በ1930ዎቹ የጀርመን ወግ አጥባቂ ልሒቃን በሀገራቸው እያቆጠቆጠ ያለው ኮሙኒዝም አስፈራቸውና አንድ “መላ” ዘየዱ። በሕዝብ ዘንድ ዝና እያገኘ የመጣውን አዶልፍ ሒትለርን ወደ ሥልጣን ማምጣትና ኮሙኒዝምን ድባቅ መምታት። ውሳኔ ተላለፈ፤ ሒትለርም የፓርቲው ካዝና፣ ቁልፍ፣ ወንበር፣ … ሁሉም ተሰጠው። አጅሬውም ወዲያውኑ የራሱን መስተጋብር በመፍጠር ያበላውን ፓርቲ መልሶ መውጋት ጀመረ። የናትዚው “አውሬ” ሒትለር የዴሞክራሲ መዋቅሮችን አፈራረሰ፣ የተቃዋሚ እንቅስቃሴዎችን አገደ፣ የቀድሞ አጋሮቹን በሙሉ አጸዳና ሥልጣኑን በኪሱ አስገባ። ነፍሰበላ አውሬ እየቀለቡ መሆናቸውን ያልተገነዘቡት ወግ አጥባቂዎቹ ባሳደጉት “ውሻ” ተበሉ። ኢትዮጵያ ውስጥ እንደ ሒትለር እየተቀለቡ ያሉና አንድ ቀን ሊበሉን ያሰፈሰፉ፤ የበሉበትን ወጭት ሰባሪዎች ብቻ ሳይሆኑ ያበላቸውን የሚበሉ ወይም ሊበሉ እያደቡ ያሉ … [Read more...] about የአማረ ሪፖርተር እያደረሰ ያለው የብሔራዊ ደኅንነት አደጋ

