"የኢትዮጵያን ባህር ኃይል ለማዘመን ከሀገር ውጭ እና በሀገር ውስጥ የሚሠጡ ስልጠናዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ" ሲሉ ተናገሩ ሬር አድሚራል ክንዱ ገዙ። የኢትዮጵያ ባህር ኃይል በአዲስ መልክ ከተመሠረተ ጀምሮ የተለያዩ አቅም ፈጣሪ ስልጠናዎችን ከሀገር ውጭ እና በሀገር ውስጥ አባላቱን በማሠልጠን ላይ ይገኛል። የኢትዮጵያ ባህር ኃይል ዋና አዛዥ ሬር አድሚራል ክንዱ ገዙ በብላቴ የኮማንዶ እና የአየር ወለድ ኃይል ማሠልጠኛ ማዕከል ተገኝተው የማሪን ኮማንዶ የሚሠለጥኑ የባህር ኃይል አባላትን ጎብኝተዋል። ዋና አዛዡ የስልጠና ሂደቱን ተዘዋውረው ከተመለከቱ በኋላ እንደተናገሩት የማሪን ኮማንዶ ሠልጣኞች በማሠልጠኛ ማዕከሉ የሚሠጡ ስልጠናዎችን በድሲፒሊን፣ በሞራል እና በብቃት መወጣት አለባቸው። እየተሠጠ ያለው ስልጠና ከሌሎች የሠራት ክፍሎች ጋር በመሆኑ የተሞክሮ እና … [Read more...] about ባህር ኃይል ለማዘመን ስልጠናዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ
Ethiopian Navy
ሩሲያ የኢትዮጵያን ባሕር ኃይል ልታዘምን ነው
የሩሲያ መንግሥት ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ለረጅም አመታት የዘለቀ መልካም ዲፕሎማሲያዊ ትብብር ያለው ሲሆን የዚህም ጉብኝት ዓላማ የዚሁ ትብብር አንድ አካል መሆኑ ተመልክቷል ፡፡ የሩሲያ ፌዴሬሽን ባህር ኃይል ልዑክ መሪ በኢትዮጵያ የሩሲያ ፌዴሬሽን ተልዕኮ ሀላፊ ሜጀር ጀነራል ኦስትሪ ኮቭ በጉብኝታቸው ወቅት እንደተናገሩት ፣ የኢትዮጵያ ባህር ኃይል በመዋቅራዊ አደረጃጀቱ ይበልጥ እየዘመነ እንዲመጣና ኢትዮጵያውያን በጋራ የሚኮሩበት ጠንካራ ተቋም ለመገንባት እየተሰራ መሆኑን መገንዘባቸውን ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ላይ ጠንካራ ባህር ኃይልና የመከላከል አቅሟን ይበልጥ ለመገንባት በምታደርገው ሁሉ አቀፍ እንቅስቃሴ ውስጥ በተለያዩ የሥልጠና መስኮች ላይ ሚናዋን መጫወት ትችላለች ተብሏል፡፡ የኢትዮጵያ ባህር ኃይል ዋና አዛዥ ተወካይ ኮሞዶር ዋላፃ ዋቻ ፣ የኢትዮጵያ … [Read more...] about ሩሲያ የኢትዮጵያን ባሕር ኃይል ልታዘምን ነው
በአየርና በውሃ አካል ላይ የታገዘ ተልዕኮ ለመወጣት የሚያስችል ሥልጠና ባሕር ኃይል እየሰጠ ነው
የኢትዮጵያ ባህር ሃይል ዋና አዛዥ ተወካይ ኮሞዶር ዋላፃ ዋቻ፣ የሀገርን ደህንነት ለማስጠበቅ የሚያስችልና ከውስጥና ከውጭ የሚመጡ ችግሮችን የሚመክት ዘመናዊ ባህር ሃይል መገንባት፣ ማደራጀትና ማሰልጠን አስፈላጊ መሆኑን ተናገሩ፡፡ ኮሞዶሩ በባህር ዳር ተገኝተው የባህር ሃይል መሠረታዊ ባህረኞች በውሃ አካል ላይ የሚሰጡ ግዳጆችን ለመወጣት የሚያስችል የውሃ ዋና ሥልጠና ባስጀመሩበት ወቅት እንደተናገሩት፣ የውጭ ሃገራት የእጩ መኮንን ሥልጠናዎችን እና ደብረ ዘይት ባቦጋያ ት/ቤት የውሃ ዋና እና የመርከብ የተግባር ሥልጠናዎችን ማከናወን መቻሉን አስረድተዋል፡፡ አሁን የሚሰጣችሁ ሥልጠና በመርከብ ላይ ሊደረጉ የሚገቡ የጥንቃቄ፤ የአደጋ መከላከል ደንቦችና በውሃ አካል ላይ የሚሰጡ ግዳጆችን ሊያሳልጥ የሚችል ትምህርት በመሆኑ ጠቀሜታው የጎላ ነው ብለዋል፡፡ ይህ የስልጠና አቅም … [Read more...] about በአየርና በውሃ አካል ላይ የታገዘ ተልዕኮ ለመወጣት የሚያስችል ሥልጠና ባሕር ኃይል እየሰጠ ነው