አቡነ ሉቃስ በተከሰሱበት የቅስቀሳ ወንጀል ጥፋተኛ በተባሉበት ድንጋጌ በሥድስት ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ተወሰነ። ከፈጸሙት ወንጀል አኳያ ወደ ኢትዮጵያ ተላልፈው ሊሰጡ ይችላሉ። የቅጣት ውሳኔውን የወሰነው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ ሕገ-መንግሥታዊና በሕገ-መንግሥት ሥርዓት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀል ጉዳዮች የሚመለከተው ችሎት ነው። የፍትሕ ሚኒስቴር የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጀነራል ዐቃቤ ሕግ በአቡነ ሉቃስ ላይ ከሦስት ወራት በፊት÷ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀጽ 247 (ሐ) እና አንቀጽ 258 (ሀ) ሥር እና የወንጀል ሕግ አንቀጽ 251 (ሐ) የተመላከተውን ድንጋጌ ተላልፈዋል የሚሉ ሁለት ክሶች ማቅረቡ ይታወሳል፡፡ ተከሳሹ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተ-ክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ አባል እና የምሥራቅ … [Read more...] about አቡነ ሉቃስ 6 ዓመት ተፈረደባቸው፤ ወደ ኢትዮጵያ ተላልፈው ሊሰጡ ይችላል
EOTC
ቀሲስ በላይን ፊት አድርጎ የተሞከረው የማጭበርበር ሤራ ከሸፈ
* ሚዲያው አስቀድሞ ዝግጅት አድርጎበታል ቀሲስ በላይን ግንባር አድርጎ አፍሪካ ኅብረትን ለመዝረፍ የተወጠነው ሤራ መክሸፉ አርብ ዕለት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አለሳልሶ ይፋ አድርጎታል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃላ አቀባይ አቶ ነቢዩ ተድላ “ጉዳዩ በሕግ ያለ ነው። ዝርዝር ልንናገር አንችልም። የተሞከረው ጥቃት ግን ከሽፏል። ጉዳዩ ወደ ሌላ ደረጃ ሳያልፍ ወይም ጉዳት ሳያስከትል ለመቆጣጠር ተችሏል” ማለታቸው ጉዳዩ ሤራ መሆኑን ያመላክታል። “ከኅብረቱ ጋር ባደረግነው ቀጥተኛ ውይይት ይህ አይነት እሳቤ በተቋሙ ውስጥ እንደሌለ የተቋሙ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አረጋግጠዋል” ሲሉ በመግለጫቸው ያመለከቱት አቶ ነቢዩ ጉዳዩ ሕግ የያዘው በመሆኑ ዝርዝር ለመስጠት እንደማይችሉ ገልጸዋል። የጎልጉል የአዲስ አበባ ተባባሪ ዜናው ከተሰማበትና ሪፖርተር ጋዜጣ በአማርኛና በእንግሊዘኛ ሁለት የተለያዩ … [Read more...] about ቀሲስ በላይን ፊት አድርጎ የተሞከረው የማጭበርበር ሤራ ከሸፈ
አወዛጋቢው የአቡነ ጴጥሮስ የጉዞ ሰነድ
የአሜሪካንን ዜግነት ለመውሰድ ቀኝ እጅን ወደ ላይ ቀስሮ መማል ግድ ነው። እከሌ ከገሌ ሳይባል “ቀደም ሲል የነበረኝን ዜግነት እክዳለሁ” በማለት የሚከናወነው ምህላ “እግዚአብሔር ይርዳኝ” በሚል ማሳረጊያ ይቋጫል። “ቀደም ሲል የነበረኝን ዜግነቴን፣ የማንኛውንም የልዑል፣ የግዛት፣ የአገር፣ ወይም የሉዓላዊ መንግሥት ተገዢነቴን በሙሉና በፍጹም መካዴን በምሕላ አውጃለሁ" በሚል የሚከናወነው የመሐላ አሰጣጥ፣ ምሕላውን በፍጹምና ያለምንም ማወላዳት መቅበልን የሚጠይቅ ሲሆን ይህንንም ቀኝ እጅ በማውጣት የሚከናወን ሥርዓት ነው። Oath"I hereby declare, on oath, that I absolutely and entirely renounce and abjure all allegiance and fidelity to any foreign prince, potentate, state, or … [Read more...] about አወዛጋቢው የአቡነ ጴጥሮስ የጉዞ ሰነድ
“ዐቢይን ግንባሩን ብለህ ዳዊት ሁን” ያሉት አቡነ ሉቃስ ክስ ተመሰረተባቸው
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይን እንደ ጎልያድ በማስመሰል በአንድ ምሳሌያዊ ዳዊት እንዲግደሉ የሃይማኖታዊ ግድያ ጥሪ ያስተላለፉት አቡን ሉቃስ የወንጀል ክስ ተመሠረተባቸው። አቡነ ሉቃስ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀጽ 247 እና 251 ድንጋጌ ተላልፈዋል በሚል ክስ ተመሰረተባቸው፡፡ ክሱ የቀረበባቸው በፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ ሕገመንግስታዊና በሕገመንግስት ስርዓት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀል ጉዳዮች ችሎት ነው። በአቡነ ሉቃስ ላይ ሁለት ክሶችን ያቀረበው የፍትሕ ሚኒስቴር የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጀነራል ዐቃቤ ሕግ ነው፡፡ ይህም ተከሳሽ አቡነ ሉቃስ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀጽ 247 (ሐ) እና አንቀጽ 258(ሀ) ስር የተደነገገውን ድንጋጌ እንዲሁም የወንጀል ህግ አንቀጽ 251 (ሐ) እና አንቀጽ 258 ስር … [Read more...] about “ዐቢይን ግንባሩን ብለህ ዳዊት ሁን” ያሉት አቡነ ሉቃስ ክስ ተመሰረተባቸው
“ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ተቀራርበን እንሠራለን” የከተማ አስተዳደሩና ቤተክርስቲያኗ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በዛሬው ዕለት ውይይት አድርገዋል። ከውይይታቸው በኋላም የጋራ መግለጫ ሰጥተዋል። የመግለጫው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል። ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ እና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጋራ የተሰጠ መግለጫ በዛሬው እለት የካቲት 8 ቀን 2014 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች በመስቀል አደባባይና በጃንሜዳ ባህረ ጥምቀት ቦታዎች በቀረቡ ጥያቄዎች ላይ የጋራ ውይይት አድርገናል፡፡ ውይይቱ በፍጹም ቅን ልቡና፣ መደማመጥና መግባባት በተሞላበት ስሜት ተካሂዷል፡፡ በመሆኑም በውይይቱ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመስቀል አደባባይና … [Read more...] about “ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ተቀራርበን እንሠራለን” የከተማ አስተዳደሩና ቤተክርስቲያኗ