
የኮማንዶ እና አየር ወለድ ዕዝ ማሠልጠኛ ማዕከል ያሠለጠናቸውን የመሠረታዊ ኮማንዶ አባላት አሥመርቋል።
በዚሁ የምርቃት መርሃ-ግብር ላይ የተገኙት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የጦር ሃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዐቢይ አሕመድ (ዶክተር) ከተናገሩት የተወሠደ፦
👉 የኢትዮጵያ ሠራዊት መሆን ያኮራል ፤
👉 ሠራዊቱ ሁለት ዓላማዎች አሉት 1ኛ ጥፋት ውድመት እና ሌላ ክስተት እንዳይፈጠር ውጊያን ማሥቀረት 2ኛ ውጊያን መጨረስ ፤
👉 ውጊያን ሠው ጀምሮ ሠው አይጨርሰውም የምንዋጋው በቴክኖሎጂ የምንጨርሰው በሠራዊቱ ነው ፤
👉 ውጊያን ጨርሳችሁ ድል የምታደርጉት እና የኩሩ ህዝቦች መዝሙር የምትዘምሩት እናንተው ናችሁ ፤
👉 ለሀገራችሁ ሶስት ነገሮችን ስጡ 1ኛ እንድታሥቡ አዕምሯችሁን 2ኛ ለሀገር ፍቅር ልባችሁን 3ኛ እንድትሠሩ እጃችሁን ፤
👉 ኢትዮጵያ የሀገር ፍቅር እና የመለዮ ፍቅር ያለው ወታደር ያሥፈልጋታል ፤
👉 ለሀገራችን ያለን ፍቅር ለእውነት ያለንን ቅርበት የሚያመላክት ነው ፤
👉 ዋነኛ ተግባራችሁ ፀንታ የኖረችውን ኢትዮጵያ በፅናት ማሻገር ይሁን ፤
👉 ኢትዮጵያ የሠላም እንጂ የጦርነት ምንጪ አትሆንም ፤
👉 ደንበር ተሻግሮ ሠላም የሚያሥከብር ሠራዊት አለን፤
👉 ከሁሉም በላይ ቀዳሚ ፍላጎታችን ሠላም ነው፤
👉 ኢትዮጵያ ታላቅ ኢኮኖሚ እየገነባች ያለች ታላቅ ሀገር ናት፤
ከዚህ ሌላ በምርቃት መርሃ ግብሩ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከተናገሩት፦
👉 እኛ የመከላከያ ሠራዊት አመራሮች እየሠራን ያለነው ሥራ ፕሮፌሽናል ሠራዊት መገንባት ነወ፤
👉 አሁን ላይ ከሁሉም ኢትዮጵያዊያን የተወጣጣ ህብረ ብሄራዊ ሠራዊት እየገነባን ነው፤
👉 ብቃት ያለው ዘመኑ ያፈራውን ቴክኖሎጂ መጠቀም የሚችል ሠራዊት እያበቃን እንገኛለን፤
👉 የዛሬ ተመራቂ ኮማንዶዎች እና አየር ወለዶች የዘመናዊነታችን ማሣያዎች ናቸው፤
👉 ኮማንዶዎች እና አየር ወለዶች የምድር ድሮዎኖች ብቻ ሳይሆኑ በእሳት ተፈትነው ያለፉ የቁርጥ ቀን ልጆች ናቸው፤
👉 ቀይ መለዮ ማለት ጠላቱን የሚያርበደብድ ወገኑን የሚያኮራ ነው፤
ፎቶዎቹና መረጃው ከመከላከያ ማኅበራዊ ድረገጽ የተወሰደ
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply