የሃይማኖትና የመንግሥትን መጣመር የሚደግፉም ሆነ ጥምረታቸውን በጽኑ የሚቃወሙ ጠንካራ የመከራከሪያ ነጥቦችን ያነሳሉ። ይህ ዘመናትን ያስቆጠረ ክርክር ባለንበትም ዘመን ሠለጠነ ከሚባለው ዓለም እስከ አገራችን የመወያያና የመከራከሪያ አጀንዳ ሆኖ ቆይቷል። ይህ አጭር ጽሑፍ በሁለቱ ጽንፎች መካከል የሚካሄደውን ክርክር ለማቅረብ ወይም ለአንዱ ለመወገን ያሰበ ሳይሆን የሁለቱ ጥምረት ምን ውጤት አመጣ? ታሪክስ ምን ያስተምረናል? የሚለውን በጣም በጥቂቱ ለማንሳት ነው። ለማሳያነትም የክርስትና እምነትና መጽሐፍ ቅዱስ የምንጠቀም ሲሆን ይህ ማለት ግን ስለ ሌሎች ሃይማኖቶች ታሪክ ምንም አይልም በሚል እንዳይወሰድ አደራ ለማለት እንወዳለን። የሦስቱ ታላላቅ ሃይማኖቶች አባት የሚባለው አብርሃም ይኖርበት ከነበረው ባቢሎን (የከለዳውያን ዑር) ወይም ያሁኗ ኢራቅ አካባቢ እግዚአብሔር … [Read more...] about የሃይማኖትና የመንግሥት ጥምረት በረከት ወይስ መርገም?

