“ባለፉት 50 ዓመታት የተከሰቱት ጦርነቶች የተጀመሩት ሚዲያው ባስተጋባው ውሸት መሆኑን ደርሼበታለሁ” ጁሊያን አሳንዥ፤ የዊኪሊክስ መሥራች። የአገራችን ሚዲያ አውታሮች በተለይም የግሉ ሚዲያ የሚባሉትና በ1997 ምርጫ ወቅት የነበሩት በኢትዮጵያ ዴሞክራሲ እንዲቀጭጭ፣ የሃሳብ ልዩነት እንዳያድግ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችና አመራሮች ጉያ ሥር ገብተው የፈጸሙት ወንጀል የሚያስጠይቅ ነው። ለቀጣዩ ትውልድ መማሪያ ይሆን ዘንድ በወጉ ተጠንቶና ተሰንዶ ሊቀመጥ ይገባል። ምክንያቱም ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በተደጋጋሚ ሲከሰት ያየነው ፖለቲካው ወይም ፓርቲዎች ሚዲያውን አጀንዳ እያስያዙ ሲመሩት ይቆዩና በኋላ ፖለቲከኞቹ እርስበርስ ሽኩቻ ውስጥ ሲወድቁ የሚፈልጉትን ለማጥቃት ወይም በሐሰት ለመወንጀልና ፕሮፓጋንዳ ለመንዛት ሲሉ ለሚዲያ ባለቤቶቹ ባሪያና ተገዢ በመሆን እነርሱ ሚዲያውን መምራት ሲገባቸው … [Read more...] about ቀጣዩ የዳያስፖራ ፖለቲካና የሚዲያው አሰላለፍ
ems
“አርበኛ” መሳይ – “የድል ዜና” ሳይበርድ 50ሺህ ዶላር በጎፈንድሚ
አሁን ፊታቸውን ያዞሩበት ጓደኞቹ አራጋቢዎቹ “ዜናን አንተ ጻፋት፤ አንተ አንብባት” እያሉ ሲያሞካሹት ነበሩ። እንዲህ እንዲሉ ያበቃቸው ደግሞ መሳይ የግንቦት ሰባት/ኢሳት ሁለገብ ሠራተኛ በነበረበት ወቅት ኤርትራ ምድር ሄዶ እንደ አንድ የጦር አዛዥ “ዘመነ ካሤ” የሚመራውን “ጦር” ሲጎበኝ ፎቶ ተነስቶ ሲያዩት፤ የሻዕቢውን መሪ በልዩ ጥሪ አስመራ ድረስ ሄዶ ቃለ መጠይቅ ሲያደርግ ሲያዩት፣ የብልፅግናን ድሎች አዲሳባ ድረስ ሄዶ ሲዘግብ በምላሹም ለከፈለው መስዋዕትነት ተብሎ ትንሽዬ ጉልት ሲቸረው ሲያዩት፣ አዲሳባ በሄደበት ወቅት የሹማምንትን ስልክ ቁጥሮች ሰብስቦ ከመጣ በኋላ ከምግብ ቤቱ ሆኖ የሚያወራበትን አንከር ብሎ የሚጠራውን ዩትዩብ ሲከፍት ሲያዩት ነበር። የመሳይ “ድሎች” እንዲህ በቀላሉ ተወርተው የሚያልቁ አይደሉምና እዚሁ ላይ ላብቃ። አንዳንዶች ሲቀልዱ እንደሰማሁት መሳይ በወኔ … [Read more...] about “አርበኛ” መሳይ – “የድል ዜና” ሳይበርድ 50ሺህ ዶላር በጎፈንድሚ