• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የማርያምን ማዕረግ ዝቅ አደረገች

December 12, 2025 09:27 pm by Editor Leave a Comment

* ውሳኔው ለአብያተ ክርስቲያናት ኅብረት መንገድ ጠራጊ ነው ተብሏል

የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ከዚህ በፊት ለማርያም ተሰጥተዋት የነበሩት “የመድኃኒዓለም ረዳት” (Co-Redemptrix) እና “ሴት አማላጅ” (እናት አማላጅ) (Mediatrix) የሚሉት ስሞች ለማርያም እንዳይውሉ ውሳኔ አስተላለፈች። ውሳኔው በአብያተ ክርስቲያናት መካከል ሊመሠረት ለታቀደው ኅብረት ድጋፍ ሰጪ እንደሆነም ተነግሮለታል።

የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያንን የአስተምህሮና ሥነ-ስርዓት የሚመራው “በጳጳሳዊ ምክር ቤት የእምነት አስተምህሮ ጽ/ቤት” (Dicastery for the Doctrine of the Faith (DDF)) በኅዳር ወር መጀመሪያ “የእግዚአብሔር ታማኝ ሕዝብ እናት” (Mater Populi Fidelis) በሚል ርዕስ ስለ ማርያም ሰፊ ማብራሪያ ይፋ አድርጓል።

ሰነዱ “የመድኃኒዓለም ረዳት (Co-Redemptrix) የሚለው ለማርያም የተሰጠው ማዕረግ ማርያምን ለማወደስ የሚረዳ አይደለም” ይላል። ለማርያም የተሰጠው ይህ ማዕረግ እንዲያውም የጌታች ኢየሱስ ክርስቶስን ልዩ የሆነውን የማዳን ሚና የሚያደበዝዝ ነው በማለት ያብራራል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ያጸደቁት ይህ ሰነድ የማርያምን የማዕረግ አጠራሮችን አስመልክቶ ዘመናትን ላስቆጠረው ክርክር ዕልባት የሰጠ እንደሆነ በምሑራን ዘንድ አስተያየት ተሰጥቶበታል። በተለይ “የመድኃኒዓለም ረዳት” (Co-Redemptrix) (ወይም “ቤዛዊተ ኩሉ ዓለም”፤ የዓለም ሁሉ ቤዛ) የሚለው መጠሪያ በተለያዩ የክርስቲያን ሃይማኖቶች መካከል አንድነት ለማምጣት ለሚደረገው ሥራ ዕንቅፋት ሆኖ መቆየቱ ይታወቃል።

በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሱ የጸደቀውን ሰነድ በፊርማቸው ይፋ ያደረጉት የእምነት አስተምህሮ ጽ/ቤት ኃላፊው ካርዲናል ቪክቶር ማኑኤል ፌርናንዴዝ፤ ሰነዱ “ክርስቶስ ብቸኛ አማላጅና አዳኝ (መድኃኒዓለም) የመሆኑን ምሥጢር ከማሳየት አንጻር የማርያምን ከምዕመናን ጋር ያላትን ግንኙነት በተመለከተ ምን ቦታ ላይ እንደሆነች ለማሳየት የታለመ ነው፤ ይህም የካቶሊክን እውነተኛና ታማኝ ማንነት በማሳየት አብያተ ክርስቲያናትን ወደ ኅብረት ለማምጣት ከሚደረገው ጥረት (ecumenical effort)” ጋር አብሮ የሚሄድ ነው ብለዋል።

ሰነዱ “የጸጋዎች ሁሉ እናት” (‘Mediatrix of All Graces,’) የሚለው የማርያም መጠሪያ ውሱንነት ያለውና የማርያምን ልዩ ቦታ በቅጡ የማያሳይ ነው ብሎታል። “የአምላክ እናት” እና “የእግዚአብሔር ታማኝ ሕዝብ እናት” የሚሉት የማርያም መጠሪያዎች እንዲቀጥሉም ማደፋፈሪያ ሰጥቷል።

ማርያም በልጇ ኢየሱስ ክርስቶስ የዳነች መሆኗን በተመለከተ “ልዩ እና ከጊዜው በቀደመ መልኩ” አጽዕኖት ሰጥቶ ሰነዱ ተናግሯል። ሲያብራራም፤ “ተወዳዳሪ የሌለው የማርያም ታላቅነት የሚገኘው በተሰጣትና መንፈስ ቅዱስ በእርሷ እንዲሠራ በታማኝነት በመፍቀዷ ላይ ነው። ከክርስቶስ ሚና እኩል ወይም ጎን ለጎን የሆነ ሚና ስንሰጣት አቻ የሌለውንና የእርሷ ብቻ የሆነውን ውበቷን እንነፍጋታለን” በማለት ማስጠንቀቂያ አዘል ምክር ይሰጣል።       

ይህ በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የተወሰደውን አቋም በተመለከተ የምስራቃዊ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ምንም በይፋ ያወጡት መግለጫ የለም። ምክንያቱም በኦርቶዶክሳውያኑ ዘንድ ማርያም እንደ ካቶሊካውያን በእነዚህ የማዕረግ ስሞች ስለማትጠራ ነው። ይህ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ውሳኔ ከአንድ ሺህ ዓመት በፊት በኦርቶዶክስና በካቶሊክ መካከል የተፈጠረውን መከፋፈል ለማጥበብ ብዙ ዕድል እንደሚሰጥና ከተቻለም ውኅደት ለማምጣት እንደሚረዳ በሁለቱም ወገን ተነግሯል።  

የማርያም ማዕረግ ዝቅ የተደረገበት ሰነድ ይፋ በሆነበት ሮም በሚገኘው የኢየሱሳውያን ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት (Jesuit Curia) ንግግር ያደረጉት ካርዲናል ቪክቶር ማኑኤል ፌርናንዴዝ፤ ሰነዱ “… አብያተ ክርስቲያናትን ወደ ኅብረት ለማምጣት ከሚደረገው ጥረት (ecumenical effort)” ጋር አብሮ የሚሄድ ነው ማለታቸው የዓቋም ለውጥ መደረጉን በግልጽ የሚያሳይ ሆኖ የቀረበ ነው።

በፕሮቴስታንቱ ዘንድ በይፋ የወጣ ሁሉንም የሚወክል መግለጫ ባይኖርም ሃሳባቸውን በተናጠል በማኅበራዊ ሚዲያ የገለጹ ውሳኔው ይበል የሚያሰኝ ነው ብለዋል። ይህ ከዚህ በፊት ስንጠይቀው የነበረ ጉዳይ ነው ያሉ አንዳንድ የፕሮቴስታንት አስተያየት ሰጪዎች ውሳኔው ለአብሮነትና ለመቀራረብ በር ከፋች ነው ብለዋል።

የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያንን ውሳኔ በተመለከተ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ያወጣችው መግለጫ ባይኖርም በማኅበራዊ ሚዲያ የተለያዩ መልዕክቶችን የሚያቀርቡ የተሃድሶ እንቅስቃሴ አራማጆች ውሳኔውን በበጎ መልኩ ተቀብለውታል። የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንም ተመሳሳይ እርምጃ እንድትወስድና ማርያምን መጽሐፍ ቅዱስ ከሰጣት ክብር የበለጠ ከመስጠት ቤተ ክርስቲያን እንድትቆጠብ ጠይቀዋል።

ከወራት በፊት የምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ገብርኤል “የሰባ ገብዣ” በሚል ርዕስ ስቅለት ዕለት ባቀረቡት መልዕክት ከፍተኛ ውግዘትና ፍረጃ ተሰንዝሮባቸው ነበር። ሊቀ ጳጳሱ በመልዕክታቸው፤ “አትደንግጡ፣ ማርያም የዓለም ቤዛ አይደለችም! … ቤዛ ልጇ ክርስቶስ ነው” በማለት ነበር የተናገሩት። የአቡነ ገብርኤል ስብከት በቤተ ክርስቲያኗ በኩል ውግዘት ቢያስከትልም በርካታ የፕሮቴስታንት መምህራን ለስብከታቸው አድናቆትና ድጋፍ በመስጠት፤ ኅብረት የምንፈልግ ከሆነ በማርያም ጉዳይ ላይ መግባባትና ስምምነት ላይ መድረስ ያስፈልገናል ሲሉ የተደመጡም ነበሩ።

ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ ባሳተሙት “ደቂቀ እስጢፋኖስ” በሚለው መጽሐፍ በአፄ ዘርአ ያዕቆብ ዘመነ መንግሥት (1426-1460) የማርያም ማዕረግ እጅግ ገንኖ እንደወጣ ጽፈዋል። የንጉሡ እናት የበፊት ልጃቸው ስለሞቱባቸው “ያሁኑ ፅንሴ ተወልዶ በጤና ካደገ” ለማርያም እሰጠዋለሁ ብለው ተስለው የነበሩ መሆኑን መጽሐፉ ይጠቅስና ስለ አፄ ዘርአ ያዕቆብ ሲናገር፤ “(ንጉሡ) በእመቤታችን እርዳታ በሰላም በጤና ስለተወለደ ለሷ ከፍ ያለ ግዴታ የተሰማው ይመስላል። አባቱ ዳዊት የጀመረውን በፈረንሳይ፣ በእስፓኝ፣ በግብጽ፣ በፍልስጥኤም የተሠሩትን ታምሮቿን ወደ ግዕዝ መተርጎም በሰፊው ቀጠለበት፤ የውጪውን አገር ማስተርጎም ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያ ውስጥ የሠራቻቸውን ተአምራት ሁሉ፤ እየሰበሰበ በጽሑፍ አሰፈራቸው። ጸሐፊዎችን ሰብስቦ፣ ተአምረ ማርያምን እያስቀዳ በቅዳሴ ጊዜ እንደ ወንጌል በሥርዓት ቆመው እንዲያነቡት ለየገዳማቱ ላከላቸው፤ ይኽም አንድ የጭቅጭቅ ምንጭ ሆነ፤ ለየገዳማቱ በላከላቸው የተአምረማርያም መጽሐፍ መግቢያ ውስጥ “ፍጥረት ሁሉ ስለ እመቤታችን ተፈጠረ” የሚል” እንደነበረበት የፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ “ደቂቀ እስጢፋኖስ” መጽሐፍ ይናገራል (ገጽ 25)። በዚህም ምክንያት ሊሆን ይችላል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ከመንበረ ፓትሪያርኩ ጽሕፈት ቤት ጀምሮ በተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት እና የምዕመናን ቤቶች ውስጥ ባብዛኛው አውሮጳዊ መልክ ያላት ምስለ ማርያም ተሰቅላ ማየት ያልተለመደ ያልሆነው።

የተሐድሶ እንቅስቃሴ ዋና መምህር የሆኑት መሪጌታ ጽጌ ሥጦታው ለማርያም የሚሰጠው ከልክ ያለፈው ክብርና ውዳሴ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ድጋፍ የለውም ሲሉ አጥብቀው ይሞግታሉ። ይህንን ጉዳይ በተመለከተ መሪጌታ ጽጌ የሰጡትን ሰፊና በማስረጃ የተደገፈ ማብራሪያ እነዚህ ቪዲዮዎችን በማዳመጥ መረዳት ይቻላል፤ (“የማርያም ህይወት”፤ “ትንሣኤዋ – ጾመ ፍልሰታ”፤ ስለ ማርያም “ብዙ ጥያቄ ፤ አንድ መልስ!”)።

በታሪክ “የጨለማው ዘመን” ተብሎ የሚጠራውና በዳንኤል 7፡25 ትንቢት እንደተነገረው ለ1,260 ዓመታት (538 ዓም – 1798 ዓም እኤአ) በዘለቀው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የበላይነት ዘመን መጽሐፍ ቅዱስ በካህናቱ ካልሆነ በቀር ማንም እንዳያነብብ ታግዶ ነበር። በዚህም ምክንያት ሰዎች ከቤተ ክርስቲያኗ የሚነገራቸውን ማንኛውንም አስተምህሮ በእምነት ይቀበሉ ነበር።

የፈረንሳዩ ንጉሥ ናፖሊዮን የጳጳሳዊ ሥልጣንን ከማስወገዱ በፊት የተነሳው የፕሮቴስታንት ተሃድሶ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን በቋንቋቸው እንዲያነቡ በር የከፈተ ነበር። ፕሮቴስት ማድረግ መቃወም እንደመሆኑ የፕሮቴስታንት እሳቤ በካቶሊክ የሚሰጡት አስተምህሮዎችን በመቃወም የተጀመረ ነበር። ይህ ከአምስት መቶ ዓመት በፊት የተካሄደ ታላቅ ንቅናቄ አሁን ላይ በሃይማኖት ኅብረት ስም መስመሩ እየደበዘዘ መጥቷል። ለኅብረቱ እውን መሆን ከካቶሊክ በኩል የሚደረጉ የአስተምህሮ ለውጦች ጥሩ መደላድል የሚፈጥሩ በመሆናቸው ይህ የማርያምን ማዕረግ ዝቅ የማድረጉ ውሳኔ የሒደቱ አንድ አካል ተደርጎ የሚታይ ነው።

ኅብረት መፍጠርና አንድ መሆን በራሱ መልካም ቢሆንም በአንድነት ስም የሚደረጉ ውሳኔዎችን በማይቀበሉ ላይ የሚያመጣው ተጽዕኖና ውግዘት ቀላል አይሆንም። ዓለም ወደ ሃይማኖታዊ አንድነት መምጣቱን ተከትሎ ዓለምአቀፋዊ ይዘት ያላቸው ውሳኔዎች መተላለፋቸው አይቀሬ ነው (ዳንኤል 3)። እነዚህን ውሳኔዎች አንቀበልም በሚሉ ላይ አስገዳጅ ውሳኔዎች አብሮ ይተላለፍባቸዋል። ሰዎች ሁሉ ውሳኔዎቹን ወድደው፣ ፈቅደውና አምነው (“በግምባራቸው”) ወይም በግድ፣ ለመኖር ሲሉ (“በቀኝ እጃቸው”) እንዲቀበሉ ይደረጋሉ (ራዕይ 13:15-17)።

ፕሮቴስታንቶች ከካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ጋር ያላቸውን ልዩነት አጥብበው በኅብረት ስም የአስተምህሮ ስምምነት ላይ በመድረስ ፕሮቴስት ማድረጋቸውን አቁመው ወደ ኅብረት እንደሚመጡ አስቀድሞ የተነገረ ነው። “ታላቁ ተጋድሎ” በሚለው መጽሐፍ 36ኛው ምዕራፍ ላይ የተሰጠውን ሰፊ ትንታኔ እዚህ ላይ ማንበብ ይቻላል። የአስተምህሮ ልዩነታችን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ስለሆነ ወደ ስምምነት ለመምጣት አንችልም፣ የመጽሐፍ ቅዱስን እውነቶች መካድ አንችልም የሚሉ የኅብረቱ ተቃዋሚ ተደርገው በመቆጠር ለከባድ መከራና ስቃይ ይዳረጋሉ። 

“ለአውሬውም ምስል የማይሰግዱለትን ሁሉ ሊያስገድላቸው፥ ለአውሬው ምስል ትንፋሽ እንዲሰጠው ተሰጠው። ታናናሾችና ታላላቆችም ባለ ጠጋዎችና ድሆችም ጌታዎችና ባሪያዎችም ሁሉ በቀኝ እጃቸው ወይም በግምባራቸው ምልክትን እንዲቀበሉ፥ የአውሬውም ስም ወይም የስሙ ቍጥር ያለው ምልክት የሌለበት ማንም ሊገዛ ወይም ሊሸጥ እንዳይችል ያደርጋል” (ራዕይ 13:15-17)። (ጊዜው መጽሔት)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Religion, Right Column Tagged With: Catholic Church, Co-Redemptrix, ecumenical effort, Jesuit Curia, Mediatrix, Mediatrix of All Graces, ሊቀ ጳጳስ አቡነ ገብርኤል, መሪጌታ ጽጌ ሥጦታው, ደቂቀ እስጢፋኖስ

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የማርያምን ማዕረግ ዝቅ አደረገች December 12, 2025 09:27 pm
  • ኢህአፓ: ከነጭ ሽብር ወደ “አዲስ አበባ ትናገር” የጎዳና ሽብር? December 12, 2025 09:11 pm
  • EOC Bans Haile Gebrselassie Over Are­qie Comments Linked to Doping November 21, 2025 07:47 pm
  • በሥራ ማቆም አድማ ጥሪ ዘርፍ ባለሙያው ጃዋር ሌላ ጥሪ አቀረበ November 17, 2025 09:25 am
  • የ-አብሮነት ማኅበር የመረጠው ሕቡዕ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይፋ ሆነ November 5, 2025 12:06 pm
  • “የኢሳያስ አፈወርቂ ውድቀት አይቀሬ ነው … “ፅምዶ” ራዕይ ዓልባ” ነው – ሼትል ትሮንቮል October 26, 2025 10:15 pm
  • አሜሪካ ስላልተቀበለችው ነው “የሽሽግር መንግሥት” ስብሰባው በአምስተርዳም ተካሄደው October 25, 2025 11:09 pm
  • በዓባይ ግድብ ምረቃ፡ የሕዝብ ደስታ፣ የቴድሮስ ካሳሁን ዝምታ September 14, 2025 04:27 am
  • ኢትዮጵያ የውኃ ኑክሊየር ማብላያዋን ልታስመርቅ ነው  August 29, 2025 11:46 pm
  • መከላከያ በፋኖ አመራሮች ላይ እርምጃ ወሰደ፤ ዘመነ በ“አንድ ማንኪያ ቅንነት” አንድ እንሁን አለ August 23, 2025 12:35 am
  • ፋኖን በፋይናንስና በሎጂስቲክስ የሚደግፉ የጎጃም ባለሃብቶች ከስደት ሊመለሱ ነው August 14, 2025 12:42 am
  • የበቀለ ገርባ የአሜሪካ ጥገኝነት ማመልከቻ ውድቅ ተደረገ August 13, 2025 12:16 pm
  • ሞዐ ተዋሕዶ “ነጻ አውጪ ግምባር” – ሞነግ August 13, 2025 12:58 am
  • የሃይማኖትና የመንግሥት ጥምረት በረከት ወይስ መርገም?  August 5, 2025 09:18 pm
  • የባከነ የስደት ሕይወት ከደባርቅ እስከ ኖርዌይ July 29, 2025 05:44 pm
  • “በዚህ ዓመት መጨረሻ ትግራይን እንቆጣጠራለን”፤ ቲፒኤፍ July 22, 2025 01:28 am
  • Rusted screws, metal spikes and plastic rubbish: the horrific sexual violence used against Tigray’s women July 4, 2025 01:48 am
  • በሞርሞን ቤ/ክ ዕርዳታ የኪዳነምህረት ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ማምለኪያ ሥፍራ አገኘች July 2, 2025 01:28 pm
  • የበረከት ስምዖን “አየር ላይ ትዕይንት” አየር ላይ ተበተነ July 2, 2025 01:24 am
  • “ዐቢይ ይውረድ፣ እኛ እንውጣ፣ በተራችን እንግዛ” ስልቴዎች (ስብሃት፣ ልደቱ፤ ቴዎድሮስ) June 11, 2025 01:56 am
  • ኤሊያስ መሠረት የሚሠራው ለማነው? ለብጽልግና? ወይስ …? June 3, 2025 01:27 am
  • በግንቦት 20 – የሁለት መሪዎች ወግ May 28, 2025 02:01 am
  • በፈቃዳቸው የተመለመሉ ወጣቶች ሁርሶ ሥልጠና ጀመሩ May 22, 2025 09:11 am
  • ድብቁ ሤራ ሲጋለጥ – “ሦስትን ወደ አራት” May 21, 2025 01:01 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule