• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ሀሰተኛውን የሪፖርተር ዘገባ ንግድ ባንክ በጽኑ ተቃወመ፤ እርማትም ጠየቀ

April 8, 2025 09:48 pm by Editor Leave a Comment

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በዚህ በጀት ዓመትም ሆነ ከዚያ በፊት አንድም ብር ለመንግሥት በቀጥታ አበድሮ እንደማያውቅ አስታውቋል።

ጉዳዩን አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተሰጠው መግለጫ እንደሚከተለው ቀርቧል፡-

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለመንግሥት አንድም ብር አበድሮ አያውቅም!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በዚህ በጀት ዓመትም ሆነ ከዚያ በፊት አንድም ብር ለመንግሥት በቀጥታ አበድሮ አያውቅም። መንግሥት ከሀገር ውስጥ የንግድ ባንኮች (በብሔራዊ ባንክ በኩል ለሽያጭ ከሚቀርበው የግምጃ ቤት ሰነድ ግዢ ውጪ) በቀጥታ የመበደር አሠራርም ሆነ ልምድ የለውም። ሀቁ ይህ ሆኖ ሳለ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በዚህ በተገባደደው ሳምንት ለኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የስምንት ወራት የስራ አፈጻጸም ማቅረባችንን ተንተርሶ በሪፓርተር ጋዜጣ የዕሁድ ዕትም ቅጽ 30 ቁጥር 2602 መጋቢት 28 ቀን 2017 ዓ.ም. ታትሞ የተሰራጨው ዜና ከርዕሱ ጀምሮ ለቋሚ ኮሚቴው ከቀረበው ሪፖርትም ሆነ ከእውነታው የተለየና የተዛባ መረጃ ሆኖ አግኝተነዋል። ለምሳሌ በጋዜጣው ዕትም ርዕስ ላይ የተገለጸውና “̋መንግሥት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተበደረው አንድ ትሪሊየን ዕዳ እንዳለበት ተገለጸ” የተባለው ዜና ከእውነት የራቀ ከመሆኑም በላይ በሪፖርቱም ፈጽሞ እንደዚህ አይነት ኃሳብ አልቀረበም።

“ባለፉት 15 ዓመታት 92 በመቶ ብድር የተሰጠው ለመንግሥት ተቋማት ነው ተብሏል” የሚለው ኃሳብም ስህተት ነው። የቀረበው ሪፖርት በግልጽ እንደሚያሳየው ከለውጡ በፊት የባንካችን የብድር ትኩረት ለመንግሥት ተቋማት እንደነበርና ይህ ብድር አድጎ በመጨረሻም ከአምስት ዓመት በፊት እስከ 92% እንደደረሰ እና ከአምስት ዓመት ወዲህ ግን ያ አሠራር የተቀየረና ቅድሚያ ለግል ተበዳሪዎች እየተሰጠ በመሆኑ ፤ ለምሳሌ ያህል በዚህ ስምንት ወራት ከተሰጠው ጠቅላላ ብር 264.65 ቢሊዮን ብድር ውስጥ ከ88% በላይ ብድር የተሰጠው ለግሉ ዘርፍ በመሆኑ አሁን ያለው የመንግሥት ተቋማት የብድር ክምችት ድርሻ ወደ 72% ዝቅ ማለቱን ተመላክቷል።

በመሰረቱ ይህ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ዕዳ መንግሥት በቀጥታ ራሱ የተበደረው የመንግሥት ዕዳ ሳይሆን የተለያዩ እንደ ባንካችን ያሉ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች የተበደሩት ዕዳ ነው። መንግሥት በእነኚህ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ውስጥ የባለቤትነት ድርሻ ቢኖረውም እነዚህ ተቋማት ከአስፈፃሚው መንግሥት የተለዩና የራሳቸው ካፒታል ያላቸው፣ እንደ ማንኛውም ድርጅት ንግድ ፍቃድ አውጥተው የሚነግዱ፣ በድርጅታቸው ስም ገንዘብ የሚበደሩ፣ ሊያተርፉም ሆነ ሊከስሩ የሚችሉ፣ ለትርፍ የተቋቋሙ የልማት ድርጅቶች ሲሆኑ ብድሮቹንም የወሰዱት ለራሳቸው ፕሮጀክቶች በመሆኑ ለእነዚህ ተቋማት የተሰጠውን ብድር የመንግሥት ብድር ተደርጎ መወሰዱ ስህተት ነው። በሀገሪቱ የማክሮ ኢኮኖሚ አስተዳደር መሰረት መንግሥት ማንኛውም ዓይነት የአጭርም ሆነ የረጅም ግዜ የገንዘብ ፍላጎቱን በሕግ በተቀመጠው አሠራርና ምንጭ ያሟላል እንጂ ከሀገር ውስጥ የንግድ ባንኮች በቀጥታ ብድር የሚወስድበት አግባብ የለም።

ትክክለኛው እውነታ ይህ ሆኖ እያለ አንዳንድ የመገናኛ ብዙኃን ዕዳውን መንግሥት በቀጥታ የተበደረው ዕዳ እንደሆነ አድርገው በሪፖርተር ጋዜጣም ሆነ ጋዜጣውን ተከትለው በወጡ አንዳንድ የሚዲያ አካላትም መረጃውን በተዛባና በተሳሳተ መልኩ መዘገባቸው ከባንካችን መግለጫ አውድ ውጭ የቀረበ ከመሆኑም በላይ የጋዜጣው ርዕስ በውስጡ ከተጻፉት ኃሳቦች ጋርም ያልተጣጣመ መሆኑ አንባቢያንን ግራ ሊያጋባ እንደሚችል ስለሰጋን እውነታውን ለማሳወቅ ተገደናል።

በጋዜጣው በጉልህ ከተገለጸው በተቃራኒ መንግሥት የልማት ድርጅቶች ከባንካችን የተበደሩትንና ለበርካታ ዓመታት ሳይከፍሉ የቆዩትን ከፍተኛ የብድር ገንዘብ በባንካችን ላይ የደቀነውን አደጋ በመገንዘብ የሚከተሉትን እርምጃዎች በመውስድ ባንካችንን ከውድቀት ታድጎታል።

በጋዜጣው በጉልህ ከተገለጸው በተቃራኒ መንግሥት የልማት ድርጅቶች ከባንካችን የተበደሩትንና ለበርካታ ዓመታት ሳይከፍሉ የቆዩትን ከፍተኛ የብድር ገንዘብ በባንካችን ላይ የደቀነውን አደጋ በመገንዘብ የሚከተሉትን እርምጃዎች በመውስድ ባንካችንን ከውድቀት ታድጎታል።

1ኛ. የልማት ድርጅቶቹ ከባንካችን ብድሩን የሚወስዱበት አሠራር አመላለሱን የሚያረጋግጥ ስላልነበረ ይህ አሠራር ሙሉ በሙሉ እንዲቀርና ባንካችን የውሳኔ ነጻነት እንዲኖረው ለመንግሥት ተቋማትም ቢሆን አዋጭ የንግድ ኃሳብ ለሚያቀርቡና ባንካችን ስለአመላለሱ እርግጠኛ ለሆነባቸው ብቻ ብድር እንዲሰጥ አቅጣጫ የተቀመጠው ከ5 ዓመት በፊት ነው። ይህ ብቻ ሳይሆን ቅድሚያ ለግል ተበዳሪዎች እንዲሰጥ እና የመንግሥት የልማት ድርጅቶችም ቀድመው የጀመሩትን ፕሮጀክቶች ሳይጨርሱ ሌላ እንዳይጀምሩ ስለተደረገ ከ5 ዓመት በፊት 92% ደርሶ የነበረው የመንግሥት ተቋማት አጠቃላይ የብድር ድርሻ ወደ 72% በአጭር ጊዜ ውስጥ ዝቅ ማለቱ እና የግሉ ተበዳሪዎች ድርሻ ደግሞ ከ8% ወደ 28% በፍጥነት ማደጉ ከፍተኛ ስኬት ሆኖ የቀረበና አንባቢያን ሊያውቁት የሚገባው ጥሬ ሀቅ ነው።

2ኛ. የልማት ድርጅቶቹ በወቅቱ መመለስ ያልቻሉትን ዕዳ በተመለከተ ደግሞ፡-

ሀ. መጀመሪያ የመንግሥት ዕዳ እና ኃብት አስተዳዳሪ ድርጅት በማቋቋም እዳዎቹን እንዲከፍል ከፍተኛ ጥረት ተደርጓል። በዚህ ጥረትም ከብር 42.4 ቢሊዮን በላይ እንዲከፈል ተደርጓል።

ለ. ችግሩ በዕዳና ሀብት አስተዳደር ድርጅት ጥረትም ሊፈታ እንደማይችል በመረጋገጡ በዚህ የበጀት ዓመት መጀመሪያ ላይ አጠቃላይ የአከፋፈል ችግር የገጠመው የመንግሥት የልማት ድርጅቶች የብር 845.3 ቢሊዮን ዕዳ ተሰባስቦ ወደ ገንዘብ ሚኒስቴር እንዲዞር እና በየዓመቱ በጀት ተይዞለት እና በአስተማማኝ ሁኔታ እንዲከፈል ለዚህም ተመጣጣኝ የመንግሥት ቦንድ ለባንካችን እንዲሰጥ በፓርላማ ጭምር በማጸደቅ ኃላፊነት የሚሰማውና ቆራጥ መንግሥት ብቻ የሚፈጽመው ታሪክ በመስራት ባንካችንን ከውድቀት ኢኮኖሚያችንንም ከትልቅ አደጋ ያዳነ እርምጃ በመውሰዱ መንግስታችንን እጅግ በጣም አመስግነናል፤ አሁንም እጅግ በጣም እናመሰግናለን። ከዚሁ ከተዛወረው ዕዳ ላይ ደግሞ በስምምነቱ መሰረት የመጀመሪያ የግማሽ ዓመት ወለድ በጥር ወር መጀመሪያ ላይ በገንዘብ ሚኒስቴር በኩል ብር 38 ቢሊዮን ለባንካችን ተከፍሏል። ስለዚህ መንግሥት ባንካችንን ለማዳን ሲል ከልማት ድርጅቶች ተቀብሎ መክፈል ከጀመረው ዕዳ ውጪ የተበደረው ምንም ገንዘብ እንደሌለ ለሕዝባችን ማሳወቅ እንፈልጋለን።

3ኛ. መንግሥት ከልማት ድርጅቶች ከተረከበው ከፍተኛ ዕዳ በተጨማሪ ባንካችንን ለማጠናከር የብር 54.7 ቢሊዮን የካፒታል ጭማሪ በማድረግ ከላይ ከተገለጸው የድርጅቶች ዕዳ ጋር ተደምሮ ብር 900 ቢሊዮን የመንግሥት ቦንድ እንዲሰጠን በማድረጉም ባንካችንን ሊገጥሙት የሚችሉትን የፋይናንሻል ስጋቶችን መቋቋም ብቻ ሳይሆን ጠንካራ እና ተወዳዳሪ ባንክ እንዲሆን ረድቶታል።

4ኛ. መንግሥት ባንካችንን የበለጠ ለማጠናከር ከዓለም ባንክ ጋር በመተባበር ላለፉት አምስት ዓመታት ጥልቅ ሪፎርም እንድናደርግ ከፍተኛ ድጋፍ እና አመራር የሰጠን ሲሆን የባንካችን ካፒታል የበለጠ እንዲጠናከርና የውጪ ምንዛሬ ፍላጎታችንን ለማሟላት ያለመ 650 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የካፒታል ማሳደጊያ ድጋፍ እንድናገኝ በማድረጉ ባንካችንን የበለጠ የሚያገዝፈው እና የማይበገር ጠንካራ ተወዳዳሪ የሚያደርገው የመንግስታችን ልዩ ድጋፍ በመሆኑ ባንካችን አሁንም አብዝቶ ያመሰግናል።

እንግዲህ እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ በስብሰባው ላይ የቀረቡትና ሕዝባችን ሊያውቃቸው የሚገቡ ብዙ መልካም ዜናዎች እያሉ ያለመታደል ሆኖ አሉታዊ ዜና የመናፈቅ ችግር ጎልቶ በታየበት አኳኋን ሪፖርተርም ሆነ ሌሎች ጥቂት ሚዲያዎች የባንካችንን እጅግ በጣም አንጸባራቂ የስምንት ወራት አፈጻጸም ላይ ጥላሸት ለመቀባት መሞከራቸው አሳዛኝ ተግባር ሆኖ አግኝተነዋል።

ይልቁንም ሕዝባችን ቢያውቀው የሚጠቅመው ባንካችን በስምንቱ ወራት አፈጻጸም በሁሉም ቁልፍ መለኪያዎች እጅግ በጣም የላቀና ከምንግዜውም እጅግ በጣም ከፍ ያለ ውጤት ማስመዝገቡን ነበር።

ለምሳሌ ያህል፦

1. በቁጠባ (Deposit)

√ በ8 ወራት ብቻ ብር 367 ቢሊዮን ማሰባሰብ መቻሉ፤ የዚህም ውጤት ከአምና ተመሳሳይ ወቅት ሲነጻጸር 344% በላይ ዕድገት መሆኑ፣

√ የባንካችን አጠቃላይ ተቀማጭ ብር 1.54 ትሪሊዮን በላይ መድረሱ፤ በዚህም የባንካችን የገበያ ድርሻ የመቀነስ ጉዞውን ቀይሮ በ2.2% በማደግ ወደ 49.3% ከፍ ማለቱ፣

2. ብድር

√ በ8 ወራት ብቻ ብር 149.2 ቢሊዮን መሰብሰቡ፤ ይህም ከአምና ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲወዳደር የ66.8% ዕድገት ማስመዝገቡ፣

√ በዚሁ ጊዜ ውስጥ አዲስ የተለቀቀ ብድር ብር 264.7 ቢሊዮን መሆኑ፤ ይኸውም ከአምና ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ82.4% ዕድገት ያስመዘገበ መሆኑ፤ ከተለቀቀው አዲስ ብድር ውስጥ ከ88.2% በላይ ለግሉ ክፍለ ኢኮኖሚ የተሰጠ መሆኑ፣

√ የባንካችን አጠቃላይ ብድር ከፍተኛ ዕድገት ያስመዘገበ በመሆኑ የባንካችን የብድር የገበያ ድርሻ የመቀነስ አቅጣጫውን ቀይሮ እ.ኤ.አ. ጁን 2024 ከነበረው 42.8% ከፍተኛ ዕድገት በማሳየት 51.7% ከፍ ማለቱ፣

√ የባንካችን የተበላሹ ብድሮች ምጣኔ አምና በተመሳሳይ ጊዜ ከነበረው የ2.7% ወደ 2.3% ዝቅ ማለቱ፤

3. በውጪ ምንዛሪ

– ባንካችን በ8 ወራት አፈጻጸሙ 2.45 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ማሰባሰቡ፤ ይህም ግኝት ከአምና ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ16.7% እድገት የነበረው መሆኑ፣

– በተለይም ከግል ኃዋላ እና ከሸቀጥ ወጪ ንግድ የተገኘው የውጪ ምንዛሪ እንደቅደም ተከተሉ የ52.2% እና የ58% ከፍተኛ እድገት ማስመዝገብ መቻላቸው፣

– ባንካችን በ8 ወራት ውስጥ አጠቃላይ ለገቢ ንግዱ የከፈለው የውጪ ምንዛሪ መጠን 5.14 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር መድረሱ እና ከዚህም ውስጥ ለግሉ ሴክተር የተከፈለው 1.22 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ከአምና ተመሳሳይ ወቅቶች ጋር ሲነፃፀር የ58% ከፍተኛ እድገት ማስመዝገቡ መልካም ስኬት ነው፡፡

4. ካፒታል

የባንካችን አጠቃላይ ካፒታል ከአምና ተመሳሳይ ወቅት ሲወዳደር የ105% ዕድገት በማሳየት ብር 132 ቢሊዮን መድረሱ፤

5. አጠቃላይ ሀብት

የባንካችን አጠቃላይ ሀብት በስምንት ወራት በብር 641.7 ቢሊዮን በማደግ ብር 2.07 ትሪሊዮን መድረሱ፤ በዚህ የ44.8% ከፍተኛ ዕድገት ማስመዝገብ በመቻሉ በሀብት የነበረን የገበያ ድርሻ እ.ኤ.አ. በጁን 2024 ከነበረው 43.7% ከፍተኛ ዕድገት በማስመዝገብ 50.4% መድረስ መቻሉ፤

6. አጠቃላይ ገቢና ወጪ

√ በ8 ወራት ባንካችን በሁሉም ዘርፍ ከፍተኛ የገቢ ዕድገት ያስመዘገበ ሲሆን አጠቃላይ ገቢውም ብር 109 ቢሊዮን መድረሱ፤ ይኸውም ከአምና ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲወዳደር የ26 % ዕድገት ማስመዝገቡ ፣

√ ባንካችን ጥብቅ የወጪ ቅነሳ ፕሮግራም ሲከተል የነበረና ከፍተኛ የተበላሹ ብድሮች ቅነሳ በማድረጉ ምንም እንኳን በማክሮ ኢኮኖሚው ደረጃ ብዙ ወጪ ጨማሪ ምክንያቶች ቢኖሩም ባንካችን ከመደበኛ የስራ እንቅስቃሴው ያስመዘገበው የወጪ ዕድገት የ2.6 በመቶ ብቻ በመሆኑ አጠቃላይ የመደበኛ ኦፕሬሽን ወጪ ብር 76.7 ቢሊዮን ብቻ መሆኑ፤

7. መደበኛ ያልተጣራ ትርፍ

√ ባንካችን በ8 ወራት ብር 32.6 ቢሊዮን ያልተጣራ ትርፍ ከመደበኛ ኦፕሬሽን ማግኘት መቻሉ እና ይኸም አፈጻጸም ከአምና ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ170.5% ዕድገት ያሳየ ብቻ ሳይሆን ከዚህ በፊት ዓመቱን በሙሉ ተመዝግቦ ከሚያውቀው ትልቁ ትርፍም ከፍተኛ ብልጫ ያሳየ መሆኑ፣

8. የዲጂታል ግብይት

√ ባንካችን በ8 ወራት በዲጂታል ቻናሎቹ ብቻ ከብር 7.7 ትሪሊዮን በላይ ማንቀሳቀሱ፤ አጠቃላይ የግብይት ብዛትም የ1.27 ቢሊዮን የበለጠ መሆኑ የተንቀሳቀሰው ገንዘብ ከአምና ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ92% ዕድገት ያሳየ ሲሆን የግብይት ብዛት ዕድገትም ከ84% በላይ ዕድገት የነበረው መሆኑ፤

√ ከባንካችን አጠቃላይ የደንበኞች ግብይት በስምንቱ ወራት አማካይ ግብይት 79% በዲጂታል የተስተናገዱ ሲሆን 21%ቱ ብቻ ወደ ቅርንጫፎቻችን ጎራ ብለው የተስተናገዱ መሆኑ ለደንበኞቻችን ምቾት እና ለባንካችን በወጪ ቁጠባም ያገዘና እጅግ በጣም ከፍተኛ ስኬት ማስመዝገቡ የሚጠቀሱ ከፍተኛ ቁልፍ ስኬቶች ናቸው፡፡

በሌሎች በተቀሩትም ዘርፎች ተመሳሳይ ስኬት የተመዘገበበት በመሆኑ እጅግ በጣም ደስ ይለናል፤ ሁላችሁም የተከበራችሁ የባንካችን ደንበኞችም ሆናችሁ ሀገር ወዳዶች በሙሉ በባንካችን መልካም አፈጻጸም ደስ እንደምትሰኙ እና ከባንካችን ጋር አብሮነታችሁን እንደምታጠናክሩ እናምናለን።

በመጨረሻም ባንካችን ለመንግሥት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴው በግልጽ ካቀረበው እውነታ ባፈነገጠና በተዛባ መልኩ የሪፖርተር ጋዜጣ በዜና አርዕስቱ “መንግሥት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተበደረው አንድ ትሪሊዮን ዕዳ እንዳለበት ተገለጸ” በሚል እንዲሁም በሌሎች ጥቂት ሚዲያዎችም የመንግሥት ዕዳ ብር 1.3 ትሪሊዮን እንደተሻገረና አሁናዊ የመንግሥት የብድር ዕዳ ዕድገትን የሚያሳይ በሚመስል መልኩ ተቀናብሮ የቀረበው ዘገባ ሀሰተኛ ከመሆኑም ባሻገር ከላይ በዝርዝር በተመላከቱት እውነተኛ መረጃዎች ላይ ተመስርቶ በባንካችን በኩል የቀረበውን ትክክለኛ ሪፖርት የማያንጸባርቅ እና እነዚህን ለመንግሥት የልማት ድርጅቶች የተሰጡትን ብድር ለባንካችን ለመክፈል መንግሥት እያደረገ ያለውን ቁርጠኝነት ታሳቢ ያላደረገ በመሆኑ ጉዳዩ በሚመለከታቸው ሚዲያዎች የተላለፈው የተዛባና የተሳሳተ ዘገባ እንዲታረም እናሳስባለን።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Left Column, News Tagged With: CBE, Reporter

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • Rusted screws, metal spikes and plastic rubbish: the horrific sexual violence used against Tigray’s women July 4, 2025 01:48 am
  • በሞርሞን ቤ/ክ ዕርዳታ የኪዳነምህረት ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ማምለኪያ ሥፍራ አገኘች July 2, 2025 01:28 pm
  • የበረከት ስምዖን “አየር ላይ ትዕይንት” አየር ላይ ተበተነ July 2, 2025 01:24 am
  • “ዐቢይ ይውረድ፣ እኛ እንውጣ፣ በተራችን እንግዛ” ስልቴዎች (ስብሃት፣ ልደቱ፤ ቴዎድሮስ) June 11, 2025 01:56 am
  • ኤሊያስ መሠረት የሚሠራው ለማነው? ለብጽልግና? ወይስ …? June 3, 2025 01:27 am
  • በግንቦት 20 – የሁለት መሪዎች ወግ May 28, 2025 02:01 am
  • በፈቃዳቸው የተመለመሉ ወጣቶች ሁርሶ ሥልጠና ጀመሩ May 22, 2025 09:11 am
  • ድብቁ ሤራ ሲጋለጥ – “ሦስትን ወደ አራት” May 21, 2025 01:01 am
  • ከትግራይ ሾልኮ የወጣው ምሥጢራዊው ሰነድ ምንድነው? May 20, 2025 09:18 am
  • በደቡብ ጎንደር በጸዳሉ ደሴ የተመሩት 72 ታጣቂዎች እጃቸውን ሰጡ May 19, 2025 02:24 pm
  • የተመሠረተው የፋኖ አደረጃጀት ዋነኛ ዓላማው ድርድር መሆኑ ተነገረ May 14, 2025 11:07 pm
  • ከፍተኛ የፋኖ አመራሮች መገደላቸው ተነገረ May 6, 2025 10:40 pm
  • ሃይማኖትን ለተራ የፖለቲካ ሸቀጥ ማዋል ውርደት ነው April 24, 2025 12:43 am
  •  የኬሪያ ኢብራሒም ኑዛዜ “ብትንትናችን ወጥቷል” April 22, 2025 12:08 am
  • ለወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አመራሮች ወታደራዊ ሥልጠና ተሰጠ April 16, 2025 11:44 pm
  • ዓቅም እንደሌለው የገመገመው ሻዕቢያ ፊቱን ከጦርነት ወደ ዲፕሎማሲ እያዞረ ነው   April 15, 2025 12:32 am
  • “አንድ የፋኖ ተቋም (የእስክንድር) ተመሥርቷል፤ ሌሎቹ ደግሞ እንዲሁ አንድ ተቋም መሥርተው ወደዚህ ይመጡ” አበበ ጢሞ April 11, 2025 12:07 am
  • መለስ (ለገሰ) ዜናዊ – ተዋርዶ ያዋረደን! April 9, 2025 10:28 pm
  • የተከዜ ዘብ: የሉዓላዊነት መጠበቂያ April 8, 2025 11:49 pm
  • አዲስ አበባ አስተዳደር የሪፖርተርን የተዛባ መረጃ ኮነነ፤ ሕጋዊ እርምጃ እወስዳለሁ አለ April 8, 2025 10:06 pm
  • ሀሰተኛውን የሪፖርተር ዘገባ ንግድ ባንክ በጽኑ ተቃወመ፤ እርማትም ጠየቀ April 8, 2025 09:48 pm
  • “ኦሮሚያ ላይ ወይም ሌላ ቦታ ላይ ስታደርገው ከነበረ ትግራይ ወስጥም የማታደርግበት ምንም ምክንያት አይኖርህም” ነው ጌታቸው ረዳ April 7, 2025 10:22 pm
  • “TPLF’s belief in a strong federal government was always tied to its own dominance in Addis Ababa” April 7, 2025 10:15 pm
  • Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation March 31, 2025 02:36 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2025 · Goolgule