• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

በሞርሞን ቤ/ክ ዕርዳታ የኪዳነምህረት ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ማምለኪያ ሥፍራ አገኘች

July 2, 2025 01:28 pm by Editor Leave a Comment

* በዕለቱ ቀሲስ ታጋይ ታደለ፣ ፓስተር ታደሰ አዱኛ እና የአካባቢው የሞርሞን ተወካይ ተገኝተዋል

* “የኦርቶዶክሳውያን ዕንባ ታብሷል” ቀሲስ ታጋይ

ላለፉት ዘጠኝ ዓመታት የማምለኪያ ቦታ በማጣት በብዙ ችግር ውስጥ የነበሩት የዩታ ጠቅላይ ግዛት ኪዳነ ምህረት ቅድስት ማርያም ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አባላት ከሞርሞን ቤ/ክ በተደረገላቸው የሕንጻ ሥጦታና ድጋፍ ቅዳሜ ሰኔ 21 ቀን 2017 ዓም (ጁን 28፣ 2025) ቋሚ የማምለኪያ ሥፍራ ማግኘታቸው ታወቀ።

በቤተክርስቲያኑ ምረቃ ሥነስርዓት ላይ የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ፀሐፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ፤ ከሞርሞን ቤ/ክ (ኃላፊውን በመወከል) ኤልደር ፔፐር መሪ እንዲሁም የኢትዮጵያ ዩኒየን ሚሲዮን ፕሬዚዳንት ፓስተር ታደሰ አዱኛ እና ሌሎችም ተገኝተዋል (ቪዲዮውን እዚህ ላይ መመልከት ይቻላል)።

በምረቃው ወቅት የዩታ ኪዳነምህረት ቅድስት ማርያም ቤ/ክ ኃላፊ አባ ፍሰሐጽዮን ሲናገሩ ምዕመኑ ተጨናንቆ ባንዲት ትንሽ ክፍል ውስጥ ያመልክ እንደነበር ጠቅሰው አሁን ግን “ይህንን በማየት የደስታ ዕንባ አነባለሁ” በማለት ደስታቸውን ገልጸዋል።

የዛሬ አራት ዓመት አካባቢ የኦርቶዶክሳውያኑን ችግር በመመልከት ቀሲስ ታጋይ ለሞርሞኑ ኤልደር ሮናልድ ራስባንድ (Ronald A. Rasband) መፍትሔ እንዲፈልጉላቸው መናገራቸውን የኪዳነምህረት ቤ/ክ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ሚካኤል ማሞ በዕለቱ አስታውሰዋል። ኤልደር ሮናልድ በተለምዶ ሞርሞን ቤ/ክ ወይም በኦፊሻል አጠራሩ የኋለኛው ዘመን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱሳን ቤ/ክ (The Church of Jesus Christ of Latter-day Saints) በሚባለው የ12ቱ ሐዋርያት አመራር (የ12ቱ ሐዋርያት ኮረም – Quorum of the Twelve Apostles) አንዱ ናቸው።

በሞርሞን ቤ/ክ የ12ቱ ሐዋርያት አመራር የሚባለው አካል ከፕሬዚዳንታዊው ኮረም ቀጥሎ ያለ የቤ/ክኑ ከፍተኛ የአመራር ሥልጣን ነው። የኮረሙ አባላት 12 ወንዶች ሲሆኑ እነዚህም ሐዋርያት ተብለው እንደሚጠሩ የቤ/ክኑ ድረገጽ ይናገራል። ከዚህ በተጨማሪም “ሐዋርያ” ተብሎ በዚህ ኮረም የሚካተት ማንኛውም ሰው “ነቢይ፣ ተመልካች እና ባለራዕይ” ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ኤልደር ሮናልድ ራስባንድም በዚሁ ማዕረግ እንደሚጠሩ ገለታሪካቸው ይናገራል።

ቀሲስ ታጋይ ከኤልደር ሮናልድ ጋር ይህንን ንግግር ካደረጉ በኋላ የሞርሞን ቤ/ክ ለኦርቶዶክስ አማኒያን የማምለኪያ ሥፍራ ማፈላለጉን ጀመረ። በመቀጠልም ከዚህ በፊት የሞርሞን ቤ/ክ ለመጋዘንነት ወይም ዕቃ ማከማቻ ይጠቀምበት የነበረውን ሁለት ተለቅ ያሉ ሕንጻዎች ለኪዳነምሕረት በመስጠት የማደስ ሥራው ተጀመረ።

