"የቀረው ደግሞ ወደ ትግራይ ሄደን የቀሩትን ማምጣት ነው" በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አባቶች መካከል ተፈጥሮ የነበረው አለመግባባት በንግግር እና ውይይት መፈታቱ ተገልጿል። ቤተክርስቲያኗ ያጋጠማትን ፈተና ለመፍታት የሃይማኖት አባቶቹ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የሀገር ሽማግሌዎች በጋራ ምክክር አድርገዋል። በውይይታቸውም አንድነትን የሚያፀና እና አገልግሎትን የሚያሰፋ መንገድ መከተል ተገቢ መሆኑን በማመን ከስምምነት መደረሱን የሃይማኖት አባቶች ባወጡት መግለጫ ገልጸዋል። ከቋንቋ ጋር በተገናኘ የሚነሡ ሐሳቦችን ለመመለስ ቤተክርስቲያን የጀመረችውን ሥራ አጠናክራ እንድትቀጥል ከመግባባት ላይ የተደረሰ ሲሆን በበጀት እና በሰው ኃይል ማጠናከር ትኩረት ተሰጥቶታል። በአፋን ኦሮሞ ቋንቋ እምነትን ለማጠናከር የሚያስችሉ ማሰልጠኛ ኮሌጅ እና … [Read more...] about “ሙሽራው እስኪመጣ የምትቆይ ቤተክርስቲያን እናድርጋት” ጠ/ሚ/ር ዐቢይ
Abune Mathias
ውዝግቡን በሐዋሪያት መንገድ ለመፍታት ስምምነት ላይ ተደርሷል
በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የተፈጠረውን መከፋፈልና ችግር በሐሃዋሪያት መንገድ መፍትሄ እንዲፈለግለት ወደ ስምምነት መደረሱ ተሰማ። ይህ የተሰማው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከሲኖዶስ አመራሮች ጋር መወያየት መጀመራቸውን ተከትሎ ነው። የቤተክርስቲያኗ አባቶች ዛሬ ረፋዱ ላይ ከመንግሥት ከፍተኛ አመራሮችና ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር በቤተመንግሥት እየመከሩ ነው። ለስብሰባው ቅርብ የሆኑ ክፍሎችን ጠቅሰው ለአዲስ አበባ ተባባሪ ዘጋቢያችን ፍንጭ የሰጡ እንዳሉት፣ ችግሩን ከጣልቃ ገቦች አሳብ ነጥሎ በሐዋሪያት አግባብ ለመፍታት የመስማማት ፍንጭ አለ። በቡራኬ የተጀመረው ውይይት ላይ ሽምግልናውን ከሚመሩት ወገኖችና ከአባቶቹ መካከል አሳብ ሲሰጡ ያለቀሱ እንዳሉና ግልጽ ውይይት እየተደረገ መሆኑን፣ ዕረፍት ላይ ከመጀመሪያው የተለየ ስሜት መታየቱንም እነዚሁ ክፍሎች አስታውቀዋል። … [Read more...] about ውዝግቡን በሐዋሪያት መንገድ ለመፍታት ስምምነት ላይ ተደርሷል
“ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ተቀራርበን እንሠራለን” የከተማ አስተዳደሩና ቤተክርስቲያኗ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በዛሬው ዕለት ውይይት አድርገዋል። ከውይይታቸው በኋላም የጋራ መግለጫ ሰጥተዋል። የመግለጫው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል። ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ እና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጋራ የተሰጠ መግለጫ በዛሬው እለት የካቲት 8 ቀን 2014 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች በመስቀል አደባባይና በጃንሜዳ ባህረ ጥምቀት ቦታዎች በቀረቡ ጥያቄዎች ላይ የጋራ ውይይት አድርገናል፡፡ ውይይቱ በፍጹም ቅን ልቡና፣ መደማመጥና መግባባት በተሞላበት ስሜት ተካሂዷል፡፡ በመሆኑም በውይይቱ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመስቀል አደባባይና … [Read more...] about “ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ተቀራርበን እንሠራለን” የከተማ አስተዳደሩና ቤተክርስቲያኗ