አሁን ፊታቸውን ያዞሩበት ጓደኞቹ አራጋቢዎቹ “ዜናን አንተ ጻፋት፤ አንተ አንብባት” እያሉ ሲያሞካሹት ነበሩ። እንዲህ እንዲሉ ያበቃቸው ደግሞ መሳይ የግንቦት ሰባት/ኢሳት ሁለገብ ሠራተኛ በነበረበት ወቅት ኤርትራ ምድር ሄዶ እንደ አንድ የጦር አዛዥ “ዘመነ ካሤ” የሚመራውን “ጦር” ሲጎበኝ ፎቶ ተነስቶ ሲያዩት፤ የሻዕቢውን መሪ በልዩ ጥሪ አስመራ ድረስ ሄዶ ቃለ መጠይቅ ሲያደርግ ሲያዩት፣ የብልፅግናን ድሎች አዲሳባ ድረስ ሄዶ ሲዘግብ በምላሹም ለከፈለው መስዋዕትነት ተብሎ ትንሽዬ ጉልት ሲቸረው ሲያዩት፣ አዲሳባ በሄደበት ወቅት የሹማምንትን ስልክ ቁጥሮች ሰብስቦ ከመጣ በኋላ ከምግብ ቤቱ ሆኖ የሚያወራበትን አንከር ብሎ የሚጠራውን ዩትዩብ ሲከፍት ሲያዩት ነበር። የመሳይ “ድሎች” እንዲህ በቀላሉ ተወርተው የሚያልቁ አይደሉምና እዚሁ ላይ ላብቃ።
አንዳንዶች ሲቀልዱ እንደሰማሁት መሳይ በወኔ የሚናገረው ድምፁ እንደኛ በአንገት በኩል ሥርዓትን ተከትሎ አልፎ በአፉ ስለማይወጣ ነው ይላሉ። ስላልገባኝ ነገሩ ምን እንደሆነ ሳጣራ የአንገቱ ርዝመት ኢመደበኛ ስለሆነ አየር ከሳንባው በቀጥታ በአፉ ነው የሚወጣው፤ ይህም በበቂ ለማሰብ ጊዜ ስለማሰጠው ነው አሉኝ። እኔ እንግዲህ የሕክምና ሰው ስላልሆንሁ ማጣራት አልቻልኩም። አቅሙ ያላችሁ አጣርታችሁ ማብራሪያ ብትሰጡኝ እወዳለሁ።
ወደ ጉዳዬ ስመለስ … ዛሬ የምጽፈው ገድለ መሳይ ስላልሆነ በአንዲት ነገር ላይ ብቻ አተኩራለሁ። ለመሳይ እና ለትግሉ የሚጠቅም ሃሳብ ለመጠቆም ነው።
በአማራ ክልል የተቆሰቆሰውን ግጭት በተመለከተ የመሳይን ማኅበራዊ ገጽ ልጥፎች ለተከታተላቸው “ተኳሽ ነን” የሚሉትም በዚህ ልክ ስለ “ድሉ” የሚያውቁ አይመስለኝም። ምናልባት ቢጠየቁ፤
“ዴ በል አንዴ! እንዴ! እኛ እንደዚህ እየተዋጋን ነው እንዴ?” የሚሉ ይመስላል። ወይም መሳይ እኛን ውጪ ያለን አበሾችን አስተኝቶን እሱ ብቻ የሚያየው ተውኔተ ቅዠት ይሆን ያስብላል።
ለማንኛውም የግጭቱን ጉዳይ በተመለከተ መሳይ ስለ ጎንደር ብዙ ሲወተውት ነበር። ማርሽ ቀያሪው ጎንደር ግን እጅ አልሰጥም ሲል መሳይ ፋሲለደስን በቦንብ እየደበደቡት ነው ግን እርግጠኛ አይደለሁም ብሎ ዘገበ። ከዚያ ቀጠለና “ይህ የዶ/ር ዓለሙ ስሜ ፌስቡክ ነው” ብሎ ማለት የሚፈልገውን ጨምሮ ምሱን ካደረሰ በኋላ “የዓለሙ ስሜ ትክክለኛ ፌስቡክ አካውንት መሆኑን አላረጋገጥሁም” ሲል ምን ቢዘል ጓሮ እንዲሉ ሽሽት ከጀለ። ነገሩ ግን እንደሸማኔው መሸመኛ “ይሄ ሌላ ያ ሌላ” ዥዋዥዌ እንደሆነ ግልጥ ነበር”። ደግሞስ በዓለሙ ስሜ ስም ራሱ መሳይ የከፈተው አካውንት መሆኑን ለምን ብሎ ያረጋግጣል? ይሄ ትግሉን ያዳክማል፤ አይጠቅምም። በአራዶቹ ቋንቋ “እንዲሆን ተፈልጎ ሆነ”።
መሳይ ይቺን ዜና ካሟሟቀ በኋላ “ዌል እንግዲሁ ጓዶች አሁን ደግሞ ለውለታዬ ትግሉ ሳይበርድ ቻፓ ሞቅ የምታደርጉበት፣ ዶላር የምትገፈትሩበት፣ ኪስ የምታወልቁበት ሰዓት ነው” በማለት በትህትና ወደ ከፈተው የጎፈንድ ሚ አካውንት ዳያስፖራውን መራ። ይቺ ለ50ሺ ዶላር የሚጫወታት ልመና ምናልባት የመጨረሻው ሳትሆን አትቀርም። እኔ ግን ለምን ይሆን 50ሺ እየለመነ ያለው ብዬ የጻፈውን ለማንበብ ሊንኩን ተጫንሁት። ዩትዩቡን ሚዲያ እያለ የሚጠራው መሳይ ሥራው እየተሠራ ያለው “በአንድ ሰው ጥረትና በተወሰኑ ሰዎች የሞራል ድጋፍ” ነው ይላል። አንድ ሰው የተባለው ማን እንደሆነ መሳይ ምሥጢር ያደረገበት ምክንያት ባይገባኝም “ለሶስት ባለሙያዎች መጠነኛ ክፍያ በመፈጸም በኤዲቲንግና በሪፖርቲንግ” እያሠራ እንደሆነ በዲጂታል የልመናው ገጽ ላይ አስፍሯል። እዛው ፌስቡክ ገጽ ላይ ወረድ ብሎ የልጁ የልደት የደስታ መግለጫ ይታያል። ቢበረብሩት ለሚስቱ በዚሁ የልመና ገንዘብ የገዛላትን ጥሎሽ አበርክቶ፣ እሷም በዛው አጊጣ አንዱ ውሃ ዳር የተነሱት ምስል አይታጣም። ኩራት እራት ይሏል እንዲህ ነው ።
መሳይ ሦስት “አጋሮቼ ያላቸው” ሰዎች እነማን ናቸው ብዬ ሳፈላልግ ያገኘሁት መረጃ የሚጠቁመው ሁለቱን ብቻ ነው – እስክንድር ነጋና እና ዘመነ ካሤ ናቸው። ሦስተኛው ግን “ትፈለጋለህ” ተብሎ ወደ ዘብጥያ ወርዷል ብለው ምንጮቼ ጠቁመውኛል። የተረሳ አራተኛ ካለ ቧያለው ዘንድ ያለውን ሊስት ማንበበ የሚችሉ ይጠቁሙት። ግን እንደው በቁም ነገር እነዚህ ሦስት ሰዎች በርግጥ መረጃ አቀባዮቹ ከሆኑ መሳይ ራሱ ሊያባርራቸው ይገባል። ምክንያቱም ትላንት ፋሲለደስ በቦምብ ተመትቶ ፈረሰ ብለው የሰጡት መረጃ የጎፈንድሚ ሥራውን የሚያበላሹ ሆነው ነው የታዩኝ። ወይም ብልጽግና ደርቦ ገዝቷቸው ሊሆን ይችላል፤ ያው የተዛባ መረጃ እያቀረቡ ተዓማኒነቱን ሊያሳጡት ማለቴ ነው።
“ተጋዳላይ” መሳይ ግን ይህ ብዙም አላሳሰበውም፤ ይልቅ ለልመና ማሟሟቂያ ብሎ ያቀረባቸው ሦስቱ “ወዳጆቹ” “ባህርዳር ሙሽሮቿን ልትቀበል እየተሽኮርመመች እንደሆነ፣ ደብረብርሃን ገቢ መሆኑን፣ ጎንደር ላይ መከላከያ አልቻለም፣ የብልጽግና ወታደሮች መሳሪያ እየጣሉ እጅ እየሰጡ መሆናቸው …” ብሎ ከመዘገብ አላቀቡትም፤ ዜና እንደዚያ አይደል የሚሠራው? እንዲያውም በዳያስፖራው ዘንድ ትን እስከሚለው በመተንተን የሚታወቅ አንዱን ሚዲያ ጠቅሶ (ስለነበረበት ያውቀዋል) ከሚዲያው ከሚወጡት 5 ዜናዎች ሦስቱ የተፈበረኩ መሆናቸውን በምሥጢር ተናግሯል። እናንተም በምሥጢር ያዙት፤ እንዲህ ዓይነት ወሬ ትግል ያኮላሻል።
እኔ ግን እንደ “ዜጋ” መሳይን ለመምከር የምፈልገው ስንት ሠራተኛ እንዳለው እንዲህ በግልጽ ባያወራ የሚሻል መሆኑን ነው። ምክንያቱም ለዓመታት ሻዕቢያን በፕሮፓጋንዳው ዘርፍ ሲያግዝ የነበረ ትጉህ ልጅ ዳያስፖራው አያምነውም ማለት አግባብ አይደለም። ስለዚህ ስለ ዩትዩቡ ምንም መረጃ ሳይሰጥ ድጋፉን ብቻ ቢጠይቅ ይሻላል። እነዚህ ሦስት ቅጥር ሠራተኞቹ ከአሸባሪ ጋር በመተባበር ተብለው ሰሞኑን በቁጥጥር ሥር ቢውሉስ። ምሥጢር መጠበቅ ያስፈልጋል ለማለት ነው። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታወጀበት ጊዜ ነውና፤ መጠንቀቅ ያስፈልጋል ለማለት ነው።
በማከል ደግሞ አሁን መሳይ የጠየቀው ሃምሳ ሺህ ዶላር የመጨረሻው እንዳይሆን ለማሳሰብ እወዳለሁ። ሁኔታውና በተለይ ምድር ላይ ያለው ተጨባጭ ነገር የሚያሳየው ነገር ስላለ ብዬ ነው። አሁን ስሰማ ደግሞ በሚዲያ ስም ዩትዩብ ከፍተው ገንዘብ የሚሰበስቡ ሁሉ እንደ ዐሥራት ከሚሰበስቡት ቢያንስ ዐሥር በመቶውን (10%) በአማራ ክልል ለሚደረገው ትግል ማበርከት አለባቸው እየተባለ ነው። ሃሳቡ መጥፎ አይመስለኝም። ዕቅዱ የሚደገፍ ነው። ምክንያቱም ተወዛዋዥ፣ ሾፌር፣ እስክስታ ወራጅ፣ አክቲቪስት፣ ተንታኝ፣ ፖለቲከኛ፣ የትግሉ ስንቅና ትጥቅ አስተዳደር ሃላፊው አበበ በለው “ሁለተኛ የቀለብ፣ የጥይት መግዣ … ብላችሁ እንዳትደውሉ። እዛው ህዝብ ዘርፋችሁ ብሉ …” ሲል ንዴት አግሞት እንዳለው ዓይነት በራስ ሚድያ መዝረከረክ እንዳይፈጠር ይረዳል ብዬ ነው። ምክሬን ላቋርጥና ልቀጥል።
የሆነው ሆኖ ትግሉ እየተፋፋመ ሄዶ በዚህ ከቀጠለ እኔ መሳይ ከዚህ በላቀ ሁኔታ ይቀጥላል ብዬ ነው የማስበው። ካልሆነ ደግሞ ባለፈው ለትግሉ ብሎ የተረከበውን መሬት ሸጦም ቢሆን ይህንን “የኢትዮጵያን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ትኩረት በመስጠት ትኩስና ወቅታዊ መረጃዎችን ለኅብረተሰቡ በማቅረብ በአጭር ጊዜ ተደማጭነትን ያገኘ ሚዲያ” በራሱ የግል ወጪ መስዋዕትነት እየከፈል ማስቀጠል አለበት እላለሁ። መሬት ላይ ያለው በደሙ መስዋዕትነት ሲከፍል መሳይ የልጁን ልደት መደገስም ቢሆን አስቀርቶ ለቆመለት ዓላማ እስከመጨረሻው ይዋደቃል ብዬ አስባለሁ። ኤርትራ ድረስ የተከፈለ መስዋዕትነት እንዲህ ባጭሩማ አይቀርም።
እኔም በመሳይ ስም ይህንን ጥሪ አቀርባለሁ። ያው ቅድም እንዳልኩት ወቅቱ ያስቸኳይ ጊዜ ዓዋጅ የታወጀበት በመሆኑ ማንኛውንም ነገር ስታዋጡ በምሥጢር አድርጉት። እናንተ ለመሳይ መረጃ የምትልኩ ሦስት ሰዎችም መረጃችሁን በጥብቅ ጥንቃቄ ላኩለት። በኋላ እንደ ዮሐንስ ቧያለው (ውይ ሳላስበው አራተኛውን ሰው ገለጥኩት። እነሱንም ሲያመልጣቸው እንደዚህ ነውና በዛው ውሰዱት) ስልካችሁ ተሸቅቦ ያላችሁበት እንዳይጠፋ። ጎፈንድሚ አድራጊዎችም ጠንቀቅ በሉ፤ እነማን ናቸው ድጋፍ ያደረጉት ተብሎ በሕግ ቢገደድ መረጃችሁን አሳልፎ ሊሰጥባችሁ ይችላል። ያው የጎ ፈንድ ነገር የመረጃም ነገር መሆኑን ለማስታወስ ያህል ነው። መሳይን ካዳለጠው ሁልሽም ያዳልጥሻል። ምክንያቱም በልምድ የሚያውቀ አራተኛ ፖሊስ ጣቢያ ምርመራ መስሎት አቃሎ፣ ዘመዴ (ዘመድኩን በቀለ) “የጀርመን ፖሊስ አጫወተኝ። አክብሮ ጠየቀኝ። ተንከባክቦ መረመረኝ” ሲል በኩራት እንደገለጸው ማለቴ ነው። ይህ ለመሳይ ይገባዋል። ሚስቱ ብቻ ነች “ስንት ሸቀልክ” እያለች ጌጣ ጌጥ ከመግዛት ውጭ ሌላ የማይገባት።
ታጋይ መሳይ ትግሉን ከቅርስ ውድመት ወደ ጅምላ ጭፍጨፋና ግድያ ሪፖርት አሳድጎ የ”ርዕሰ መስተዳድር” ጌታቸው ረዳን የቀድሞ ሃላፊነት መረከቡን ማስታወቁን በዝምታ ማለፍ “ንፉግነት ነው” በሚል መግለጽ ወድጃለሁ። እዚህ ላይ “ንጹሃን አልሞቱም” ለማለት ሳይሆን ከድል ፋና ዘማሪነት በፈጣን አክሮባት የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪን ስልት መከተሉን “በጎበዝ ኮራጅነት” ታሪክ ላይ እንድትመዘግቡልኝ ነው። ነገሮች ሲረጋጉና በተገቢው መልካቸውን ሲይዙ ወንጀለኞችን ከሚታገሉት እውነተኞች ጋር የምቆም እንደሆንኩ፣ ይህን ለማድረግ የሚስቴን ነጠላ አንጥፌ ጎ ፈንድ ይደረግልኝ ብዬ እንደማልጮህ አስቀድሜ ለመግለጽ እወዳለሁ።
በነገራችን ላይ አንድ ነገር ልጠቁምና ላብቃ። መሳይ ከባልደረቦቹ ሲለይ “በቃኝ” ብሎ ነበር። አንድ ነቄ “የሚታለብ ህዝብ እያለ፣ አስመራ ድረስ የጋበዘው መረብ እያለ በዩቲዩብ ሽቀላ ገቢውን በግል መሰልቀጥ እያለ ለምን ለሶስት ወይ አራት ይካፈላል” ሲል ለብቻው ዩቲዩብ የሚባለውን የዲጂታል መለመኛ እንደሚከፍት ጽፎ ነበር። ስሙን ብቻ አላወቀም እንጂ በሌላው እርግጠኛ ነበር። ይህን ነቄ “ነብይ” ባልለውም ከኡበር ገቢ ጋር ደምሮ የዩቲዩብ ልመናን አስልቶ የመሳይን መዳረሻ ቀድሞ አሳይቶ ነበር። ግጥምጥም!!
ባለማተቡ ነኝ
“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣበ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።
Mesfin says
Nothing but untimely garbage. Please don’t write for the sake of writing unless it is valuable. This scribble of yours is nothing but an old lady’s gossip. At least Mr Mesay has something to contribute to his fellow citizens instead of gossiping like you. What a waste of a human brain. The funny part of all this is let alone other readers you can’t even entertain yourself with this type writing style. I suggest you go back to the sketchbook & start again.
Good day
Tesfa says
እንዲዝህ አይነት ከእውነት የራቀ እይታ ያላቸው ሰዎች ናቸው ሃገራችን በየዘመናቱ የሚያምሷት። ባለምተቡ የሚለው ሁሉ የቆሻሻ ክምር እንጂ ከእውነት ጋር አይገናኝም። እርግጥ ነው የሚነገረንና የምንሰማው ሁሉን ነገር እንዳለ መሰልቀጥ ልብና ሆድን ያሳምማል። ያም ሆኖ ስለ ጋዜጠኛ መሳይ ከላይ የተጎፈጨረው ጉዳይ በሃበሻይቱ ምድር ከሚታየውና ከሚሰማው እውነታ ጋር የሚጋጭ ማተብ አልባ በሆነ ሰው የተጻፈ ትችት ነው። ፓለቲካ ማለት የውሸት ክምር ማለት ነው። ለዚህ ነው የሃበሻው ፓለቲካ የአዙሪት ዋና የሆነው። ማንም ምንም መንግስትም ሆነ ወሬ አራጋቢ ሙሉነት የላቸውም። ሁሉም ከእነ ጉድለታቸው ነው ሃገር የሚመሩት ወሬ ነጋሪውም ወሬውን የሚያናፍሱት። በምድሪቱ የሚኖሩትና በውጭ ሃገር ሆነው ስለ ሃገራቸው ያገባናል የሚሉ ሁሉ ነገሮችን መፈተሽና ግብስብሱን ከእውነቱ መለየት ሃላፊነት አለባቸው። በዚህ ዘመን የወሬ አናፋሽም ሆነ የነጻነት ታጋዪ በተግባራቸው ካልተመዘኑ በቃል ድርደራ አብሮ ሆ ማለት ራስን ጅል ማድረግ ነው።
በብሄርተኞች ስካር ውስጥ ሆነው እየተወላገድ ለህዝቤ ያሉን ሁሉ ህዝባቸውን ክደው ለራሳቸው የመኖሪያና የመጦሪያ ሂሳብ በህዝቡ ስም ከፍተው ዛሬ እልፎች እረግፈው እነርሱ ቆመው ሲውረገረጉ ማየት አይ ሰላምና ነጻነት በስምሽ ስንት ግፍ ተሰራ ያስብላል። በብሄር ነጻነት ስም ዛሬ የራሳቸውን ሃገር እሳት ለኩሰው እግራቸው በረገጠው ሌላ ሃገር ሁሉ ሃገር አፍራሽና ሰላም አደፍራሽ የሆኑ ስንቶች ናቸው? የደቡብ ሱዳን