የዓባይ አጀንዳ ሲቋጭ የቀይ ባህር ጉዳይ መነሳቱ አጀንዳው እጅግ ተደርጎ የታሰበበት ለመሆኑ ማሳያ ተደርጓል። “የቀይባህር አጀንዳ ሃሳብ ማስቀየሪያ ነው” በማለት ለፕሮፓጋንዳ የሚነሱ የማይሳካላቸው በዚሁ መነሻ እንደሆነም ተመልክቷል። እጅግ ሰላማዊ በሆነና በሰጥቶ መቀበል መርህ አማራጮችን አቅርበው ኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤት መሆን እንዳለባት ያመለክቱት ዐቢይ ቀይ ባሕር “ጉዳይ የኅልውና ነው” ብለውታል።
የወንበዴው መሪ መለስ ዜናዊ “መንገዱን ጨርቅ ያድርግላችሁ” ሲል አሰብ ወደብና ቀይ ባህርን አስመልክቶ ለተከራከሩ የሰጠው መልስ ነበር። ኢትዮጵያን የሚያክል አገር የተቆለፈባት እንድትሆን የተስማማው ትህነግ፣ ላለፉት ሠላሳ ዓመታት ኢትዮጵያ አንጡራ ሃብቷን እንድትበትን ፈርዶባት ኖሯል። የድርጅቱ መሪ መለስ “አሰብን ከኢትዮጵያ ከመውሰድ ከኤርትራ መቀማት ይቀላል” በሚል ሥጋት ወደፊት ትግራይን “አገር” የማድረግ ሕልሙን አስልቶ መናገሩን ምስክሮች የሚታወሱት ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በድርጅት ወይም በፓርላማ አባልነታቸው ሳይሆን፣ እንድ አንድ አገር ወዳድ እንደሚናገሩ አስታውቀው እንዳሉት የቀይ ባህርና የዓባይ ጉዳይ ለኢትዮጵያ ህልውና ናቸው። ሁሉም የኢትዮጵያ ንብረት ሆኖ ሳለ፣ ስለ ዓባይ ማንም እንደማይፈራን፣ እና ግን ህጋዊ መብት ስላለን ቀይ ባህር መናገር እንፈራለን ሲሉም ፍርሃቻው አግባብ አልነበረም ብለዋል።
ከዚህ በፊት ዐቢይ አህመድ አዲሱ ዓመት በርካታ ድሎች የሚገኙበት እንደሆነ መናገራቸው አይዘነጋም። ጠቅላዩ ትልቅ ዓለም አቀፍ አጀንዳ ማስቀመጣቸን ተከትሎ ሕዝብ በስፋት እየተነጋገርበት ነው። ዐቢይ አህመድ ያስቅመጡትን ትልቅ አጀንዳ የሰሙ “ምን አለበት ሻለቃ አድማሴ ይህን አዋጅ ቢሰሙ” ብለዋል። (ethio12)
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ካነሱት ነጥቦች መካከል የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል እንደገና እየተዋቀረ ባሕረኞችን ሲያስመርቅ የተነገረውን ተቃውሞ ነው። ኢትዮጵያን ያከለ አገር ባሕር ኃይል ሲኖረው እና ወደፊት ቀይ ባሕርን የራሳችን አድርገን ባሕር ኃይል ለማዘጋጀት ከማሰብ ይልቅ ካሁኑ የተዘጋጀ ኃይል ማብቃት በምን ሥሌት ነው የምንቃወመው? ምን ዓይነት አስተሳሰብስ ነው? የሚሉ ጥያቄዎችን አንስተዋል።
ከዓባይ ግድብ በማይተናነስ ሁኔታ የቀይ ባሕር ፖለቲካ አገር ውስጥ ያለውን ብቻ ሳይሆን በዓለምአቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የፖለቲካ መነጋገሪያ እንደሚሆን ይጠበቃል። የውሃ ፖለቲካ አጥኚዎችም የጠቅላይ ሚኒስትሩን አጀንዳ በቀጣይ በተለያዩ መድረኮች እንደሚወያዩባቸው ተጠቁሟል። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Tesfa says
የጠ/ሚሩ ንግግር ማለፊያ ነው። ችግሩ የራሳችን አንድነትና ህብረት ጭራሽ መጥፋቱ ነው። በዘርና በጎሳ አልፎ ተርፎም በቋንቋ በተሰመረች ሃገር ላይ እየተራኮትን ስለ ቀይ ባህር ማሰቡ ይከብዳል። ግን ጉዳዪ አይነሳ፤ አይጻፍ፤ አይዘከር የሚሉ ሁሉ ተሳስተዋል። ይህ ጥያቄ ዛሬ የተነሳ ሳይሆን ጄ/ጻድቃን ልብሱን ጠቅሎ ትግራይ ገብቶ የራሱን ወታደር እስከ ወጋበት ድረስ አልፎ አልፎ በጽሁፍም ሆነ በንግግር የባህር በርን ጉዳይ ያወሳ እንደነበር የቆመ ይመሰክራል። ለምሳሌ እውቁ ፓለቲከኛ አቶ ልደቱ አያሌው ወያኔን በፓርላማ በዚህ ጉዳይ ላይ እንዳፋጠጡት የሚያሳዪ ቪዲዎችም አሉ።
