• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

January 28, 2026 09:56 am by Editor Leave a Comment

የሪፖርተርን እና የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የ“በሬ ካራጁ” አዋዋል በአንድ ታሪክ እናብራራው … አንድ አውራ ዶሮ የነበረው አንድ ሰነፍ ገበሬ ነበር፤ ገበሬው ይህንን አውራ ዶሮ ከገዛበት ቀን ጀምሮ ዶሮውን ለመብላት የሚመኝ አንድ ኮሳሳ ቀበሮ በገበሬው ቤት ሁልጊዜ ያንዣብባል፤ በሰፈሩ እየዞረም “ዶሮው ታምሟል፤ ጠዋት ይሞታል” እያለ ቀበሮው ለሰፈረተኛው በሙሉ ያወራል፤ የሚወራበትን ያልሰማው ወይም ጆሮ ዳባ ያለው ሰነፍ ገበሬም ጉዳዩን ከመጠየቅና ከማጣራት ይልቅ “ቀበሮው መዞር ከጀመረ አንድ ቀን ሆነው፤ አንድ ሳምንት ሆነው፤ 15 ቀን ሆነው፤ … መቼም ቢርበው ነው” እያለ ያገኘውን ሥጋ ሲመግበውና የዙረቱን “በዓል” ሲያከብርለት ከሰነበተ በኋላ ቀበሮው በደንብ ሲጠበድል ዶሮውንም ያበላውን ገበሬም ሰለቀጣቸው።

በኢትዮጵያ በነጻ ሚዲያ ስም በነጻነት እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው ሪፖርተር ሚዲያ የተመሠረተበትን 30ኛ ዓመት እያከበረ ይገኛል። ለ30 ዓመት በሕይወት ለመኖር መቀለብ የግድ ነውና ለሦስት ዐስርተ ዓመታት ሲቆይ በርካታ ቀላቢዎች አፍርቷል።

ከአበበ ባልቻ ጋር 25ሺህ ብር በነፍስ ወከፍ አዋጥተን በ50ሺህ ብር ሪፖርተርን መሠረትን የሚለው አማረ አረጋዊ በዘመነ ትህነግ ቀላቢዎቹ የራሱ የትህነግ ድርጅቶችና የመንግሥት ማሽነሪው (state machinery) ነበር (አበበ ባልቻ ከአማረ ጋር ሪፖርተርን መመሥረቱ እንደ ክብር ማውራቱ በሌላ ጊዜ የምናየው ይሆናል)። ምክንያቱም ሪፖርተር የተቋቋመው የትህነግን ዓላማ የትህነግ ተቃዋሚ በመምሰል ለማስፈጸም ነው – በሌላ አነጋገር አውሬው ሪፖርተር በኢትዮጵያ ማሊያ ለትህነግ የሚጫወት ነበር፣ አሁንም ነው።

ባለፈው ስለ ሪፖርተር ባቀረብነው ሰፋ ያለ መረጃ ላይ ሪፖርተር በአዲስ አበባ የተቀመጠ የትህነግ ጉዳይ ፈጻሚ መሆኑን መጥቀሳችን ይታወሳል። ከዚህ በላይ በዋነኝነት ለማሳየት የሞከርነው የሪፖርተርን የአጀንዳ ተካይነት ሚና የተለያዩ ማስረጃዎችን በማጣቀስ ነበር።

ሪፖርተር ይህንን ሥራ ለመከወን ደግሞ በደንብ መቀለብ አለበት፤ በመረጃ ብቻ ሳይሆን በፋይናንስም። በሟቹ የደኅንነት ሰው ክንፈ ገብረመድኅን መረጃ ሲቀለብ የነበረው ሪፖርተር ከክንፈ ሞት በኋላ የትህነግ አጀንዳ ተካይነት ሚናው ቀጥሎ ቀላቢ ሳይቸገር ኖሯል። አሁን ላይ ደግሞ በቀዳሚነት ቀላቢዎቹ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሲሆኑ ባልተለመደ መልኩ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ሌላው ቀላቢ ሆኗል።

በ2014ዓም አጋማሽ አካባቢ የተቋቋው ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ብዙ የተለፋበት ታላቅ ተቋም ነው። ኮሚሽኑ እጅግ ሥር የሰደዱ የኢትዮጵያን ችግሮች በተለይም በዘመነ ትህነግ የተተከሉትን የሠንደቅ ዓላማ፣ የብሔራዊ ሕዝብ መዝሙር፣ የክልል አወቃቀርና አወሳሰን፣ በቋንቋ ላይ የተመሠረተ ፖለቲካ፣ … በተለይ ባለፉት 30 ዓመታት በሀገራችን የፖለቲካ ሥርዓት ውስጥ ትህነግ የተከለውን አፍራሽ አጀንዳ ሕዝብን አወያይቶ ዘላቂ መፍትሔ የሚያመጣ፣ መርዝ የሚያረክስ፣ ሰንኮፍ የሚነቅል ነው። በሌላ አነጋገር የምክክር ኮሚሽኑ አጥፊ አጀንዳዎችን ይነቅላል፤ ጠቃሚዎቹን ይተክላል።

ስለዚህ የኮሚሽኑ መቋቋም በመጀመሪያ የሚጎዳው ፖሊሲዎቹን እንዳይነቀሉ አድርጎ የተከለው ትህነግ እና የርዕዮቱ አራማጆችን ነው። በመሆኑም ትህነግም ሆነ ትህነጋውያን ኮሚሽኑን ፈጽሞ አይወዱትም። ግጭት ባለበት የአማራ ክልል ጨምሮ በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍል ኮሚሽኑ አጀንዳ ሲያሰባስብ፤ በትግራይ አጀንዳ እንዳያሰባስብ እስካሁን ድረስ በትጋት እየሠሩ ነው።

