
የሩሲያ መንግሥት ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ለረጅም አመታት የዘለቀ መልካም ዲፕሎማሲያዊ ትብብር ያለው ሲሆን የዚህም ጉብኝት ዓላማ የዚሁ ትብብር አንድ አካል መሆኑ ተመልክቷል ፡፡
የሩሲያ ፌዴሬሽን ባህር ኃይል ልዑክ መሪ በኢትዮጵያ የሩሲያ ፌዴሬሽን ተልዕኮ ሀላፊ ሜጀር ጀነራል ኦስትሪ ኮቭ በጉብኝታቸው ወቅት እንደተናገሩት ፣ የኢትዮጵያ ባህር ኃይል በመዋቅራዊ አደረጃጀቱ ይበልጥ እየዘመነ እንዲመጣና ኢትዮጵያውያን በጋራ የሚኮሩበት ጠንካራ ተቋም ለመገንባት እየተሰራ መሆኑን መገንዘባቸውን ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ላይ ጠንካራ ባህር ኃይልና የመከላከል አቅሟን ይበልጥ ለመገንባት በምታደርገው ሁሉ አቀፍ እንቅስቃሴ ውስጥ በተለያዩ የሥልጠና መስኮች ላይ ሚናዋን መጫወት ትችላለች ተብሏል፡፡
የኢትዮጵያ ባህር ኃይል ዋና አዛዥ ተወካይ ኮሞዶር ዋላፃ ዋቻ ፣ የኢትዮጵያ ባህር ኃይል የዛሬ ሶስት አመት በአዋጅ መቋቋሙን ገልፀው፣ ክፍሉን በተማረ የሰው ኃይል ለማደራጀት ሥራዎች እየተሰሩ ያሉ መሆኑን ለሩሲያ ልዑካን ቡድን አብራርተዋል።
ከሌሎች ሀገሮች የባህር ኃይሎች አደረጃጀትና ቀደም ሲል ከነበረ የኢትዮጵያ ባህር ኃይል ልምድ በመውሰድ የተሰጠንን ሀገራዊ ተልዕኮ በአግባቡ ለመፈፀም የሚያስችል የተሟላ አደረጃጀት ሰርተን በመከላከያ ፀድቆ ወደ ሥራ ተገብቷልም ብለዋል፡፡
ኮሞዶሩ አያይዘውም ኢትዮጵያ ከባህር ኃይሏ ማግኘት የምትችለውን ጥቅምና ግልጋሎት እንድታገኝ ከሩሲያ ፌደረሽን ባህር ኃይል በተለያዩ የስልጠና ዘርፎች በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ ደርሰናል ብለዋል ሲል የሀገር መከላከያ ሠራዊት በማህበራዊ ገጹ ዘግቧል፡፡
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
,እጅግ መልካም ዜና ነው። እድሜ ለነ መለስ ዜናዊ ፓሊሲ(ኤርማን ኮሄን።ቶኒና ቡሽ)
የባሕር እንድናጣ ቢፈርዱብንም ዛሬ ወግ ደርሶን ይህን ሃይል መመለሱ ለአገራችን ትልቅ ኩራት ለምዕራቡ መሪዎች ግን ራስ ምታት ነው።በጊዜው የባሕር ሃይላችንም ይከበራል።