በድል የሰከረው የያኔው ወያኔ ኤርትራን እወቁልኝ በማለት ሁለቱንም የባህር በሮች እንካችሁ በማለት ካሰረከበ በህዋላ ቆይተው ድራፍት እየጠጡ ነገሩን ሲያስቡት የፓለቲካ ስህተት እንደሰሩ ገብቷቸዋል። ግን የያኔው የወያኔ ስብስብ መሪ አቶ መለስ አፍቃሪ ኤርትራና የሻቢያ ሌላኛው መልክ በመሆኑ ከአቶ ስብሃት ጋር በማበር ሃገሪቱን በር አልባ እንደሆነች እንድትቀጥል አድርጓል። አሁን እንሆ ዳግም በመሪ ደረጃ ጥያቄው መነሳቱና አመላካችና ትውልድ ተሻጋሪ ሃሳብ ማድረጉ ጠቃሚነት አለው። የሃገር መሪዎች ቋሚ አይደሉም። እንኳን በቅኝ ግዛት ሳቢያ የተፈጠሩ ድንበሮች ቀርቶ እንግሊዞችና ጀርመኖች እንዲሁም ራሽያዊያን ድንበራቸው አንዴ ሲሰፋ ሌላ ጊዜ ሲጠብ ይኽው ያለንበት ዘመን ላይ ደርሰናል። ስለሆነም የኦሮሚያ ክልል፤ የአማራ ክልል፤ የትግራይ የአፋር ገለ መሌ እያሉ በድንጋይ ዘመን አስተሳሰብ ከመፋጀት ይልቅ ሁሉም በህበረትና በአንድነት መጀመሪያ ኢትዮጵያዊ ሆኖ በውስጡ የራሱን ወገና ባህል አስጠብቆና የሌላውን አክብሮ የሚኖር ትውልድና ህዝብ እስካልፈጠርን ድረስ እናንሳለን እንጂ አናድግም።
የኢትዮጵያ ቀዳሚ ጠላቷ የወያኔ የዘርና የቋንቋ ፓለቲካ ነው። አሁን እንሆ ኦሮሞዎቹም ብሶባቸው ሰውን በዘሩና በቋንቋው እየለዪ በመፍጀት ላይ ይገኛሉ። እንዲህ ባለ ሰላም በጠፋበት ሃገር ላይ ስለ ወደብ ጉዳይ ማሰብ ይከብዳል። ህዝብ አንድ ሲሆን፤ በምድሩ በሰላም ወጥቶ ሲገባ የሃገር ድንበርና ሌላውም ጉዳይ ሁሉ ፍንትው ብሎ ይታየዋል። ነፍሴ አውጭኝ እያለ ለሚሮጥ፤ ያለዚያም የሚበላው አቶ ጦም ለሚያድር ወገን የባህር በር ጥያቄ የፓለቲካ እንፋሎት ማቀዝቀዣ የጊዜው ቱልቱላ እንጂ እውነት መስሎ አይታየውም። በኦሮሞና በአማራ ክልል ያለው መገዳደል መቆም አለበት። ያኔ ሰው ረግቶ የሚነገረውንም ሆነ የሚጻፈውን አንቦ ለመረዳትና ሃሳብ ለመስጠት ጊዜ ያገኛል።
በመጨረሻም በዚህ ጉዳይ ላይ የዪቱቭ ሳንቲም ለመልቀም ነገርን እያጋነኑና የሌለና ያለን ወሬ እያዳመቁ ሁለቱ ሃገሮች እንዲላተሙ ጥረት ሲደረግ እያየንና እየሰማን ነው። የጅል መንጋ ማን ለማን ይሞታል? ማን እየሞተ ማን ይኖራል የምን ጦርነት ነው? በምንም ሂሳብ ኤርትራና ኢትዮጵያ በዚህም ይሁን በሌላ ውጊያ ውስጥ መግባት የለባቸውም። ያ ከሆነ መገዳደላችን ለማስቀጠል ምዕራባዊያንና አረቦች ያሸከሙን አጀንዳ እንጂ ኤርትራም ሆነች ኢትዮጵያ ከራሳቸው ያመነጩት ሃሳብ እንዳልሆነ እንገነዘባለን። ሰው ከትግራዪና ከአማራው መተላለቅ፤ በስመ ነጻ አውጭ ሰው ከሚያግተው ከኦነጉ ሽኔ አረመኔነትና ሰው በላነት መማር አለበት። ነጻ አውጭ ብሎ ነገር የለም። ባርነት አምጪ እንጂ። ለሃገር ለወገን ለሃይማኖትህ ለዚህና ለዚያ እየተባለ መተላለቁም ዋጋ ይብሉን። በተቻለ መጠን ሁሉን ነገር በሰላም ለመቋጨት የሚደረጉ ጥረቶች ግን ለአሁኑም ይሁን ለወደፊቱ ለህዝባችን ጠቃሚነቱ አያጠያይቅም። በቃኝ!
Muhammed says
ትክክል
kokob solomon says
እኛ ኤርትራዊያን የማንም ኣገር ድንበር ጥሰን ገብተን ኣናውቅም ሆኖ ግን ቀይ ባህር ለኛ ደማችን ነው ። እንኳን ልትነካው ማሰቡ ራሱ ለውንድም የኢትዩጵያ ሕዝብ ሳይሆን ላንተ (ተላላኪ) እንፍርድህ ኣለን ይገርምሃል ስሙኑን ስራ ቀዝቅዞናል