ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ በማኅበራዊ የትሥሥር ገጻቸው ይህንን ጽፈዋል።
ዛሬ በአቡዳቢ በመሠራት ላይ ያለውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጎብኝቻለሁ። 17682 ካሬ ሜትር መሬት ከተባበሩት ዓረብ ኤምሬት መንግሥት ተሰጥቶናል።
ለዚህም በኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ስም አመሰግናቸዋለሁ። ለጊዜው መገልገያ የሚሆነው ቤተ ክርስቲያን እየተጠናቀቀ ነው።
የጥምቀት በዓል በቦታው እንዲከበር የሚቻለው ሁሉ እንደሚደረግ ከሚመለከታቸው የሥራ ኃላፊዎች ቃል ተገብቶልናል።
ይሄንን መሰል ቦታዎች የታሪክና የዲፕሎማሲያችን ትእምርቶች ናቸው። እነርሱ ለእኛ ይሄንን ሲያደርጉ፣ አኛ ለገዛ ወገኖቻችን ከዚህ በላይ እንድናደርግ ትምሀርት ይሆነናል።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply