የኮማንዶ እና አየር ወለድ ዕዝ ማሠልጠኛ ማዕከል ያሠለጠናቸውን የመሠረታዊ ኮማንዶ አባላት አሥመርቋል።በዚሁ የምርቃት መርሃ-ግብር ላይ የተገኙት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የጦር ሃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዐቢይ አሕመድ (ዶክተር) ከተናገሩት የተወሠደ፦ 👉 የኢትዮጵያ ሠራዊት መሆን ያኮራል ፤👉 ሠራዊቱ ሁለት ዓላማዎች አሉት 1ኛ ጥፋት ውድመት እና ሌላ ክስተት እንዳይፈጠር ውጊያን ማሥቀረት 2ኛ ውጊያን መጨረስ ፤👉 ውጊያን ሠው ጀምሮ ሠው አይጨርሰውም የምንዋጋው በቴክኖሎጂ የምንጨርሰው በሠራዊቱ ነው ፤👉 ውጊያን ጨርሳችሁ ድል የምታደርጉት እና የኩሩ ህዝቦች መዝሙር የምትዘምሩት እናንተው ናችሁ ፤👉 ለሀገራችሁ ሶስት ነገሮችን ስጡ 1ኛ እንድታሥቡ አዕምሯችሁን 2ኛ ለሀገር ፍቅር ልባችሁን 3ኛ እንድትሠሩ እጃችሁን ፤👉 ኢትዮጵያ የሀገር ፍቅር እና የመለዮ … [Read more...] about ኢትዮጵያ በታሪኳ የመጀመሪያውን ግዙፍ ወታደራዊ ኃይል አስመረቀች
ethiopian defense force
ከ፴ ዓመት ውርደት በኋላ የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል የውሃ አካል ላይ ግዳጅ ለመወጣት ዝግጁ ነው
በትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ትህነግ) ተላላኪነትና ባንዳነት የፈረሰው ገናናው የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ከ፴ ዓመት ውርደት በኋላ ዳግም እያንሠራራ ነው። አዳዲስ ባሕረኞችን በውጭ አገር እያሠለጠነ ሲሆን አዳዲሶችን ደግሞ በአገር ውስጥ እያስመረቀ ነው። ትላንት በመሠረታዊ ባሕረኞችን አስመርቋል። ከመከላከያ ማኅበራዊ ሚዲያ ያገኘነው ዜና ከዚህ በታች ቀርቧል። የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል አካዳሚ አዛዥ ኮማንደር ከበደ ሚካኤል በባሕረኞች የምረቃ ፕሮግራም ላይ እንደገለፁት አካዳሚው ባሕረኞች ከባህረኝነት ሙያ ጋር በቀጥታ ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ ሳይንሳዊ መርሆችን እንዲረዱ ስልጠና ወስደዋል። ባሕረኞች በባሕር ላይ የሚያጋጥማቸውን ዋና ዋና የሚባሉ መሠረታዊ የባሕር ላይ ደህንነት ትምህርቶች እና ሌሎች ጠቅላላ እውቀት ማግኘታቸውንም ገልፀዋል። ኮማንደር ከበደ … [Read more...] about ከ፴ ዓመት ውርደት በኋላ የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል የውሃ አካል ላይ ግዳጅ ለመወጣት ዝግጁ ነው
የሽብር ጥቃት ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ በቁጥጥር ስር ዋሉ
በአዲስ አበባና በአንዳንድ የኦሮሚያ ከተሞች የተቀናጀ የሽብር ጥቃት ለመፈፀም አቅደው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የሽብር ቡድን አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የደህንነትና ፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይል አስታወቀ፡፡ የደህንነትና ፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይል ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፥ በአዲስ አበባና በአንዳንድ የኦሮሚያ ከተሞች ሁከት፣ ሽብርና ትርምስ በመፍጠር ድብቅ የፖለቲካ አጀንዳቸውን ለማሳካት በሚንቀሳቀሱ የውጭ እና የውስጥ ፀረ-ሰላም ኃይሎች የሚደገፉ የሸብርተኞቹ የህወሓትና የሸኔ ቡድን አባላት በሰው ሕይወትና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ለማድረስ ሴራ ወጥነው ወደ እንቅስቃሴ ለመግባት በዝግጅት ላይ እንዳሉ በጋራ ግብረ ኃይሉ በተደረገባቸው ጥብቅና የተቀናጀ ክትትል በቁጥጥር ስር ውለዋል። ይህን እኩይ የጥፋት ሴራ ለመፈጸም ከውጭ በተለያዩ አካላት በሚደረግላቸው … [Read more...] about የሽብር ጥቃት ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ በቁጥጥር ስር ዋሉ