ራሱን የትግራይ ነጻ አውጪ ግምባር (ትህነግ) በማለት የሚጠራው ሕገወጥ የወንበዴዎች ቡድን ተክሎብን እና ጥሎብን የኼደው መርዝ እስካኹን አልፋታ ብሎን የመከራ ዘመናችንን አርዝሞታል። ሀገርን በዘር ከፋፍሎ፤ ሕዝብን እንደ ከብት በክልል ወስኖ፤ ኢትዮጵያዊነትን በሰፈርና በወንዝ ወስኖ፤ ለዘመናት አብሮ የኖረን ሕዝብ በጠላትነት እንዲተያይ አድርጓል። እንዳሰበው ባይሳካለትም ሀገራችን ከመፍረስ ድና አኹን ያለችበት ቁመና ላይ ትገኛለች። ትህነግ ግን ነጻ አወጣዋለኹ ብሎ ሲነግድበት የነበረውን ሕዝብ የምድር ሲዖል ውስጥ ጨምሮ እያሰቃየው ይገኛል። ወደ ጉዳያችን ስንመለስ፤ ትህነግ መርዙን ተፍቶብን ወደ ትግራይ ኼዶ ቢመሽግም አሁንም ግን ግድያ፣ ደም ማፍሰስ፣ ማፈናቀል፣ አልቆመም። በሀገሪቱ ላይ የሚፈጽመው ዕልቂት የገፊና ጎታች ሤራ እንደሆነ በተደጋጋሚ ያነሳነው ጉዳይ ነው። ጎልጉል በዚህ … [Read more...] about ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው?
Moa Tewahido
ሞዐ ተዋሕዶ “ነጻ አውጪ ግምባር” – ሞነግ
ሰሞኑን ሞዐ ተዋሕዶ አየሩን ሞልቶታል። በተለይ በቅርቡ ከሞዐ ተዋሕዶ አመራሮች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ፋንታኹን ዋቄ የሰጡት ቃለ ምልልስ ወደኋላ ሄደን ብዙ ነገሮችን እንድንዳስስ የሚያስደርግ ሆኗል። የዛሬ ሦስት ዓመት በቀነኒሳ ሆቴል ዶ/ር ወንደሰን በሚመራው ስብሰባ መግለጫ በሰጡበት ወቅት የተናገሩትና ሰሞኑን የተሰማውን ጉዳይ ባጭሩ ለማስቀመጥ እንሞክራለን። ይህንን በማድረግም የሞዐ ተዋሕዶን ሁኔታ ለየት ባለ ሁኔታ ለማየት እንሞክራለን፤ እንደተባለው ሞዐ ሃሳብ የሚያመጣና ወደ ሕዝቡ የሚያሰርጽ ንቅናቄ ነው? ወይስ ሌላ ተልዕኮ አለው? የሚለውን በንጽጽር እናያለን። የዛሬ ሦስት ዓመት አካባቢ በቀነኒሳ ሆቴል ከተካሄደው የሞዐ ተዋሕዶ ስብሰባ በኋላ የማኅበረ ቅዱሳን ሚዲያ ከሶስት የሞዐ ተዋሕዶ አመራሮች ጋር ውይይት አድርጎ ነበር። በውይይቱ የተገኙት መምህር ገብረመድኅን እንየው፣ … [Read more...] about ሞዐ ተዋሕዶ “ነጻ አውጪ ግምባር” – ሞነግ
የሃይማኖትና የመንግሥት ጥምረት በረከት ወይስ መርገም?
የሃይማኖትና የመንግሥትን መጣመር የሚደግፉም ሆነ ጥምረታቸውን በጽኑ የሚቃወሙ ጠንካራ የመከራከሪያ ነጥቦችን ያነሳሉ። ይህ ዘመናትን ያስቆጠረ ክርክር ባለንበትም ዘመን ሠለጠነ ከሚባለው ዓለም እስከ አገራችን የመወያያና የመከራከሪያ አጀንዳ ሆኖ ቆይቷል። ይህ አጭር ጽሑፍ በሁለቱ ጽንፎች መካከል የሚካሄደውን ክርክር ለማቅረብ ወይም ለአንዱ ለመወገን ያሰበ ሳይሆን የሁለቱ ጥምረት ምን ውጤት አመጣ? ታሪክስ ምን ያስተምረናል? የሚለውን በጣም በጥቂቱ ለማንሳት ነው። ለማሳያነትም የክርስትና እምነትና መጽሐፍ ቅዱስ የምንጠቀም ሲሆን ይህ ማለት ግን ስለ ሌሎች ሃይማኖቶች ታሪክ ምንም አይልም በሚል እንዳይወሰድ አደራ ለማለት እንወዳለን። የሦስቱ ታላላቅ ሃይማኖቶች አባት የሚባለው አብርሃም ይኖርበት ከነበረው ባቢሎን (የከለዳውያን ዑር) ወይም ያሁኗ ኢራቅ አካባቢ እግዚአብሔር … [Read more...] about የሃይማኖትና የመንግሥት ጥምረት በረከት ወይስ መርገም?