ላለፉት አራት ዓመታት ከኪዳነምሕረት፣ ከሞርሞን ቤ/ክ፣ ከስተርሊንግ ፋውንዴሽን (Stirling Foundation) እና ከሌሎችም በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ሁለቱም ሕንጻዎች ታድሰው አንዱ ለማምለኪያ ሥፍራነት፤ ሌላኛው ደግሞ ለወጥቤት፣ ለመጸዳጃ ቤትና ለካህናት መኖሪያ እንዲያገለግል በጥሩ ሁኔታ ታድሰው ቅዳሜ በተደረገው የምረቃ መርሃግብር ተመርቋል።

ቅዳሜ በተደረገው የምረቃ ፕሮግራም ላይ የስተርሊንግ ፋውንዴሽንን በመወከል የተገኙት የተቋሙ ምክትል ፕሬዚዳንት ኒኮል ስተርሊንግ ሲናገሩ፤ “ይህ ሕንጻ በሃይማኖቶች መካከል በሚደረግ ጥረትና ትብብር ምን ማድረግ እንደሚቻል በቀዳሚነት አመልካች ሆኖ የሚታይ ነው። ሰዎች እግዚአብሔርን ለማምለክ ይችሉ ዘንድ ሁሉም ወደጌታ በጋራ ሲያለቅስ፣ ሲጮህ የሚመጣውን ውጤት የሚያሳይ ነው” ብለዋል።

ከሞርሞን ቤ/ክ ጋር በቅርብ የሚሠራው ስተርሊንግ ፋውንዴሽን በበርካታ የምግባረ ሰናይ አገልግሎቶች ላይ በዓለም ዙሪያ የተሰማራ ሲሆን ከነዚህም መካከል፤ የማኅበረሰብ ልማት፣ የትምህርት፣ የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ፣ የጤና፣ ስደተኞችን መልሶ የማቋቋም፣ ወዘተ አገልግሎቶችን የሚሰጥ ሲሆን ከዚሁ ጋር የሃይማኖት መቻቻል እና በሃይማኖቶች መካከል መግባባትና መተባበር እንዲኖር የሚሠራ ትርፍ ዓልባ ተቋም እንደሆነ ድረገጹ ይጠቁማል።

ቅዳሜ ሰኔ 21 (ጁን 28) በኪዳነምህረት ቤ/ክ በተካሄደው የምረቃ ሥነስርዓት በክብር ዕንግድነት የተገኙት ፓስተር ታደሰ አዱኛ የሃይኖቶች መተባበር ለሰላም አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል። ፓስተር ታደሰን ጠቅሶ ዴዘርት ኒውስ (Deseret News) የተባለው ሚዲያ እንደዘገበው በዓለም የሚገኙ ሃይማኖቶች ሁሉ አንዱ ኃላፊነታቸው እርስበርሳቸው ሰላም እንዲሰፍን ማበረታታት መሆኑን ፓስተር ታደሰ መናገራቸውን ዘግቧል። ፓስተሩ ሲቀጥሉም፤ “እርስበርስ መረዳዳት አለብን፤ ምክንያቱም ኢየሱስ የኖረው ለራሱ ሳይሆን ለሌሎች ነው፤ ክርስትናም ማለት ይኸው ነው፤ እርስበርስ መረዳዳት ነው፤ ስለዚህ የሌሎች ሰዎች ሕይወት እንዲሻሻል መሥራት አለብን” ብለዋል። “ይህ ማለት” አሉ ፓስተሩ፤ “ዓላማው ሰላም ለመፍጠርና (ሰዎችን) ከፍ ለማድረግ ነው እንጂ ሰዎችን (ሃይማኖታቸውን) ለማስለወጥ ወይም አስተሳሰባቸውን ለማስቀየር አይደለም” ብለው ለሚዲያው መናገራቸውን ድረገጹ ዘግቧል።

ኤልደር ሮናልድ ራስባንድን በመወከል ከሞርሞን ቤ/ክ የተናገሩ ኤልደር ፔፐር መሪ (Elder Pepper Murray) ሲሆኑ እርሳቸውም በፓስተር ታደሰ የንግግር ቃላት ላይ አጽንዖት በመስጠት ዋናው ትኩረት መሆን የሚገባው “የዶክትሪን የአስተምህሮ ልዩነት” ላይ መሆን እንደሌለበት ከዚያ ይልቅ ግን “የወዳጅነትን ድልድዮችን በመገንባትና በመግባባት ላይ መሆን እንዳለበት” ለዴዘርት ኒውስ ተናግረዋል።  

ኤልደር ፔፐር ሲቀጥሉም “በዓለማችን ላይ የሃይማኖት ነጻነት ከዕለት ወደ ዕለት አደጋ ላይ እየወደቀ ባለበት ባሁኑ ወቅት ወዳጅነትንና ቁርኝትን በማጠናከር እና ድልድዮችን በመገንባት ላይ መሥራት ነው የሚያስፈልገን” ብለዋል። “እንደዚህ ያለውን ጉባዔ ማጠናከር ሁላችንንም ያጠናክረናል፤ ማኅበረሰብ ሲጠናከር እኛን የተሻልን፤ ማኅበረሰቡን ደግሞ የተጠናከረ እንዲሆን ያደርጋል፤ ስለዚህ በተናጠል ወይም በፍላጎት ተለያይተን ከምናደርገው ይልቅ በትብብር በጣም የተሻለ ማድረግ ይቻላል” ብለዋል።

በአሜሪካ የምረቃ ሥነስርዓቱ ሲካሄድ በአዲስ አበባም የሞርሞን ቤ/ክ አባላትና ወዳጆች በቀጥታ ሥርጭት መርሃግብሩን ተከታትለዋል። ወደ አርባ የሚጠጉ በተካፈሉበት የሆቴል አዳራሽ የተገኙት የሞርሞን ኢትዮጵያ ሚሲዮን ኃላፊ ኦሊቫ ኮውሊ (Oliva Cowley) “እንዲህ ዓይነቱ ኩነት ሃይማኖትን ወይም ዘርን ወይም እምነትን ሳይነኩ እርስበርስ መደጋገፍን የሚያደፋፍር ነው” ብለዋል። አበባ ብርሃኔ የተባሉ በአዳራሹ የተገኙ የኦርቶዶክስ ቤ/ክ አባል ደግሞ “ኤልደር ሮናልድ ራስባንድ ቤ/ክኗ ቦታ እንድታገኝ የቤተክርስቲያኗ አባላት ደግሞ ሕንጻውን በማደስ በመተባበራቸው ደስ ብሎኛል” ብለዋል። “በብዙ ኪሎሜትሮች ቢራራቁም የሁለቱም ቤተክርስቲያናት መሪዎች መተባበር መቻላቸውና ይህንን ማድረጋቸው ልቤን ነክቶኛል” ማለታቸውን የሞርሞን ቤ/ክ ድረገጽ ዘግቧል።

በሞርሞን ቤ/ክ እና በኦርቶዶክስ ቤ/ክ መካከል በተገነባው ድልድይ ምክንያት ሁለቱን ሃይማኖቶች ከሚያለያይዋቸው ይልቅ የጋራ የሆኑ ነገሮች እንዳሉ አባ ፍሰሐጽዮንም ተናግረዋል። ዴዘርት ኒውስ እንደዘገበው አባ ፍሰሐጽዮን የሞርሞን ቤ/ክ የግማሽ ዓመት ጉባዔ ሁለት ጊዜ የተሳተፉ ሲሆን የቤ/ክኑ መዘምራን የሚያቀርቡትን መዝሙርም መከታተላቸውን፣ ከሚሲዮናውያኑም ጋር መገናኘታቸውን እንዲሁም ከቤ/ክኑ አመራሮች ጋር የቀረበ ግንኙነት እንዳላቸው ታውቋል።

ኢትዮጵያውያን በአሜሪካ የዩታ ጠቅላይ ግዛት እንክብካቤ እንደሚደረግላቸው ሁሉ የሞርሞን ቤ/ክ አባላትም በኢትዮጵያ ተመሳሳይ እንዲደረግላቸው በወቅቱ ተነስቷል።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Middle Column, News, Religion Tagged With: Mormon Church, Stirling Foundation, The Church of Jesus Christ of Latter-day Saints, Utah St Mary Church

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • Rusted screws, metal spikes and plastic rubbish: the horrific sexual violence used against Tigray’s women July 4, 2025 01:48 am
  • በሞርሞን ቤ/ክ ዕርዳታ የኪዳነምህረት ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ማምለኪያ ሥፍራ አገኘች July 2, 2025 01:28 pm
  • የበረከት ስምዖን “አየር ላይ ትዕይንት” አየር ላይ ተበተነ July 2, 2025 01:24 am
  • “ዐቢይ ይውረድ፣ እኛ እንውጣ፣ በተራችን እንግዛ” ስልቴዎች (ስብሃት፣ ልደቱ፤ ቴዎድሮስ) June 11, 2025 01:56 am
  • ኤሊያስ መሠረት የሚሠራው ለማነው? ለብጽልግና? ወይስ …? June 3, 2025 01:27 am
  • በግንቦት 20 – የሁለት መሪዎች ወግ May 28, 2025 02:01 am
  • በፈቃዳቸው የተመለመሉ ወጣቶች ሁርሶ ሥልጠና ጀመሩ May 22, 2025 09:11 am
  • ድብቁ ሤራ ሲጋለጥ – “ሦስትን ወደ አራት” May 21, 2025 01:01 am
  • ከትግራይ ሾልኮ የወጣው ምሥጢራዊው ሰነድ ምንድነው? May 20, 2025 09:18 am
  • በደቡብ ጎንደር በጸዳሉ ደሴ የተመሩት 72 ታጣቂዎች እጃቸውን ሰጡ May 19, 2025 02:24 pm
  • የተመሠረተው የፋኖ አደረጃጀት ዋነኛ ዓላማው ድርድር መሆኑ ተነገረ May 14, 2025 11:07 pm
  • ከፍተኛ የፋኖ አመራሮች መገደላቸው ተነገረ May 6, 2025 10:40 pm
  • ሃይማኖትን ለተራ የፖለቲካ ሸቀጥ ማዋል ውርደት ነው April 24, 2025 12:43 am
  •  የኬሪያ ኢብራሒም ኑዛዜ “ብትንትናችን ወጥቷል” April 22, 2025 12:08 am
  • ለወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አመራሮች ወታደራዊ ሥልጠና ተሰጠ April 16, 2025 11:44 pm
  • ዓቅም እንደሌለው የገመገመው ሻዕቢያ ፊቱን ከጦርነት ወደ ዲፕሎማሲ እያዞረ ነው   April 15, 2025 12:32 am
  • “አንድ የፋኖ ተቋም (የእስክንድር) ተመሥርቷል፤ ሌሎቹ ደግሞ እንዲሁ አንድ ተቋም መሥርተው ወደዚህ ይመጡ” አበበ ጢሞ April 11, 2025 12:07 am
  • መለስ (ለገሰ) ዜናዊ – ተዋርዶ ያዋረደን! April 9, 2025 10:28 pm
  • የተከዜ ዘብ: የሉዓላዊነት መጠበቂያ April 8, 2025 11:49 pm
  • አዲስ አበባ አስተዳደር የሪፖርተርን የተዛባ መረጃ ኮነነ፤ ሕጋዊ እርምጃ እወስዳለሁ አለ April 8, 2025 10:06 pm
  • ሀሰተኛውን የሪፖርተር ዘገባ ንግድ ባንክ በጽኑ ተቃወመ፤ እርማትም ጠየቀ April 8, 2025 09:48 pm
  • “ኦሮሚያ ላይ ወይም ሌላ ቦታ ላይ ስታደርገው ከነበረ ትግራይ ወስጥም የማታደርግበት ምንም ምክንያት አይኖርህም” ነው ጌታቸው ረዳ April 7, 2025 10:22 pm
  • “TPLF’s belief in a strong federal government was always tied to its own dominance in Addis Ababa” April 7, 2025 10:15 pm
  • Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation March 31, 2025 02:36 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2025 · Goolgule