የአውሬው ሪፖርተር ባለቤት አማረ አረጋዊም ኮሚሽኑን ፈጽሞ አይፈልገውም። ስለዚህ ምን አደረገ? ልክ እንደ ቀበሮው ገና ኮሚሽኑ እንደተቋቋመ “ዶሮው ታምሟል፤ ነገ ይሞታል” እያለ ማስወራት ጀመረ።

ፌብሩዋሪ 23 ቀን 2022ዓም “መንግሥት ጣልቃ የሚገባ ከሆነ ከኃላፊነታቸው እንደሚለቁ የምክክር ኮሚሽኑ ሰብሳቢ አሳሰቡ” በሚል ርዕስ የፕሮፌሰር መስፍንን የተጨነቀ ወይም ለመልቀቅ ያገረገረ የሚመስል ፎቶ አክሎ ሪፖርተር አንድ ዜና አስነብቦ ነበር። ሌላው በ“ውጪ ሚዲያ” ስም ከሪፖርተር ጋር እየተናበበ የትህነግን አጀንዳ የሚተክለው ቢቢሲም በተመሳሳይ ርዕስ ዜና አውጥቶ ነበር።

ኮሚሽኑ ሥራውን ሲጀምር ሁሉንም ኮሚሽነሮች ያቀፈ የትውውቅ ፕሮግራም ከሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት ኃላፊዎች አድርጎ ነበር።

የካቲት 16 ቀን 2014ዓም በተወካዮች ምክርቤት በተካሄደው ፕሮግራም ላይ ዋናው ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ በዋነኛነት የተናገሩት ኃላፊነቱ ከባድ እንደሆነ፣ ግን ደግሞ ለመሥራት ፈቃደኛና ቁርጠኛ መሆናቸውን፣ ያለ መንግሥት ጣልቃ ገብነት በገለልተኝነት እንደሚሠሩና ይህም የመንግሥት አቋም እንደሆነ ቃል እንደተገባላቸው ነበር። ይህ ካልሆነ ግን ሥራቸውን ለመልቀቅ እንደሚገደዱም ተናግረዋል። ይህም ተገማችና ተጠባቂ ነው።

በተወካዮች ምክርቤት በተደረገው ስብሰባ ላይ ያልተገኘው፤ ጋዜጠኛ ያልላከው ወይም ያልተጋበዘው ሪፖርተር (ቢቢሲም እንዲሁ) ከምክር ቤቱ ድረገጽ ላይ ያገኘውን ዜና በራሱ የምኞትና የአጀንዳ ተካይ አቅጣጫ በመሥፈር ገና ኮሚሽኑ ቢሮ፣ ጠረጴዛ፣ ወንበር፣ ወረቀት፣ እስክሪብቶ፣ ላጲስ፣ መቅረጫ፣ … ሳይኖረው “ዶሮው ታምሟል፤ ነገ ጠዋት ይሞታል” በማለት ዘገበለት። “መንግሥት ጣልቃ የሚገባ ከሆነ ከኃላፊነታቸው እንደሚለቁ የምክክር ኮሚሽኑ ሰብሳቢ አሳሰቡ” ነበር የሪፖርተር ምኞታዊ ዜና።

ሪፖርተር “30ኛ ዓመቴን እያከበርሁ (ሠላሳ ዓመት እየዞርሁ) ነውና ስፖንሰር አድርጉኝ” በማለት የፕላቲኒየም፣ የወርቅ፣ የብር ስፖንሰሮችን መልምሎ “ቀልቡኝ” ማለቱን የሰሙ ሀገር አፍራሹን አውሬ ጥሩ አድርገው በሀገር ሃብት እየቀለቡ ነው። ከእነዚህ ቀላቢዎች መካከል የብር ስፖንሰሩ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ነው።

በቀጣይ ሌላኛውን ቀበሮ ቀላቢ ሰነፍ ገበሬ እናቀርባለን።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Middle Column, Politics Tagged With: Ethiopian National Dialogue Commission, Feeding the Beast, Feeding the Fox, operation dismantle tplf, Reporter

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
  • “ከህወሓት፣ ከሻዕቢያ፣ ከግብፅ ሰዎች ጋር ሆኖ እንዴት የአማራን ጥያቄ ማስመለስ ይቻላል?” ኮሎኔል ፈንታው January 25, 2026 04:23 am
  • የኢትዮጵያ አየር ኃይል: ለአፍሪካ ሀገራት የመጀመሪያዎቹን የአየር ኃይል አብራሪዎች ያሰለጠነ ተቋም January 25, 2026 03:50 am
  • የአማረ ሪፖርተር እያደረሰ ያለው የብሔራዊ ደኅንነት አደጋ January 22, 2026 01:56 am
  • የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የማርያምን ማዕረግ ዝቅ አደረገች December 12, 2025 09:27 pm
  • ኢህአፓ: ከነጭ ሽብር ወደ “አዲስ አበባ ትናገር” የጎዳና ሽብር? December 12, 2025 09:11 pm
  • EOC Bans Haile Gebrselassie Over Are­qie Comments Linked to Doping November 21, 2025 07:47 pm
  • በሥራ ማቆም አድማ ጥሪ ዘርፍ ባለሙያው ጃዋር ሌላ ጥሪ አቀረበ November 17, 2025 09:25 am
  • የ-አብሮነት ማኅበር የመረጠው ሕቡዕ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይፋ ሆነ November 5, 2025 12:06 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule