አቡነ ሉቃስ በተከሰሱበት የቅስቀሳ ወንጀል ጥፋተኛ በተባሉበት ድንጋጌ በሥድስት ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ተወሰነ። ከፈጸሙት ወንጀል አኳያ ወደ ኢትዮጵያ ተላልፈው ሊሰጡ ይችላሉ። የቅጣት ውሳኔውን የወሰነው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ ሕገ-መንግሥታዊና በሕገ-መንግሥት ሥርዓት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀል ጉዳዮች የሚመለከተው ችሎት ነው። የፍትሕ ሚኒስቴር የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጀነራል ዐቃቤ ሕግ በአቡነ ሉቃስ ላይ ከሦስት ወራት በፊት÷ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀጽ 247 (ሐ) እና አንቀጽ 258 (ሀ) ሥር እና የወንጀል ሕግ አንቀጽ 251 (ሐ) የተመላከተውን ድንጋጌ ተላልፈዋል የሚሉ ሁለት ክሶች ማቅረቡ ይታወሳል፡፡ ተከሳሹ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተ-ክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ አባል እና የምሥራቅ … [Read more...] about አቡነ ሉቃስ 6 ዓመት ተፈረደባቸው፤ ወደ ኢትዮጵያ ተላልፈው ሊሰጡ ይችላል