ራሱን የትግራይ ነጻ አውጪ ግምባር (ትህነግ) በማለት የሚጠራው ሕገወጥ የወንበዴዎች ቡድን ተክሎብን እና ጥሎብን የኼደው መርዝ እስካኹን አልፋታ ብሎን የመከራ ዘመናችንን አርዝሞታል። ሀገርን በዘር ከፋፍሎ፤ ሕዝብን እንደ ከብት በክልል ወስኖ፤ ኢትዮጵያዊነትን በሰፈርና በወንዝ ወስኖ፤ ለዘመናት አብሮ የኖረን ሕዝብ በጠላትነት እንዲተያይ አድርጓል። እንዳሰበው ባይሳካለትም ሀገራችን ከመፍረስ ድና አኹን ያለችበት ቁመና ላይ ትገኛለች። ትህነግ ግን ነጻ አወጣዋለኹ ብሎ ሲነግድበት የነበረውን ሕዝብ የምድር ሲዖል ውስጥ ጨምሮ እያሰቃየው ይገኛል። ወደ ጉዳያችን ስንመለስ፤ ትህነግ መርዙን ተፍቶብን ወደ ትግራይ ኼዶ ቢመሽግም አሁንም ግን ግድያ፣ ደም ማፍሰስ፣ ማፈናቀል፣ አልቆመም። በሀገሪቱ ላይ የሚፈጽመው ዕልቂት የገፊና ጎታች ሤራ እንደሆነ በተደጋጋሚ ያነሳነው ጉዳይ ነው። ጎልጉል በዚህ … [Read more...] about ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው?