ነጻነት ለደቡብ ሱዳን ያመጣው ተስፋ ምንድን ነው? የኤርትራው ነጻነት ለሰፊው የኤርትራ ህዝብ ያመነጨው መከራና ሰቆቃን ብቻ ነው። ከቁራሽ በተረፈችው ኢትዮጵያ በወያኔ የአፓርታይድ የክልል ፓለቲካ ተከፋፍላ ይኸው እንሆ ዛሬ እንደምናየውና እንደምንሰማው በብልጽግናው መንግስት የራስን ህዝብ በድሮን የሚገደልበት ሰአት ላይ ደርሰናል። የኦሮሞው የአማራው የትግሬው የሌላውም የክልልና የዘር እንዲሁም የቋንቋ ሰካራም ሁሉ ትርፍ አልባ የሙት ስብስብ ነው። ሰው አብሮ ሲኖር ብቻ ነው ሰላም የሚሰፍነው። አንድ እያለቀሰ ሌላው በሚስቅባት ምድር ሰላም በጭራሽ አይኖርም። ዛሬ የህዝብን መከራ ቸል ብለው ከገዢው መንግስት ጋር ቂጥ የገጠሙ ሁሉ ካለፈው ታሪክ ያልተማሩ እኖር ባይ ሟቾች ናቸው። በዚህም በዚያም ከእውነት የራቀ የወሬ አናፋሾ ለህዝቡና ለሃገሪቱም የሚጠቅም ነገር አለመሆኑን በመረዳት በተቻለ መጠን ሁሉ ሚዛናዊ የሆነና በመረጃ የተደገፈ ወሬ ቢነግሩን ለሁሉም የሚጠቅም ይሆናል። ይህ ማሩን አምሮ፤ ወተቱን አጥቁሮ የሆነ ያልሆነውን መቀባጠር ለሽርፍራፊ ሳንቲም ለቀማ ይበጅ እንደሆነ እንጂ ለህዝባችን አይጠቅምም።
Abdi Nor Iftin – Call me an American በተሰኘው መጽሃፉ ላይ የዚያድ ባሬው መንግስት ከወረደ በህዋላ ምድሪቱ ስርዓት አልባ ሆና የጎሳ ጦርነት የፈጠረውን ትርምስና የሰው የቤት የእንስሳትና የድር አውሬ እልቂት በልጅነት አይኑ ያየውን ሲነገረን አንድ ቦታ ላይ እንዲህ ይላል። ” ቤተሰባችን ከባይደዋ ወደ መቋድሾ እየተመለስን እያለ መንገድ ሁሉ ሬሳ በሬሳ ሆኗል፤ ሾፌሩም በሬሳ ክምር መንገድ ስለተዘጋበት ወርዶ የሰዎችን አስከሬን እየጎተተ ከመንገድ አውጥቶ መንገዳችን ቀጠልን። ወደ መቋድሾ ስንጠጋ ያ ከጥቂት ሰአት በፊት መንገድ ለመክፈት የሰው አስከሬን ይጎትት የነበረው ሰው ሳይታሰብ ተመትቶ ሞተ፡ እኛም ከመኪና ወርደን በእግር ሩጫችን ያዝነው ይለናል”። በጊዜ የኢትዮጵያ ሁኔታ በሰላም ካልተረጋጋ በዘርና በቋንቋ እንዲሁም በክልል ያለልክ የጦፈው የሃገሪቱ የፓለቲካ ስካር የሶማሊያውን እልቂትና የሃገር አወዳደቅ እጅግ የከፋ እንደሚሆን ከአሁኑ መገመት ይቻላል። ልብ ያለው የዛሬን ሳይሆን የነገንም ጭምር ማየት አለበት። ለጊዜአዊ ጥቅም እልፎችን እያስለቀሱና እያፈናቀሉ፤ በስማቸው እየነገድ፤ በየመንደሩና በከተማ መሃል ያዙኝ ልቀቁኝ ማለቱ ጠቃሚነት የለውም። የሃበሻዋ ምድር ገደል አፋፍ ላይ ቆማለች። መገፈታተርና መካሰሳችን ትተን የሃበሻዋን ምድር ኗሪዎች ወደ ሰላምና አንድነት ሊያመጡ በሚችሉ ነገሮች ላይ ማተኮሩ ለአሁኑም ሆነ ለወደፊቱም ትውልድ ይጠቅማል። በቃኝ!