የሩሲያ መንግሥት ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ለረጅም አመታት የዘለቀ መልካም ዲፕሎማሲያዊ ትብብር ያለው ሲሆን የዚህም ጉብኝት ዓላማ የዚሁ ትብብር አንድ አካል መሆኑ ተመልክቷል ፡፡ የሩሲያ ፌዴሬሽን ባህር ኃይል ልዑክ መሪ በኢትዮጵያ የሩሲያ ፌዴሬሽን ተልዕኮ ሀላፊ ሜጀር ጀነራል ኦስትሪ ኮቭ በጉብኝታቸው ወቅት እንደተናገሩት ፣ የኢትዮጵያ ባህር ኃይል በመዋቅራዊ አደረጃጀቱ ይበልጥ እየዘመነ እንዲመጣና ኢትዮጵያውያን በጋራ የሚኮሩበት ጠንካራ ተቋም ለመገንባት እየተሰራ መሆኑን መገንዘባቸውን ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ላይ ጠንካራ ባህር ኃይልና የመከላከል አቅሟን ይበልጥ ለመገንባት በምታደርገው ሁሉ አቀፍ እንቅስቃሴ ውስጥ በተለያዩ የሥልጠና መስኮች ላይ ሚናዋን መጫወት ትችላለች ተብሏል፡፡ የኢትዮጵያ ባህር ኃይል ዋና አዛዥ ተወካይ ኮሞዶር ዋላፃ ዋቻ ፣ የኢትዮጵያ … [Read more...] about ሩሲያ የኢትዮጵያን ባሕር ኃይል ልታዘምን ነው