ከኅብረቱ ጋር ባደረግነው ቀጥተኛ ውይይት ይህ አይነት እሳቤ በተቋሙ ውስጥ እንደሌለ የተቋሙ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አረጋግጠዋል” ሲሉ በመግለጫቸው ያመለከቱት አቶ ነቢዩ ጉዳዩ ሕግ የያዘው በመሆኑ ዝርዝር ለመስጠት እንደማይችሉ ገልጸዋል። የጎልጉል የአዲስ አበባ ተባባሪ ዜናው ከተሰማበትና ሪፖርተር ጋዜጣ በአማርኛና በእንግሊዘኛ ሁለት የተለያዩ … [Read more...] about ቀሲስ በላይን ፊት አድርጎ የተሞከረው የማጭበርበር ሤራ ከሸፈ
ቀጣዩ የዳያስፖራ ፖለቲካና የሚዲያው አሰላለፍ
“ባለፉት 50 ዓመታት የተከሰቱት ጦርነቶች የተጀመሩት ሚዲያው ባስተጋባው ውሸት መሆኑን ደርሼበታለሁ” ጁሊያን አሳንዥ፤ የዊኪሊክስ መሥራች። የአገራችን ሚዲያ አውታሮች በተለይም የግሉ ሚዲያ የሚባሉትና በ1997 ምርጫ ወቅት የነበሩት በኢትዮጵያ ዴሞክራሲ እንዲቀጭጭ፣ የሃሳብ ልዩነት እንዳያድግ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችና አመራሮች ጉያ ሥር ገብተው የፈጸሙት ወንጀል የሚያስጠይቅ ነው። ለቀጣዩ ትውልድ መማሪያ ይሆን ዘንድ በወጉ ተጠንቶና ተሰንዶ ሊቀመጥ ይገባል። ምክንያቱም ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በተደጋጋሚ ሲከሰት ያየነው ፖለቲካው ወይም ፓርቲዎች ሚዲያውን አጀንዳ እያስያዙ ሲመሩት ይቆዩና በኋላ ፖለቲከኞቹ እርስበርስ ሽኩቻ ውስጥ ሲወድቁ የሚፈልጉትን ለማጥቃት ወይም በሐሰት ለመወንጀልና ፕሮፓጋንዳ ለመንዛት ሲሉ ለሚዲያ ባለቤቶቹ ባሪያና ተገዢ በመሆን እነርሱ ሚዲያውን መምራት ሲገባቸው … [Read more...] about ቀጣዩ የዳያስፖራ ፖለቲካና የሚዲያው አሰላለፍ
“ሙሽራው እስኪመጣ የምትቆይ ቤተክርስቲያን እናድርጋት” ጠ/ሚ/ር ዐቢይ
"የቀረው ደግሞ ወደ ትግራይ ሄደን የቀሩትን ማምጣት ነው" በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አባቶች መካከል ተፈጥሮ የነበረው አለመግባባት በንግግር እና ውይይት መፈታቱ ተገልጿል። ቤተክርስቲያኗ ያጋጠማትን ፈተና ለመፍታት የሃይማኖት አባቶቹ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የሀገር ሽማግሌዎች በጋራ ምክክር አድርገዋል። በውይይታቸውም አንድነትን የሚያፀና እና አገልግሎትን የሚያሰፋ መንገድ መከተል ተገቢ መሆኑን በማመን ከስምምነት መደረሱን የሃይማኖት አባቶች ባወጡት መግለጫ ገልጸዋል። ከቋንቋ ጋር በተገናኘ የሚነሡ ሐሳቦችን ለመመለስ ቤተክርስቲያን የጀመረችውን ሥራ አጠናክራ እንድትቀጥል ከመግባባት ላይ የተደረሰ ሲሆን በበጀት እና በሰው ኃይል ማጠናከር ትኩረት ተሰጥቶታል። በአፋን ኦሮሞ ቋንቋ እምነትን ለማጠናከር የሚያስችሉ ማሰልጠኛ ኮሌጅ እና … [Read more...] about “ሙሽራው እስኪመጣ የምትቆይ ቤተክርስቲያን እናድርጋት” ጠ/ሚ/ር ዐቢይ
በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ በማኅበራዊ የትሥሥር ገጻቸው ይህንን ጽፈዋል። ዛሬ በአቡዳቢ በመሠራት ላይ ያለውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጎብኝቻለሁ። 17682 ካሬ ሜትር መሬት ከተባበሩት ዓረብ ኤምሬት መንግሥት ተሰጥቶናል። ለዚህም በኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ስም አመሰግናቸዋለሁ። ለጊዜው መገልገያ የሚሆነው ቤተ ክርስቲያን እየተጠናቀቀ ነው። የጥምቀት በዓል በቦታው እንዲከበር የሚቻለው ሁሉ እንደሚደረግ ከሚመለከታቸው የሥራ ኃላፊዎች ቃል ተገብቶልናል። ይሄንን መሰል ቦታዎች የታሪክና የዲፕሎማሲያችን ትእምርቶች ናቸው። እነርሱ ለእኛ ይሄንን ሲያደርጉ፣ አኛ ለገዛ ወገኖቻችን ከዚህ በላይ እንድናደርግ ትምሀርት ይሆነናል። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
ባለፉት ሦስት ወራት የተያዘ ህገ ወጥ ሲሚንቶና ነዳጅ
በመጀመሪያው ሩብ ዓመት በህገ ወጥ መልኩ ሲዘዋወር የነበረ ከ71 ሺህ ኩንታል በላይ ሲሚንቶ እና 500,153 ሊትር ነዳጅ ተይዟል። በዚህም መሰረት፦- በአዲስ አበባ 54,976 ኩንታል ሲሚንቶ- በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት 14,094 ኩንታል ሲሚንቶ፣ እና 49,520 ሊትር ነዳጅ- በአማራ ክልላዊ መንግስት 1,914 ኩንታል እና 39,8505 ሊትር ነዳጅ- በሶማሌ ክልላዊ መንግስት 530 ኩንታል እና 12,560 ሊትር ነዳጅ- በደቡብ ምዕራብ 39,568 ሊትር ነዳጅ በድምሩ 71,514 ኩንታል ሲሚንቶ እና 500,153 ሊትር ነዳጅ በህገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር ተገኘቶ በህገ ወጥ አካላት ላይም አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስዶባቸዋል፡፡ በዚህ ህገ-ወጥ ድርጊት ላይ ተሳተፎ ባደረጉ አካላት ላይ ድርጅት የማሸግ እንዲሁም ምርት የመውረስ … [Read more...] about ባለፉት ሦስት ወራት የተያዘ ህገ ወጥ ሲሚንቶና ነዳጅ
“ትህነግን ለማጥፋት የሚደረግ ማንኛውም ነገር ቅዱስ ነው”
የትህነግ 10 በደሎች - በተለይ በአማራ ሕዝብ! "ትህነግ"... (ትግራይ/ተጋሩ አላልሁም) የተሸነፈው በ1967 ነው። ማንም ቡድን ወይም ርዕዮተ አለም ሕዝብን ጠላት አድርጎ ማሸነፍ አይችልም። ግለሰቦች፣ የፊውዳሉ ስርዓት ጠላት ሊሆን ይችላል። ሁሉም አማራ ግን ጠላት ሊሆን አይችልም። ትህነግ እንጂ የትግራይ ሕዝብ ጠላት እንዳልሆነው ሁሉ። የትህነግ መሠረታዊ ትርክት (ድርሰት) በገሃድ የተተወነው ባለፈው ዓመት ነው። ትህነግ በተለይ በአማራ ሕዝብ 10 ዐበይት በደሎች ፈፅሟል። በእኔ ሚዛንና ምልከታ። 1) መልክዓምድራዊ ለውጥ (Demographic Change): ድህረ 1983 ማንነትን ባላገናዘበ መልኩ ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ዋግና ራያ ላይ መሬቱን በመውረር ሰዎችን አፈናቅሎል፣ ጅምላ ግድያ ፈፅሟል። ሴቶችን በመድፈርና አስገድዶ በማግባት የዲሞግራፊ … [Read more...] about “ትህነግን ለማጥፋት የሚደረግ ማንኛውም ነገር ቅዱስ ነው”
ሙስሊምና ክርስቲያን በአንድነት የሚያከብረው የአኾላሌ ባሕላዊ ጭፈራ
በሴቶች ጭፈራ ደምቆ በወንዶች የሚታጀበው የአኾላሌ ባሕላዊ ጭፈራን ለማስተዋወቅ የሁለት ቀን ፌስቲቫል በደሴ ከተማ ተካሂዷል። እራሷን ተሰርታ ወለባ ስጋለች፣ እንሶስላ ሙቃ ሎሚ ጨብጣለች፣ ያች ያገሬ ልጅ እሷዉ ትሆናለች። ሲሉ ጨዋታውን ደመቅ ያደርጉታል የወሎ ወይዛዝርት። ታዲያ በዚህ ጭፈራ ጊዜ ወንዶቹ ሴቶቹን ተቀላቅለው ጭፈራውን ደመቅ ያደርጉታል። አኾላሌ በሃይማኖታዊና ሃይማኖታዊ ባልሆኑ ክብረ በዓላት የሚከናወን ብዙ ጊዜ ጥር ወር ላይ በአርሶ አደሩ የዕረፍት ወቅት፣ በመተጫጫና ጋብቻ እንዲሁም የመዋቢያ ጊዜ የሚከናወን ባህላዊ ጨዋታ ነው። በአብዛኛው በወሎ በተለይም በተውለደሬ የሚከወነው ተዉኔት አዘል ባህላዊ የወጣቶች ጭፈራ ሃይማኖት ሳይለይ በክርስትናም በእስልምና ተከታዮችም ይካሄዳል። አሆላሌ ባህላዊ ጨዋታ የራሱ የኾነ የመከወኛ አጋጣሚዎች እና ወቅቶችም … [Read more...] about ሙስሊምና ክርስቲያን በአንድነት የሚያከብረው የአኾላሌ ባሕላዊ ጭፈራ
“ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ተቀራርበን እንሠራለን” የከተማ አስተዳደሩና ቤተክርስቲያኗ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በዛሬው ዕለት ውይይት አድርገዋል። ከውይይታቸው በኋላም የጋራ መግለጫ ሰጥተዋል። የመግለጫው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል። ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ እና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጋራ የተሰጠ መግለጫ በዛሬው እለት የካቲት 8 ቀን 2014 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች በመስቀል አደባባይና በጃንሜዳ ባህረ ጥምቀት ቦታዎች በቀረቡ ጥያቄዎች ላይ የጋራ ውይይት አድርገናል፡፡ ውይይቱ በፍጹም ቅን ልቡና፣ መደማመጥና መግባባት በተሞላበት ስሜት ተካሂዷል፡፡ በመሆኑም በውይይቱ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመስቀል አደባባይና … [Read more...] about “ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ተቀራርበን እንሠራለን” የከተማ አስተዳደሩና ቤተክርስቲያኗ
የዛሬ ዓመት በማይካድራ በተፈጸመው የዘር ጭፍጨፋ
• አንድ ሺ 564 ሰዎች በጭካኔ ተገድለዋል። • 81 ሰዎች ከፍተኛ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል። • ድርጊቱን የፈጸመው አሸባሪው ሕወሓት ያደራጀው ሳምሪ የሚባል ገዳይ ቡድን ነው። የዛሬ ዓመት በማይካድራ በተፈጸመው የዘር ጭፍጨፋ አንድ ሺ 564 ሰዎች በጭካኔ መገደላቸውን፤ 81 ሰዎች ከፍተኛ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑን ድርጊቱን የፈጸመው አሸባሪው ሕወሓት ያደራጀው ሳምሪ የሚባል ገዳይ ቡድን መሆኑን በጎንደር ዩኒቨርሲቲ መምህርና ወልቃይት፣ ጠገዴና ጠለምት የጥናት ቡድን መሪ ገለጹ። የጥናት ቡድኑ መሪ አቶ ጌታ አስራደ አለማየሁ በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የዛሬ አመት በማይካድራ ጭፍጨፋውን ያካሄዱት ሳምሪ የተባለ አሸባሪው ሕወሓት ያደራጃቸው ገዳይ ቡድን ነው። ይህ ቡድን አንድ ሺ 564 ሰዎችን መጥረቢያ፣ ቆንጨራና፣ ቢለዋ፣ ማጭድና መሰል … [Read more...] about የዛሬ ዓመት በማይካድራ በተፈጸመው የዘር ጭፍጨፋ