* በዕለቱ ቀሲስ ታጋይ ታደለ፣ ፓስተር ታደሰ አዱኛ እና የአካባቢው የሞርሞን ተወካይ ተገኝተዋል * “የኦርቶዶክሳውያን ዕንባ ታብሷል” ቀሲስ ታጋይ ላለፉት ዘጠኝ ዓመታት የማምለኪያ ቦታ በማጣት በብዙ ችግር ውስጥ የነበሩት የዩታ ጠቅላይ ግዛት ኪዳነ ምህረት ቅድስት ማርያም ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አባላት ከሞርሞን ቤ/ክ በተደረገላቸው የሕንጻ ሥጦታና ድጋፍ ቅዳሜ ሰኔ 21 ቀን 2017 ዓም (ጁን 28፣ 2025) ቋሚ የማምለኪያ ሥፍራ ማግኘታቸው ታወቀ። በቤተክርስቲያኑ ምረቃ ሥነስርዓት ላይ የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ፀሐፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ፤ ከሞርሞን ቤ/ክ (ኃላፊውን በመወከል) ኤልደር ፔፐር መሪ እንዲሁም የኢትዮጵያ ዩኒየን ሚሲዮን ፕሬዚዳንት ፓስተር ታደሰ አዱኛ እና ሌሎችም ተገኝተዋል (ቪዲዮውን እዚህ ላይ መመልከት … [Read more...] about በሞርሞን ቤ/ክ ዕርዳታ የኪዳነምህረት ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ማምለኪያ ሥፍራ አገኘች

